• Amharic  
  • English  
  • ቀዳሚ ገጽ
  • የኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
    • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • ልዩ ጽ/ቤት
    • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት
    • የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች
    • የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
    • የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጒዞ
  • ቃለ በረከት
  • ዜና መዋእል
  • አርዕስተ ሊቃነ ጳጳሳት
  • ያግኙን
  • Menu Menu

ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ችግር አስመልክቶ ከሰኔ 21 እስከ ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ ለሁለት ሱባኤ ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ መታወጁን ቅዱስነታቸው በሐዋርያዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤
በሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ እየታየ ያለውን ወቅታዊ የሰላም ዕጦት አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘመናት ውስጥ በዓለም የምትታወቅበት የነበረ ሀብቷ ሰላም አንድነትና አብሮነት ሆኖ ሕዝቧ በፈሪሀ እግዚአብሔርና በበጎ ሥነ-ምግባር የሚታወቅ አገሪቱ የአየር ንብረቷ ለዜጎቿ ቀርቶ በውጭው ዓለም የሚገኙ ሁሉ የሚናፍቁት የሰው ልጅ መኖሪያና ምድረ-ገነት መሆኗን ዓለም የሚገነዘበው ሐቅ ነው፡፡ በእነዚህ በርካታ ዘመናትም በአገሪቱ ውስጥ በመሪና በተመሪ በአጠቃላይ በዜጎች መካከል የነበረው የመከባበር እርስ-በርስ የመግባባትና የመፈቃቀር ሁኔታ አልፎ አልፎ ዕንቅፋት ቢያጋጥመውም የቀደሙ አባቶቻችን የነበራቸው የችግር አፈታትና ወደ አንድነት ለመመለስ ያደርጉት የነበረ ጥረትና ተቀባይነቱም በእጅጉ የሚያስመሰግን እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ግን በአገራችን እየታየ ያለው ችግርና አለመግባባት ከእርስ በርስ ግጭትና ከውይይት አለመግባባት አልፎ እስከ ሕይወት መጠፋፋት መድረሱ የአገራችንንና የዜጎቿን የዘመናት አኵሪ ታሪክና ምሳሌነት እንዳልነበር ያደረገው መሆኑ መላውን ዜጎችም በሀገራዊው ሰላም ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው ያደረገ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ይኸው ሀገራዊ ችግር አስመልክቶ የግንቦት ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሰፊው ተነጋግሮ ችግሩ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ እንዳይደርስ ማድረግ እንዲቻል ችግር ባለባቸው የአገራችን ክልሎች ሁሉ ዕርቀ ሰላም ማውረድ በቀጣይም ችግር እንዳይፈጠር መከላከል እንዲቻል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ የሰላምና የአንድነት ኮሚቴ መሰየሙና ለዚሁ የሰላም ተልእኮ ማስፈጸሚያ በጀት መመደቡና የሰላም ኮሚቴውም ወደ ሥራ ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

ሆኖም በአገራችን እንደ ችንሽ ነገር እየተቈጠረ የተጀመረው አለመግባባት በየክልሉ ለብዙዎች ዜጎቻችንና ሕይወት መጥፋትና ከቄያቸው መፈናቀል ለረኃብና ለስደት መዳረግ ምክንያት መሆኑ ከዚያም አልፎ ተርፎ የአገርን ህልውና አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ እስከ ሕይወት መጠፋፋት መድረሱ ከወዲሁ በአጭሩ እስከአልተቋጨ ድረስ በቀጣይ ምን ሊመጣ እንደሚችል መገመቱ ቀላል አይሆንም፡፡

ስለዚህ የሀገራችን ዜጐች ሁሉ ስለዚህች እናት ሀገራችን ስትሉ ትናንት የነበረውን የመከባበርና የአንድነት ባህላችሁን አጥብቃችሁ በመያዝ ለነገ ትልቅ ተስፋ ያላት አገራችን እንደምኞታችንና ሐሳባችን ካሰብነው ደርሳ ልማቷ አድጎ፥ አንድነቷ ተጠብቆ ሕፃናት የሚያድጉበት፣ ሽማግሌዎች የሚጦሩበት፣ የሁሉ ተስፋ የሆነች አገር እንድትኖረን ለማድረግ ሁላችሁም የዜግነታችሁን እንድታበረክቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ከዚህም ጋር የሰላም አምላክ ሰላም ገንዘቡ የሆነ እግዚአብሔር ጸሎታችንና ልመናችንን ሰምቶ መዓቱን በምሕረት ቍጣውን በትዕግሥት እንዲመልስልን በአገራችንም ሆነ በውጭው ዓለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር በሚገኙ ገዳማትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ከዛሬ ሰኔ 21 እስከ ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ ሁለት ሱባኤ ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ አውጇል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/007-3.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/logo-am.svg tc32019-07-11 09:34:022025-01-27 09:35:47ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ችግር አስመልክቶ ከሰኔ 21 እስከ ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ ለሁለት ሱባኤ ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ መታወጁን ቅዱስነታቸው በሐዋርያዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ምርቃት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጡ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማስመልከት ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወኣምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመተ ምሕረት

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • April 2025
  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ከግንቦት 14 ቀን እስከ ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡ Link to: ከግንቦት 14 ቀን እስከ ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡ ከግንቦት 14 ቀን እስከ ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የተካሄደው... Link to: ጳጒሜን 2 ቀን 2011 ዓ.ም.የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ለመክፈት ባዘጋጀው ቡድናዊ አሠራር መሠረት አሽቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ጠርቶ ለሦስት ቀናት ዝግ ጉባኤ አድርጎ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ Link to: ጳጒሜን 2 ቀን 2011 ዓ.ም.የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ለመክፈት ባዘጋጀው ቡድናዊ አሠራር መሠረት አሽቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ጠርቶ ለሦስት ቀናት ዝግ ጉባኤ አድርጎ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ ጳጒሜን 2 ቀን 2011 ዓ.ም.የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top