• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ አይኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በግፍ ስለተገደሉት ኢትዮጵያውያን በመስቀል አደባባይ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን አስተላልፈዋል፡፡

April 22, 2015

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ/ም ራሱን አይ ኤስ በማለት የሚጠራው ሰብኣዊ ርኅራኄ የሌለው አሸባሪ ቡድን በወገኖቻችን ላይ ያደረሰውን አሠቃቂ የወንጀል ድርጊት ከሰማንበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ በአምላካችን ዘንድ የወገኖቻችን ደም በከንቱ እንዳይቀር ልብን በሚሰብር ኀዘን በጸሎት በማሰብ ላይ እንገኛለን፡፡ ይህ በሰብኣዊ ፍጡር ይፈጸማል ተብሎ የማይታሰብ ድርጊት አሳሳቢና ፍጹም ጭካኔ የተመላው በመሆኑ ከኀዘናችንና ሰማዕታቱን በጸሎት ከማሰብ በተጨማሪ ወጣቶቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች መሆናቸውን ስለተረዳን ስለጌታችን ስምና ስለቀናች ሃይማኖት፣ ስለ እግዚአብሔርም ፍቅር ዐላውያን በቅጣት የሚያሠቃዩትን ክርስቲያናዊ ቸል አትበሉ ተብሎ በዲድስቅልያ በተደነገገው ቀኖና መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በተደጋጋሚ ልዩ ልዩ መግለጫዎች በማውጣት፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልታደርግ የሚገባትን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ሥርዐት በማከናወን ላይ ትገኛለች፡፡

በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው የሁሉም ሃይማኖቶች ተልእኮ ሰውን ማዳን እንጂ ሰውን መግደል እንዳይደለ ቢታመንም ንጹሓን ዜጎችን በሃይማኖት ምክንያት በአሠቃቂ ግድያ የመግደል ወንጀል በዓለማችን መታየት ከጀመረ ሰነባብቶአል፡፡ ኢትዮያውያን ወገኖቻችንም በተለያየ ጊዜና በተለያየ አካባቢ የዚህ ዐይነቱ ግድያ ሰለባ መሆናቸው አልቀረም፡፡ ከዚህ አንጻር በዚህ ሰሙን በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች በሆኑት ልጆቻችን ላይ የተፈጸመው አሠቃቂ ግድያ ከምንም ጊዜ በላይ ቤተ ክርስቲያናችንን፣ ሀገራችንንና ሕዝባችንን ያሳዘነና ያሳሰበ ጉዳይ ሆኖ ተገኝቶአል፡፡

የተፈጸመው አሠቃቂ ድርጊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የዓለም ሃይማኖቶች ላይ የተቃጣ የወንጀል ተግባር መሆኑን በማመን መላው የሀገራችን ሕዝቦችና የሃይማኖት ተቅዋማት እንደዚሁም መላው የዓለም መንግሥታት ይህን ድርጊት በጽኑ መቃወምና ማውገዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም የተፈጸመውን ድርጊት ፈጽሞ ታወግዛለች ከመንግሥትና ከሕዝብ ጋር ተሰልፋም የሚጠበቅባትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ታረጋግጣለች፡፡

ቀደም ሲል በመግለጫችን እንደተነገረው የአሸባሪዎች የጥፋት ዕልቂት ሃይማኖትን፣ ቀለምን፣ ጾታንና አካባቢን ሳይለይ በአጠቃላይ በሰው ዘር ላይ የዘመተ የጥፋት ተልእኮ ስለሆነ ሁሉም የሃይማኖት መሪዎችና የፀረ ሽብር ተቅዋማት ለዓለማችን ሰላም መረጋገጥና ለሰው ልጆች በሕይወት የመኖር መብት መከበር ተባብረው እንዲሠሩ ቤተ ክርስቲያናችን በአጽንዖት ትጠይቃለች፤

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም ዐቀፍ ማኅበረ ሰብና ከየሀገሩ መንግሥታት ጋር በመሆን የሚያካሂደውን የፀረ ሽብር እንቅስቃሴ አጠናክሮ በመቀጠል የዜጎቻችን ሕይወት በአሸባሪዎች እንዳይቀጠፍ ከእስከ አሁኑ በበለጠ እንዲንቀሳቀስ፤ ሕዝቡም ከአሁን በፊት በበጎ ታሪካችን እንደሚታወቀው በሃይማኖትና በሌላው ሁሉ ሳንለያይ ጠብቀን ያቆየነውን በአንድነት፣ በፍቅርና በመቻቻል የመኖር ዕሴት አሁንም አጥብቀን በመያዝ የጋራ ጠላት የሆነውን ግብረ ሽብር በመመከት ራሱንና ሀገሩን ከአሸባሪዎች ነቅቶ እንዲጠብቅ ቤተ ክርስቲያናችን ታሳስባለች፤

