የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች

የቤተ ክርስቲያናችን ዓላማ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ማስተማርና መንፈሳዊ አገልግሎትን ለእግዚአብሔርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ማበርከት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ሳይዛባ፣ ሳይፋለስ፣ ፈሩን ሳይለቅ በነበረበት ለማስቀጠል የመንበረ ሐዋርያት ወራሾች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በዓመት ሁለት ጊዜ በቋሚነት እየተሰበሰቡ፣ ስለአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እየገመገሙ፣ እየመከሩና እየወሰኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እምነትዋንና ሥርዓቷን እንዲጠብቁ ቅዱሳን አበው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ደንግገዋል፡፡

በፌስቡክ ያግኙን

ሐምሌ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ ልዩ አስቸኳይ ጉባኤ

ሐምሌ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ ልዩ አስቸኳይ ጉባኤ አድርጓል በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የቆየውን ልዩነት እንዲያበቃ ለማድረግ ሰላምና አንድነትን ለማምጣት እንዲቻል ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፣የቅዱስ ሲኖዶስን ወሳኔ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከሐዋርያዊ መልእክት ጋር አስተላልፈዋል፡፡

ከሚያዝያ 24 ቀን እስከ 29 ቀን 2010 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ አምስት ንኡስ አንቀጽ 164 በተደነገገው መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ የዘንድሮውን የርክበ ካህናት ጉባኤ በማስመልከት የስብሰባው መክፈቻ ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከበዓሉ ዋዜማ ከሚያዝያ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ለአንድ ሱባኤ ያህል ባደረገው ስብሰባ ለሀገራችንና ለቤተ ክርስቲያናችን የሚበጁ ጠቀሜታ ያላቸውን ውሳኔዎች አሳልፎአል፡

ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

“ዘይሁብ መርሐ ርቱዐ ለቤተ ክርስቲያን” ለቤተ ክርስቲያን የተስተካከለ መርሕን የሚሰጥ እግዚአብሔር አምላክ ነው› (መጽሐፈ ኪዳን)፡፡

ከጥቅምት 12 ቀን እስከ 21 ቀን 2010 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 164 በተደነገገው መሠረት ምልአተ ጉባኤው ከጥቅምት 6 ቀን 201ዐ ዓ.ም. ጀምሮ የመንበረ ፓትርያርኩን አጠቃለይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤና ዓመታዊውን የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ ለ15 ቀናት ወሳኝ በሆኑ የአጀንዳ ነጥቦች ተወያይቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፎአል፡፡

ጥቅምት 12 ቀን 2010 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

“ወዘንተ ባሕቱ አእምር ከመ በደኃረ መዋዕል ይመጽኣ ዓመታት እኩያት ወይከውኑ ሰብእ መፍቀርያነ ርእሶሙ፡፡ ነገር ግን በኋለኞቹ ዓመታት ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱበት ክፉ ዘመን እንደሚመጣ ዕወቅ” (2ኛ ጢሞ.9.1)

ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም የኤጲስ ቆጶሳት ሥርዐተ ሢመት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ክብርና ሥነ ሥርዐት ተፈጽሟል፡፡

“አኮ አንትሙ ዘኀረይክሙኒ አላ አነ ኀረይኩክሙ ወሤምኩክሙ ከመ ትሑሩ ወፍሬ ትፍረዩ፤ እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብ በስሜ የምትለምኑትን እንዲሰጣችሁ፣ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ፣ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ”፡፡ (ዮሐ 15፡16)