የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች

የቤተ ክርስቲያናችን ዓላማ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ማስተማርና መንፈሳዊ አገልግሎትን ለእግዚአብሔርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ማበርከት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ሳይዛባ፣ ሳይፋለስ፣ ፈሩን ሳይለቅ በነበረበት ለማስቀጠል የመንበረ ሐዋርያት ወራሾች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በዓመት ሁለት ጊዜ በቋሚነት እየተሰበሰቡ፣ ስለአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እየገመገሙ፣ እየመከሩና እየወሰኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እምነትዋንና ሥርዓቷን እንዲጠብቁ ቅዱሳን አበው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ደንግገዋል፡፡

በፌስቡክ ያግኙን

ከግንቦት 14 ቀን እስከ ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

የሕዝብና ቤት ቈጠራው በትክክል ይካሄድ፣ ስለተመለሡልን ሕንጻዎች በማመስገን ቤተ ክርስቲያናችን ከመንፈሳዊ አገልግሎት በተጨማሪ በማኅበራዊ ዘርፍ ለሀገር እድገትና ለሕዝቦች ኑሮ መሻሻል፣ በተለይም ለሀገራዊ ሰላምና አንድነት በመቆም ድርሻዋን እንድትወጣ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል

ግንቦት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

“ወናሁ ወሀብኩክሙ ሥልጣነ ትኪዱ ዲበ ዐቃርብት ወዲበ አራዊተ ምድር ወዲበ ኵሉ ኀይለ ጸላኢ ወአልቦ ዘይነክየክሙ እነሆ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ በጠላትም ኀይል ሁሉ ላይ ሥልጣንን ሰጥቻችኋለሁ የሚጐዳችሁም ምንም የለም” (ሉቃ 10፥19)፡፡

ከጥቅምት 11 ቀን እስከ 21 ቀን 2011 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቍጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልአተ ጉባኤው የመክፈቻው ሥርዐተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የተለመደውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ሲያካሂድ ሰንብቶ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሚበጁ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡

ጥቅምት 12 ቀን 2011 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

ወአንገለጉ ሐዋርያት ወቀሲሳን ከመ ይርአዩ ዘይገብሩ በእንተዝ ነገር፣ ሐዋርያትና ቀሳውስትም ስለዚህ ነገር ለመመካከር ተሰበሰቡ