• Amharic  
  • English  
  • ቀዳሚ ገጽ
  • የኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
    • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • ልዩ ጽ/ቤት
    • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት
    • የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች
    • የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
    • የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጒዞ
  • ቃለ በረከት
  • ዜና መዋእል
  • አርዕስተ ሊቃነ ጳጳሳት
  • ያግኙን
  • Menu Menu

ከግንቦት 14 ቀን እስከ ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቍጥር 164 ድንጋጌ መሠረት ከግንቦት 14-ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደውን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አስመልከቶ ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፤ ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በጸሎት የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ጉዳዩች ላይ ለ18 ቀናት ሲመክር ቆይቶ በርካታ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሚበጁ ጠቃሚ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚህም መሠረት፡-

1. ለጉባኤው መክፈቻ የቀረበው ንግግር ቤተ ክርስቲያናችን ለምታከናውነው መንፈሳዊ ተግባር በእጅጉ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘው በቀጣይ ለሚደረገው የሥራ ስምሪት መመሪያ በማድረግ ጉባኤው አጽድቋል፡፡
2. ከግንቦት 2010 – ግንቦት 2011 ዓ.ም. በቋሚ ሲኖዶስና በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተወስነው የተላለፉ ጉዳዮች አፈጻጸማቸው በእጅጉ ውጤታማ መሆናቸውን ጉባኤው ተቀብሎ አጽድቋል፡፡
3. የቋሚ ሲኖዶስ ሥልጣንና የሥራ አፈጻጸም አስመልክቶ ተከሠቱ በተባሉ የሥራ አፈጻጸሞችና ታዩ በተባሉ ግድፈቶች ጉባኤው በሰፊው ተነጋግሮ በቀጣይ ማንኛውም መንፈሳዊም ሆነ ማኅበራዊ ጉዳዮች ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን መሠረት አድርጎ እንዲሠራ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
4. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሌሎችም መላው አህጉረ ስብከት እየታዩ ባሉ ችግሮች ላይ በመነጋገር፣ ለቀጣዩ የቤተ ክርስቲያናችን መልካም አስተዳደር ጠቃሚ ግብአቶችን ማግኘት እንዲቻል ችግሮቹን አጥንተውና ለይተው የሚያቀርቡ ብፁዓን አባቶችና ባለሙያዎች እንዲሰየሙ ተደርጓል፡፡
5. ከአገር ውጭና በአገር ውስጥ ባሉ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተከሥተው የነበሩ ችግሮች በአጥኚ ልኡካን ተጣርቶ በቀረበ አጀንዳ ላይ በመነጋገር ለአብያተ ክርስቲያናቱ መፍትሔ ይሆናል የተባለ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
6. የቤተ ክርስቲያኒቱ ቤቶችና ሕንጻዎች ሆነው ሳለ ያለአግባብ ተወርሰው የነበሩ በመንበረ ፓትርያርኩ ኩታ ገጠም የሚገኙ ሕንጻዎች በክቡር የአገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ቍርጠኛ አመራር በመመለሳቸው፣ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ መንግሥት ለቤተ ክርስቲያናችን መብት መጠበቅ የሰጠውን ትኵረት በማድነቅ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከፍተኛ ምስጋና አቅርቧል፡፡
