የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች

የቤተ ክርስቲያናችን ዓላማ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ማስተማርና መንፈሳዊ አገልግሎትን ለእግዚአብሔርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ማበርከት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ሳይዛባ፣ ሳይፋለስ፣ ፈሩን ሳይለቅ በነበረበት ለማስቀጠል የመንበረ ሐዋርያት ወራሾች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በዓመት ሁለት ጊዜ በቋሚነት እየተሰበሰቡ፣ ስለአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እየገመገሙ፣ እየመከሩና እየወሰኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እምነትዋንና ሥርዓቷን እንዲጠብቁ ቅዱሳን አበው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ደንግገዋል፡፡

በፌስቡክ ያግኙን

ሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓ.ም በአባቶች መካከል በተፈጠረው ልዩነት የተላለፈው ቃለ ውግዘት ተነሣ

ሐዋርያዊት፣ ጥንታዊትና ታሪካዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በረጅም የታሪክ ዘመኗ አንድነቷን ጠብቃ፤ የሀገሪቱንም አንድነትና ነፃነት በማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋፅ ስታደርግ ኑራለች፤ አሁንም ከማድረግ የተቈጠበችበት ጊዜ የለም፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ልኡካን ሽኝት ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም

ቤተ ክርስቲያን የሰላም ቤት ናት፣ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ምንጭ ናት፣ ቤተ ክርስቲያን የመለያየትና የመከፋፈል ምክንያት አይደለችም