የሟዋች ቤተሰቦች የሆናችሁ ወገኖቻችን ሁሉ በዚህ ግፍ የተሞላበት ጭካኔ የተገደሉት ልጆቻችን በዚህ ዓለም የመኖር ተስፋቸው ባጭሩ ቢቀጭም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተገፉ መንግሥተ ሰማያትን ይናጠቋታል ማለትም ይወርሱአታል ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት እግዚብሔር ዕንባቸውን አብሶ በመንግሥቱ የሚቀበላቸው መሆኑን ዐውቃችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንም ለሰማዕታቱ የአንድ ሳምንት የጸሎተ ፍትሐት ያወጀች መሆኑንና ሰማዕታቱን በሚገባቸው ክብር ለማክበር የሚገባትን ሥርዐት የምታከናውን መሆኑን ተረድታችሁ ልትጽናኑ ይገባችኋል፡፡

ከዚሁ ጋር ለማሳሰብ የምንወደው ጉዳይ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር ከመውጣት፣ አስተማማኝ የሕይወትና የንብረት ዋስትና ወደሌለበት ሀገር ከመሄድ ተቈጥቦ በሀገሩ ሠርቶ ኑሮውን እንዲመራ ቤተ ክርስቲያን የምትመክር መሆኑን እናስገነዝባለን፤

ክቡራንና ክቡራት፡ የተወደዳችሁ የሀገራችን ሕዝቦች
ሞትን ለመጀመሪያ ጊዜ የቀመሰው አቤል የተገደለው በወንድሙ በቃየል እጅ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ግን በዐመፅና በክፋት ተመልቶ ወንድሙን አቤልን የገደለ ቃየልን ከነጥፋቱ እንዲሠወር አልፈቀደም፡፡ ይልቁንም ገዳዩን “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? አቤል ምን አደረገህ?” የወንድምህ የአቤል የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮሃልና ብሎ ጠይቆታል፡፡ (ዘፍ 4፥10)

ስለዚህ ዛሬም በግፍና በጭካኔ የተመሉ አሸባሪዎች ከፈጣሪን ጥያቄና ፍርድ ፈጽመው እንደማያመልጡ እናምናለን፡፡ ምክንያቱም ፈጣሪ የወንድሙን ደም ያፈሰሰውን ቃየልን የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ፣ በምድር ላይ ኮብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ በማለት በቃየል ላይ ፈርዷልና ነው፡፡ ይህ አምላካዊ ፍርድ ዛሬም ወንድሞቻቸው የሚሆኑ የንጹሓን ወጣቶችን ሕይወት ያለርኀራኄ የቀጠፉ አሸባሪዎች ከዚህ ሰማያዊና ምድራዊ ፍርድ እንደማያመልጡ እምነታችን የጸና ነው፡፡ ስለዚህ እኛም በዛሬው ዕለት በወገኖቻችን የደረሰውን አሠቃቂ ወንጀል ልባችንን ስለነካው አቤል ወዴት አለ ብሎ የተገደለውን እንደፈለገው ፈጣሪ ወንድሞቻችን ወዴት አሉ ብለነን ሁላችንም ከመኖሪያ ቤታችን ከሥራችን ወጥተን ይህንን አሠቃቂ የወንጀል ድርጊት ለመቃወምና ለማውገዝ ወደ አደባባይ መውጣታችን ሰውን በሚወድ በፈጣሪ ፊት የሚያስመሰግን ነው፡፡

ክቡራንና ክቡራት፥ የተወደዳችሁ የሀገራችን ሕዝቦች
ይህ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን አሠቃቂ የወንጀል ድርጊት ከሰው ልጅ ተፈጥሮኣዊ ተግባር የወጣ ደረቅ ወንጀል ስለሆነ፣ ልንቃወምና ልንመክት የምንችለው በጥልቀትና በተረጋጋ መንፈስ በመሆን በመላው ዓለም ካሉ ከፀረ ሽብረ ግብረ ኀይላት ጋር በመተባበር ስለሆነ በትዕግሥትና በጥበብ የሰው ልጅ ሉዓላዊ ክብር እንዳይጣስ በነፃነት ሊኖርባት በተሰጠችው ምድር የሕይወት ዋስትና እንዲኖረው ለማስቻል ሁሉም ነቅቶና ተግቶ ኀላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚብሔር እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/007-3.jpg 664 1000 tc https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc2015-04-22 16:51:452024-12-04 16:54:00ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ አይኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በግፍ ስለተገደሉት ኢትዮጵያውያን በመስቀል አደባባይ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን አስተላልፈዋል፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ በሰማዕትነት ስለተሠዉ ኢትዮጵያውያን የቅዱስነታቸው መግለጫ Link to: ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ በሰማዕትነት ስለተሠዉ ኢትዮጵያውያን የቅዱስነታቸው መግለጫ ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ በሰማዕትነት ስለተሠዉ... Link to: ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓ/ም፡ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት Link to: ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓ/ም፡ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓ/ም፡ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top