7. በውጭ አገር የሚገኙ አህጉረ ስብከትን በማጠናከር መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎታቸውን ማስፋፋት እንዲቻል ከቃለ ዐዋዲው ጋር እና ከየአገሮቹ መንግሥታት ሕግ ጋር የተጣጣመ ደንብ እንዲዘጋጅና ለጥቅምቱ 2012 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንዲቀርብ ተወስኗል፡፡
8. ለተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት፣ ለአብነት ት/ቤቶች፣ ሰው ሠራሽ አደጋ ለደረሰባቸው አብያተ ክርስቲያናት፣ ለተፈናቀሉ ወገኖች፣ ለጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕንጻ ማደሻ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
9. መንግሥት ዜጎች እንዲቈጠሩ በያዘው መርሐ ግብር መሠረት የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች በትክክል እንዲቈጠሩ፣ ቈጠራውም በሰላም እንዲከናወንና አገራዊው ተልእኮውም እንዲሳካ በየአህጉረ ስብከቱ ትምህርት እንዲሰጥ አስፈላጊውም ክትትል እንዲደረግ የኮሚቴ አባላት እንዲሰየሙ ተደርጓል፡፡
10. በጉባኤው፡- “ግጭቶችና አፈታታቸው በዓለም ዐቀፍና በአገር ዐቀፍ እይታ” በሚል ስለ ወቅታዊ የሀገራችን ሰላምና ሊደረግ ስለሚገባው ሐዋርያዊ ተልእኮ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ በስፋት በመነጋገር በአገራችን ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሥርዐት እንዲያድግ፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን፣ ልማት እንዲጐለብትና ድህነት እንዲወገድ በሁሉም አቅጣጫ መሥራት እንደሚያስፈልግ ለሚመለከታቸው ሁሉ ቅዱስ ሲኖዶስ አሳስቧል፡፡
11. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ሆነው በከፍተኛ ትምህርት ቤቶች በሚቆዩባቸው ዓመታት ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው ተከብሮ፣ የእምነት ነፃነታቸው ተረጋግጦ፣ እንደ እምነታቸው ሥርዐት በዓመት ውስጥ ባሉ ሰባት አጽዋማት የመጾም መብታቸው ተጠብቆ፣ አስፈላጊው አቅርቦት እንዲደረግላቸው፣ ሃይማኖታዊ በዓላትንም በሚያከብሩበት ጊዜያት የኖረና የቆየውን ትውፊታዊ አልባሳትን የመልበስ መብታቸው እንዲጠበቅ ለየኮሌጆቹና ዩንቨርሲቲዎች የቅዱስ ሲኖዶሱ ማሳሰቢያ እንዲደርሳቸው ወስኗል፡፡
12. የአገራችንን የቱሪስት መስሕብነት ምክንያት በማድረግ ዜጎች በቅድስናና በፈሪሀ እግዚአብሔር ተከብረው የሚታወቁባት የአገራችንን ታሪክ የሚቀይር የዜጎችን መልካም ሥነ ምግባር የሚለውጥ ሕገ ተፈጥሮንና የተቀደሰውን ሥርዐተ ጋብቻን የሚያበላሽ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የተወገዘ ግብረ-ሰዶምን በአገራችን ለማስፋፋት፣ በዚህም የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ቅድስና የሚጐዳ ሕገ-ወጥ ተግባር ለመፈጸም፤ መቀመጫውን በአሜሪካን ሀገር ያደረገው የግብረ ሰዶማውያን አስጐብኚ ድርጅት በመቃወም ወደ ቅድስት አገራችን ኢትዮጵያ እንዳይገባ፣ ቅዱሳት መካናትንም እንዳይጐበኝ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አውግዟል፡፡ የሀገራችን ዜጎች ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንም ከእንዲህ ዐይነት የአገራችንን መልካም ገጽታና መልካም ሥነ-ምግባርን ከሚያበላሽ፣ በሃይማኖት ትምህርት ተጠብቆ የቆየው ባህላችንን ከሚያጠፋ፣ የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ጠላት ከሆኑ ወራሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ፣ በሀገራችንም ይህንን ሕገ-ወጥ ተግባር በመደገፍ እየተባበሩ ያሉት ግለሰቦችና ድርጅቶች ሁሉ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ቅዱስ ሲኖዶስ አበክሮ ያሳስባል፡፡
13. ወቅታዊውን የቤተ ክርስቲያን ችግር አስመልክቶ በስፋት ሲነጋገር የሰነበተው ጉባኤ፣ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንና በምእመናን ተከታዮቿ ላይ እየደረሰ ያለው፡-

• የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠል፣
• የክርስቲያኖችን መገደል እና ከቀያቸው መፈናቀል፣
• በሃይማኖታቸውና በሃይማኖታዊ ሥርዐታቸው ላይ ተጽዕኖ ማድረግ፣
• የአብያተ ክርስቲያናት ነባር የይዞታ ቦታዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ መቀማት፣
• ለቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅበራዊና ልማታዊ ተግባር በጎ ፈቃድ አለማሳየትና የመሳሰሉት፤
ሪፖርቶች ከየአህጉረ ስብከቱ ቀርበው ጉባኤው በኀዘን ተመልክቶታል፡፡ በዚሁ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ አገሪቱንና ሕዝቡን ይመራሉ ተብለው አደራ ለተቀበሉ የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች ሁሉ ማእከላዊው መንግሥት አስፈላጊውን መመሪያ እንዲሰጣቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ጠይቋል፡፡

14. በየሦስት ዓመቱ በቅዱስ ሲኖደስ ምልአተ ጉባኤ የሚመረጡ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምርጫ አስመልክቶ በሰፊው በመወያየትና አስፈላጊውን ጥናት በማድረግ፡- (ሀ) ብፁዕ አባ ዮሴፍ የምሥራቅ ጐጃም ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ፣ (ለ) ብፁዕ አባ ያሬድ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በማድረግ ለቀጣይ ሦስት ዓመታት እንዲሠሩ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሰይሟል፡፡ ከዚህም ጋር አዲስ የሀገረ ስብከት ደረጃ የተሰጣቸው ዞኖችና መምሪያዎች ላይ ብፁዓን አባቶችን መድቧል፡፡
15. ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው” የሚለውን መርሕ ተከትላ፣ ሰላሟን፣ ፍቅርዋንና አንድነትዋን ጠብቃ፣ ከውጭ የሚመጡባትን ባዕዳን ወራሪዎች በመመከት ክብርዋንና ልዕልናዋን ለረጅም ዘመናት ጠብቃና አስጠብቃ የኖረች፣ ወደፊትም በዚሁ ጸንታ የምትኖር ታላቅ ሀገር መሆኗ ይታወቃል፡፡ ሕዝቦችዋም በአሁኑ ዘመን የሚታዩትን ያልተለመዱ ባሕርያት በሰከነ መንፈስ ቆም ብለው በመምከርና በመወያየት ወደ ጥንተ ሰላምዋ እንድትመለስ የማድረግ ኀላፊነት አለባቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ከምትሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት በተጨማሪ በማኅበራዊው ዘርፍም ለሀገር እድገትና ለሕዝቦች ኑሮ መሻሻል፣ በተለይም ለሀገራዊ ሰላምና አንድነት በመቆም ድርሻዋን እንድትወጣ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ በላይ በተጠቀሱትና በሌሎችም ዐበይት ጉዳዮች ላይ ለ18 ቀናት ያህል በአገር ዐቀፍ ጉዳዮች በስፋትና በጥልቀት ሲወያይ ሰንብቶ ስብሰባውን በጸሎት አጠናቋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/007-3.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/logo-am.svg tc32019-06-10 09:30:302025-01-27 09:32:05ከግንቦት 14 ቀን እስከ ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ምርቃት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጡ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማስመልከት ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወኣምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመተ ምሕረት

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • April 2025
  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ግንቦት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ግንቦት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ግንቦት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ... Link to: ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ችግር አስመልክቶ ከሰኔ 21 እስከ ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ ለሁለት ሱባኤ ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ መታወጁን ቅዱስነታቸው በሐዋርያዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ Link to: ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ችግር አስመልክቶ ከሰኔ 21 እስከ ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ ለሁለት ሱባኤ ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ መታወጁን ቅዱስነታቸው በሐዋርያዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top