የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች

የቤተ ክርስቲያናችን ዓላማ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ማስተማርና መንፈሳዊ አገልግሎትን ለእግዚአብሔርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ማበርከት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ሳይዛባ፣ ሳይፋለስ፣ ፈሩን ሳይለቅ በነበረበት ለማስቀጠል የመንበረ ሐዋርያት ወራሾች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በዓመት ሁለት ጊዜ በቋሚነት እየተሰበሰቡ፣ ስለአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እየገመገሙ፣ እየመከሩና እየወሰኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እምነትዋንና ሥርዓቷን እንዲጠብቁ ቅዱሳን አበው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ደንግገዋል፡፡

በፌስቡክ ያግኙን

ከግንቦት 1 ቀን እስከ ሰኔ 14 ቀን 2009 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

የሢመተ ኤጴስ ቆጶሳት ምርጫና የግብጻውያን ስርዋጽ ከሕግ መጽሐፍ ስለመሰረዝና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የኑፋቄ ትምህርት አስፋፊዎችን ስለማውገዝ የተሰጡ ውሳኔዎች

ግንቦት 2 ቀን 2009 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

“ወይእዜኒ ዕቀቡ ርእሰክሙ ወኵሎ መራዕየ ዘሀሎ ኀቤክሙ፤ አሁንም ራሳችሁንና በእናንተ ሥር ያለውን መንጋ ሁሉ ጠብቁ፤”(የሐዋ.ሥራ 20፡28)

ጥቅምት 11 ቀን እስከ 16 ቀን 2009 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

በወቅታዊ የሀገራችን ሰላምና ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ሰማዕት ተብለው እንዲጠሩ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መወሰኑ የሚገለጽ ውሳኔ

ጥቅምት 12 ቀን 2009 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

“ኦ አባ ቅዱስ ዕቀቦሙ በስምከ ለእለ ወሀብከኒ ከመይኩኑ አሐደ ብነ ከማነ፤ ቅዱስ አባት ሆይ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው” (ዮሐ17፡11)፡፡

ከግንቦት 16 ቀን እስከ ሰኔ 1 ቀን 2008 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቊጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልአተ ጉኤው የዘንድሮውን መደበኛ የርክበ ካህናት ስብሰባ የጉባኤው መክፈቻ ሥርዐተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከበዓሉ ዋዜማ ከግንቦት 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ለ16 ቀናት ያህል ባደረገው ጉባኤ ጠቀሜታ ባላቸው የአጀንዳ ነጥቦች ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡ ከእነዚህም መካከል የሚከተሉት በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