የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ዐበይት የሥራ ክንውኖችና አባታዊ መመሪያዎች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በቅዱስ ፓትርያርክነት ሥልጣን ከተሠየሙበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ በቅዱስ ሲኖዶስ እያስወሰኑ ለቤተ ክርስቲያናችን በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መቀላጠፍ ዐይነተኛ ጠቀሜታ ያላቸው መመሪያዎችን አስተላልፈዋል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጒዞ
መድኀኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላካዊ የማዳን ሥራውን ወደ ዓለም እንዲያዳርሱ ዐሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርትን ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል መርጦ ለሦስት ዓመት ከአራት ወር ከዐሥር ቀን አምላካዊ ትምህርተ ወንጌልን አስተምሮአቸዋል፡፡ ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ አምላካዊ ትምህርቱን ሰምተው፣ መለኮታዊ ገቢረ ተኣምሩን አይተው፣ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ተረድተዋል፡፡ (ዮሐ. 6) ካመኑ በኋላ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፤ ያመነ የተጠመቀ ይድናል@ ያላመነ ግን ይፈረድበታል”፡፡ (ማር.16፥15-16) ብሎ አዘዛቸው፡፡ በክርስትና ትምህርት ይህ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠው ወንጌልን ለዓለም ሁሉ የማስተማር (የመስበክ) ተልእኮ “ዐቢይ ተልእኮ” (great mission) ተብሎ ይጠራል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት የተከበረው የጸሎተ ሐሙስ በዓል እንደተለመደው በጾም፣በጸሎት፣ በኅጽበተ እግር ሥነ ሥርዐትና በሥርዐተ ቅዳሴ ተከብሯል፡፡ሙሉ ሥነ ሥርዐቱ በቅዱስ ፓትርያርኩ የተመራ ሲሆን ቀኑ የትሕትና የፍቅር ስለሆነ ይህንን የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትሕትና ተግባር ሁሌም ከልባችን ጽላት ላይ በመጻፍ ምእመናን የሕይወታቸው መርሕ እንዲያደርጉት አሳስበዋል፡፡



ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ምርቃት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጡ
ቅዳሴ ቤቱ ሲከበር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፤ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የኢትዮጵያ […]
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶሳዊ በመሆኗ አበው ቅዱሳን በፍትሕ መንፈሳዊና በጉባኤ አድያም ዘአንጾኪያ “ወይኩን ሲኖዶስ ዘጳጳሳት ፪ተ ጊዜያተ በበዓመት – የጳጳሳት ጉባኤም በዓመት ሁለት ጊዜ ይሁን” […]
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማስመልከት ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ
ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት እንደሚከተለው ነው፦ መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ‹‹ተዘከሩ መቁሓነ ዘከመ ተሞቃሕክሙ ምስሌሆሙ ወእለ ተሣቀዩ ከመ ዘሀለውክሙ በሥጋክሙ፡- ከእነርሱ ጋር አብራችኋቸው እንደታሰራችሁ ሆናችሁ እስረኞችን ዐስቡ፤ መከራ የጸናባቸውንም በሥጋችሁ ከእነርሱ ጋር እንዳላችሁ ሆናችሁ ዐስቡ›› (ዕብ. 13፡3) እውነተኛ እምነትም […]
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ ኣምላክ ኣሜን! ብፁዕ ኣቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ ኣስኪያጅ፤ ብፁዕ ኣቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ፤ ብፁዕ ኣቡነ ሕርያቆስ የኣዲስ ኣበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት፣ በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልኣተ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፦ ማሕየዊት በምትሆን ሞቱ ሰማያውያንና […]
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወኣምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመተ ምሕረት
በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሐዱ ኣምላክ ኣሜን፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ፣ በቤዛዊ መሥዋዕትነቱ ከሞተ ኃጢኣት ታድጎ የትንሣኤ ሙታንን በር የከፈተልን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው […]
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ: ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ በኢትዮጵያ የጣልያን አምባሳደር ሆነው የተሾሙትን አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ (Sem Fabrizi) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በኢትዮጵያ አዲሱ የኢጣልያ አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። በውይይቱ ወቅት ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአዲሱ ተሿሚ አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ፣ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል። ቅዱስነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊትና ታሪካዊት መሆኗን […]
“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ”
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሐዱ አምላክ አሜን !! ‹‹ወነአምር ከመ ለእመሂ ተነሥተ ቤተ ማኅደርነ ዘበምድር ዘውእቱ ሥጋ ብነ ሕንጻ በኀበ እግዚአብሔር በሰማያት ዘኢገብሮ እደሰብእ፡- በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን፡፡›› (2ቆሮ. 5፡1) በልዩ ልዩ ጊዜያት ዐረፍተ ዘመን የገታቸውን ወገኖች ልንሸኝ እንችላለን፤ የአንዳንድ ሰዎች ሞት ግን […]
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ በ13ኛው ዓመት በዓለ ሢመተ ፓትርያርክ በዓል አከበባር ሥነ ሥርዓት ላይ ያስተላለፉት አባታዊ ሙሉ መልእክት
“ወቦቱ ረከብነ ጸጋ ወተሠየምነ ሓዋርያተ ከመ ናስምዖሙ ለኣሕዛብ ወይእመኑ በስሙ፤በስሙ ያምኑ ዘንድ ቃለ ወንጌልን ለኣሕዛብ እንድናሰማ የተሾምንበት ሓዋርያነት ከሱ የተገኘ ጸጋ ነው›› (ሮሜ.፩÷፭)
የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
‹‹ወልበሱ ወልታ እግዚአብሔር በዘትክሉ ተቃውሞቶ ለመናግንተ ሰይጣን፤
የሰይጣንን ሽንገላ መቃወም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን ጋሻ ልበሱ›› (ኤፌ.፮፥፲፩)፤
ታኅሣሥ 29 ቀን 2018 ዓ.ም የልደት በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ
“ወበዝንቱ ተዓውቀ ፍቅሩ ለእግዚአብሔር ላዕሌነ እስመ ለወልዱ ዋሕድ ፈነዎ ውስተ ዓለም ከመ ንሕየው በእንቲኣሁ፤ ወዝንቱ ውእቱ ፍቅሩ ለእግዚአብሔር፡- የእግዚአብሔር ፍቅሩ በእኛ ዘንድ ተገለጠ፤ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነው፤ (፩ዮሓ. ፬፥፱)