https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/007-3.jpg
664
1000
tc3
https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/logo-am.svg
tc32016-05-25 08:46:492024-12-07 08:48:48ግንቦት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬየቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች
የቤተ ክርስቲያናችን ዓላማ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ማስተማርና መንፈሳዊ አገልግሎትን ለእግዚአብሔርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ማበርከት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ሳይዛባ፣ ሳይፋለስ፣ ፈሩን ሳይለቅ በነበረበት ለማስቀጠል የመንበረ ሐዋርያት ወራሾች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በዓመት ሁለት ጊዜ በቋሚነት እየተሰበሰቡ፣ ስለአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እየገመገሙ፣ እየመከሩና እየወሰኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እምነትዋንና ሥርዓቷን እንዲጠብቁ ቅዱሳን አበው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ደንግገዋል፡፡
በፌስቡክ ያግኙን
https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/007-3.jpg
664
1000
tc3
https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/logo-am.svg
tc32016-05-25 08:46:492024-12-07 08:48:48ግንቦት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ
ሚያዝያ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በንጹሓን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሠቃቂ ግፍ
“ወይቤ እግዚአብሔር ንግበር ሰብአ በአርኣያከ ወበአምሳሊከ -- እግዚአብሔርም አለ ሰውን በአርኣያችንና በአምሳላችን እንፍጠር” (ዘፍ.1፥26)

የካቲት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ቀናት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
«ኅሡ ሰላማ ለብሔር እስመ በሰላመ ዚኣሃ ይከውን ሰላምክሙ፤
የአገርን ሰላም ሹ ፈልጉ የአገራችሁ ሰላም የእናንተ ሰላም ነውና።

ጥቅምት 12 ቀን እስከ 22 ቀን 2008 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በመደበኛ ስብሰባ፤ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ተራ ቍጥር 164 በተደነገገው መሠረት የመክፈቻው ሥርዐተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከበዓሉ ዋዜማ ከጥቅምት 11 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ለዐሥራ ሁለት ቀናት ያህል ባደረገው ስብሰባ፡ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዳይፋለስ ለመጠበቅና ለመቈጣጠር፤ ካህናት በመንፈሳዊው ተልእኮአቸው እንዲፋጠኑ ለማስተባበር፤ ምእመናን በምግባር፣ በሃይማኖት ጸንተው እንዲኖሩ ለማስተማር፤ እግዚአብሔር የሚመሰገንበትን፣ ቤተ ክርስቲያን የምትገለገልበትን ሥርዐት ለመወሰን፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ሥራውን በጸሎት ጀምሮአል፡፡

ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ
“ምንተ ይቤ መንፈስ ቅዱስ ለአብያተ ክርስቲያናት፤ መንፈስ ቅዱስ አብያተ ክርስቲያናትን አስመልክቶ ምን አለ?” (ራእ. 2፥7)፡፡

ሚያዝያ 27 ቀን እስከ 30 ቀን 2007 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡
“የሊቢያ ሰማዕታት”
ክርስቲያን በመሆናቸው በሊቢያ የተገደሉ 30 ኢትዮጵያውያን እና 21 የግብጽ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሰማዕታት በመባል በአንድነት እንዲታሰቡ ስለመወሰኑ፡፡