https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/007-3.jpg
664
1000
tc3
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg
tc32015-11-02 08:28:262024-12-07 08:32:25ጥቅምት 12 ቀን እስከ 22 ቀን 2008 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች
የቤተ ክርስቲያናችን ዓላማ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ማስተማርና መንፈሳዊ አገልግሎትን ለእግዚአብሔርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ማበርከት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ሳይዛባ፣ ሳይፋለስ፣ ፈሩን ሳይለቅ በነበረበት ለማስቀጠል የመንበረ ሐዋርያት ወራሾች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በዓመት ሁለት ጊዜ በቋሚነት እየተሰበሰቡ፣ ስለአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እየገመገሙ፣ እየመከሩና እየወሰኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እምነትዋንና ሥርዓቷን እንዲጠብቁ ቅዱሳን አበው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ደንግገዋል፡፡
በፌስቡክ ያግኙን
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/007-3.jpg
664
1000
tc3
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg
tc32015-11-02 08:28:262024-12-07 08:32:25ጥቅምት 12 ቀን እስከ 22 ቀን 2008 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡
ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ
“ምንተ ይቤ መንፈስ ቅዱስ ለአብያተ ክርስቲያናት፤ መንፈስ ቅዱስ አብያተ ክርስቲያናትን አስመልክቶ ምን አለ?” (ራእ. 2፥7)፡፡

ሚያዝያ 27 ቀን እስከ 30 ቀን 2007 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡
“የሊቢያ ሰማዕታት”
ክርስቲያን በመሆናቸው በሊቢያ የተገደሉ 30 ኢትዮጵያውያን እና 21 የግብጽ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሰማዕታት በመባል በአንድነት እንዲታሰቡ ስለመወሰኑ፡፡

ሚያዝያ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ
‹‹ኀበ ሀለዉ ክልኤቱ ወሠለስቱ ጉቡኣን በስምየ አነ እሄሉ ማእከሌሆሙ ህየ -- ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እገኛለሁ።›› (ማቴ. 18÷20)

ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓ/ም፡ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት
"ዘሰ አምነኒ በቅድመ ሰብእ አነኒ አአምኖ በቅድመ አቡየ ዘበሰማያት
በሰው ፊት ያመነኝን ሰው እኔም በሰማያዊ አባቴ ፊት አምነዋለሁ።"
(ማቴ. 10፥32)

ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ አይኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በግፍ ስለተገደሉት ኢትዮጵያውያን በመስቀል አደባባይ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን አስተላልፈዋል፡፡
ይህ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን አሠቃቂ የወንጀል ድርጊት ከሰው ልጅ ተፈጥሮኣዊ ተግባር የወጣ ደረቅ ወንጀል ስለሆነ፣ ልንቃወምና ልንመክት የምንችለው በጥልቀትና በተረጋጋ መንፈስ በመሆን በመላው ዓለም ካሉ ከፀረ ሽብረ ግብረ ኀይላት ጋር በመተባበር ስለሆነ በትዕግሥትና በጥበብ የሰው ልጅ ሉዓላዊ ክብር እንዳይጣስ በነፃነት ሊኖርባት በተሰጠችው ምድር የሕይወት ዋስትና እንዲኖረው ለማስቻል ሁሉም ነቅቶና ተግቶ ኀላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