የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ዐበይት የሥራ ክንውኖችና አባታዊ መመሪያዎች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በቅዱስ ፓትርያርክነት ሥልጣን ከተሠየሙበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ በቅዱስ ሲኖዶስ እያስወሰኑ ለቤተ ክርስቲያናችን በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መቀላጠፍ ዐይነተኛ ጠቀሜታ ያላቸው መመሪያዎችን አስተላልፈዋል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጒዞ
መድኀኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላካዊ የማዳን ሥራውን ወደ ዓለም እንዲያዳርሱ ዐሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርትን ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል መርጦ ለሦስት ዓመት ከአራት ወር ከዐሥር ቀን አምላካዊ ትምህርተ ወንጌልን አስተምሮአቸዋል፡፡ ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ አምላካዊ ትምህርቱን ሰምተው፣ መለኮታዊ ገቢረ ተኣምሩን አይተው፣ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ተረድተዋል፡፡ (ዮሐ. 6) ካመኑ በኋላ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፤ ያመነ የተጠመቀ ይድናል@ ያላመነ ግን ይፈረድበታል”፡፡ (ማር.16፥15-16) ብሎ አዘዛቸው፡፡ በክርስትና ትምህርት ይህ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠው ወንጌልን ለዓለም ሁሉ የማስተማር (የመስበክ) ተልእኮ “ዐቢይ ተልእኮ” (great mission) ተብሎ ይጠራል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት የተከበረው የጸሎተ ሐሙስ በዓል እንደተለመደው በጾም፣በጸሎት፣ በኅጽበተ እግር ሥነ ሥርዐትና በሥርዐተ ቅዳሴ ተከብሯል፡፡ሙሉ ሥነ ሥርዐቱ በቅዱስ ፓትርያርኩ የተመራ ሲሆን ቀኑ የትሕትና የፍቅር ስለሆነ ይህንን የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትሕትና ተግባር ሁሌም ከልባችን ጽላት ላይ በመጻፍ ምእመናን የሕይወታቸው መርሕ እንዲያደርጉት አሳስበዋል፡፡



ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ: ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ በኢትዮጵያ የጣልያን አምባሳደር ሆነው የተሾሙትን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ (Sem Fabrizi) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በኢትዮጵያ አዲሱ የኢጣልያ አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። በውይይቱ ወቅት ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአዲሱ ተሿሚ አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ፣ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል። ቅዱስነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊትና ታሪካዊት መሆኗን […]
“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ”
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሐዱ አምላክ አሜን !! ‹‹ወነአምር ከመ ለእመሂ ተነሥተ ቤተ ማኅደርነ ዘበምድር ዘውእቱ ሥጋ ብነ ሕንጻ በኀበ እግዚአብሔር በሰማያት ዘኢገብሮ እደሰብእ፡- በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን፡፡›› (2ቆሮ. 5፡1) በልዩ ልዩ ጊዜያት ዐረፍተ ዘመን የገታቸውን ወገኖች ልንሸኝ እንችላለን፤ የአንዳንድ ሰዎች ሞት ግን […]
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ በ13ኛው ዓመት በዓለ ሢመተ ፓትርያርክ በዓል አከበባር ሥነ ሥርዓት ላይ ያስተላለፉት አባታዊ ሙሉ መልእክት
“ወቦቱ ረከብነ ጸጋ ወተሠየምነ ሓዋርያተ ከመ ናስምዖሙ ለኣሕዛብ ወይእመኑ በስሙ፤በስሙ ያምኑ ዘንድ ቃለ ወንጌልን ለኣሕዛብ እንድናሰማ የተሾምንበት ሓዋርያነት ከሱ የተገኘ ጸጋ ነው›› (ሮሜ.፩÷፭)