የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች

የቤተ ክርስቲያናችን ዓላማ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ማስተማርና መንፈሳዊ አገልግሎትን ለእግዚአብሔርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ማበርከት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ሳይዛባ፣ ሳይፋለስ፣ ፈሩን ሳይለቅ በነበረበት ለማስቀጠል የመንበረ ሐዋርያት ወራሾች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በዓመት ሁለት ጊዜ በቋሚነት እየተሰበሰቡ፣ ስለአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እየገመገሙ፣ እየመከሩና እየወሰኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እምነትዋንና ሥርዓቷን እንዲጠብቁ ቅዱሳን አበው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ደንግገዋል፡፡

በፌስቡክ ያግኙን

ሚያዝያ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

‹‹ኀበ ሀለዉ ክልኤቱ ወሠለስቱ ጉቡኣን በስምየ አነ እሄሉ ማእከሌሆሙ ህየ -- ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እገኛለሁ።›› (ማቴ. 18÷20)

ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓ/ም፡ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት

"ዘሰ አምነኒ በቅድመ ሰብእ አነኒ አአምኖ በቅድመ አቡየ ዘበሰማያት በሰው ፊት ያመነኝን ሰው እኔም በሰማያዊ አባቴ ፊት አምነዋለሁ።" (ማቴ. 10፥32)

ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ አይኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በግፍ ስለተገደሉት ኢትዮጵያውያን በመስቀል አደባባይ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን አስተላልፈዋል፡፡

ይህ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን አሠቃቂ የወንጀል ድርጊት ከሰው ልጅ ተፈጥሮኣዊ ተግባር የወጣ ደረቅ ወንጀል ስለሆነ፣ ልንቃወምና ልንመክት የምንችለው በጥልቀትና በተረጋጋ መንፈስ በመሆን በመላው ዓለም ካሉ ከፀረ ሽብረ ግብረ ኀይላት ጋር በመተባበር ስለሆነ በትዕግሥትና በጥበብ የሰው ልጅ ሉዓላዊ ክብር እንዳይጣስ በነፃነት ሊኖርባት በተሰጠችው ምድር የሕይወት ዋስትና እንዲኖረው ለማስቻል ሁሉም ነቅቶና ተግቶ ኀላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ በሰማዕትነት ስለተሠዉ ኢትዮጵያውያን የቅዱስነታቸው መግለጫ

ግፉዓን ይትማሠጥዋ ለመንግሥተ ሰማያት በሃይማኖታቸው ምክንያት ግፍ የሚደርስባቸው መንግሥተ ሰማያትን ይናጠቋታል፡፡ (ማቴ. 11፣12)

ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሊቢያ ሀገር በንጹሓን ወገኖች ላይ ስለተፈጸመው አሠቃቂ ግድያ ስለማውገዝ በቅዱስነታቸው የተሰጠ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ

የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፈጣሪ የተሰጠች የማንኛውም የሰው ልጅ ሕይወት ኀላፊነት በማይሰማቸውና በእነርሱ ላይ ሊደረግ በማይፈቅዱ ምንም ዐይነት ሰብኣዊ ርኅራኄ በሌላቸው እንድትቀጠፍ ስለማትፈቅድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን አሠቃቂ ድርጊት በጽኑ ትቃወማለች፣ አጥብቃም ታወግዘዋለች፡፡

ከጥቅምት 12 እስከ 26 ቀን 2007 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

ምልአተ ጉባኤው ከጥቅምት 12-26 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ ባደረገው ምልአተ ጉባኤ በተመረጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና የሕግ ባለሙያዎች ሲደከምበት የቆየውን የተሻሻለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያን አጽድቋል፡፡ በ33ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተወያይቶ ባጸደቀው የዐቋም መግለጫና በሌሎችም በርካታ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ በስፋትና በጥልቀት ሲወያይ ከሰነበተ በኋላ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ስብሰባውን በጸሎት አጠናቋል፡፡