• Amharic  
  • English  
  • ቀዳሚ ገጽ
  • የኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
    • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • ልዩ ጽ/ቤት
    • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት
    • የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች
    • የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
    • የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጒዞ
  • ቃለ በረከት
  • ዜና መዋእል
  • አርዕስተ ሊቃነ ጳጳሳት
  • ያግኙን
  • Menu Menu

ሚያዝያ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በንጹሓን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሠቃቂ ግፍ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤
“ወይቤ እግዚአብሔር ንግበር ሰብአ በአርኣያከ ወበአምሳሊከ — እግዚአብሔርም አለ ሰውን በአርኣያችንና በአምሳላችን እንፍጠር” (ዘፍ.1፥26)፤ ፈጣሬ ፍጥረታት እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር በሦስት ነገሮች ከሌሎች ፍጥረታት የተለየ አድርጎ ፈጥሮታል፤ ይኸውም እንደሌሎች ፍጥረታት ይሁን በማለት በቃል – ትእዛዝ ሳይሆን ከምድር አፈር አበጅቶ ፈጥሮታል፣ ይህም ማለትም፡ በእጁ አከናውኖ፣ አሳምሮና አክብሮ የፈጠረው በመሆኑ፤ ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ ሁናቴ በአርኣያውና በአምሳሉ የፈጠረው በመሆኑ፣ ከፍጥረታት ሁሉ ለይቶ የሕይወት እስትንፋስን እፍ ያለበት ሕያው ፍጡር በመሆኑ ከሌሎች ፍጥረታት የተለየ ያደርገዋል፡፡
በኀላፊነት ደረጃም ምድርንና በምድር ያሉትን ፍጥረታት ሁሉ እንዲያስተዳድር፣ እንዲያዝና እንዲገዛ ባለሙሉ ሥልጣን ሆኖ በእግዚአብሔር ተሹሞአል፡፡

ይህ ሁሉ የሚያመለክተው ሰው በፈጣሪ ዘንድ እጅግ በጣም የተከበረና የተወደደ ፍጡር ከመሆኑም በላይ አርኣያ እግዚአብሔር፣ አምሳለ እግዚአብሔር የሆነ ክቡር ፍጥረት መሆኑን ነው፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ክብር ታላቅነት በሚያስተምርበት ጊዜ ‹‹በወንድሙ ላይ በማይገባ የሚቈጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል›› ብሎአል፤ (ማቴ.5፡21-22) ጌታችን በዚህ ትምህርቱ የሰው ልጅን መግደል ይቅርና መሳደብና መቈጣት እንደማይቻል አበክሮ አስተምሮአል፤ ሰውን መግደል አርኣያ እግዚአብሔርን፣ አምሳለ እግዚአብሔርን ማፍረስ ስለሆነ በፈጣሪ ዘንድ ትልቅ በደል ነው፡፡

ከዚህ አንጻር በእግዚአብሔር የተሰጠውን የሰው ክብር በተግባር ለመጠበቅና ለማስከበር፣ በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ ያሉትን ልጆቿን በእኩልነትና በአንድነት አስተባብራ ለዘመናት ተጭኖን የቆየውን ድህነት ለመቀነስ ብሎም ለማስቆም ከዳር እስከ ዳር እየተጋች ያለችና ብሩህ ተስፋ የሠነቀች ሀገር እንደሆነች ዓለም የተገነዘበበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ ይሁን እንጂ አልፎ አልፎ በሰው ልጆች ሕይወት ላይ እየተከሠቱ ያሉት ግድያዎች የሰውን ክቡርነት በግልጽ የሚጋፉ ናቸው፤ በመሆኑም የግድያ ድርጊት፣ ለዚያም ዐቅም በሌላቸውና መከላከል በማይችሉ ሕፃናትና እናቶች የሚፈጸሙትን ግድያዎች፣ ሁሉም አምርሮ ሊያወግዛቸውና ሊመክታቸው ይገባል፤ በተለይም በዚህ ሰሙን በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በንጹሓን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ግድያ፣ ዘረፋና የንብረት ውድመት ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ አሳዝኖአል፡፡ ይህን ግድያ ልዩ የሚያደርገው በተለይ በሕፃናትና እናቶች ላይ ያነጣጠረ በመሆኑ ነው፣ ይህ ኅሊናን የሚያቈስልና ሕገ እግዚአብሔርን የሚጥስ የጭካኔ ተግባር በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን አጥብቃ ታወግዘዋለች፡፡

ሀገራችንም ሆነች የዓለም ማኅበረ ሰብ በአጠቃላይ የሰው ልጅ በሕይወትና፣ በነፃነት የመኖር ዋስትና ኖሮት፣ በሀገሩ ሠርቶ የመሻሻል መብቱ እንዲከበር ተግተው በሚሠሩበት ወቅት እንዲህ ያለ ድርጊት መፈጸሙ ሀገራችንን ወደኋላ የሚጎትት ስለሆነ እንዲህ ያለው ድርጊት ድጋሚ እንዳይከሠት ተገቢውን ጥንቃቄ ከማድረግ ጋር አስተማሪ የሆነ ሥራ ሊሠራ ይገባል፡፡ አሁን የተከሠተው ዐይነት ችግር፣ ይብዛም ይነስም በጋምቤላ አካባቢ በተደጋጋሚ እየታየ የቆየ ከመሆኑ አንጻር ችግሩ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያከትም ለማድረግ የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን መንግሥታት በጋራ ቢሠሩ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ቤተ ክርስቲያናችን ታምናለች፤ ለዚህም ድጋፏን ትሰጣለች፡፡

በመጨረሻም፡ በጋምቤላ ክልል በሚገኙት ልጆቻችንና ወገኖቻችን በተፈጸመው የግድያ፣ የዘረፋና የንብረት ውድመት ምክንያት የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን በራሳችንና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም እየገለጽን የመዋች ቤተሰቦችንና የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትን እግዚአብሔር እንዲያጽናናቸው እንጸልያለን። በዚህ አጋጣሚ ቤተ ክርስቲያናችን አሁንም ሆነ ወደፊት ከክልሉ ሕዝብና መንግሥት ጎን እንደማትለይ እናረጋግጣለን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/007-3.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/logo-am.svg tc32016-04-20 08:43:182024-12-07 08:45:32ሚያዝያ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በንጹሓን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሠቃቂ ግፍ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ምርቃት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጡ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማስመልከት ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወኣምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመተ ምሕረት

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • April 2025
  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የካቲት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ቀናት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ Link to: የካቲት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ቀናት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ የካቲት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ... Link to: ሚያዝያ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ሚያዝያ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሚያዝያ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓል ቃለ ምዕዳንና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top