• Amharic  
  • English  
  • ቀዳሚ ገጽ
  • የኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
    • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • ልዩ ጽ/ቤት
    • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት
    • የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች
    • የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
    • የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጒዞ
  • ቃለ በረከት
  • ዜና መዋእል
  • አርዕስተ ሊቃነ ጳጳሳት
  • ያግኙን
  • Menu Menu

33ኛው ዓመታዊ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከጥቅምት 5-8 ቀን 2007 ዓ/ም አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡

“እንኳን ወደዚህ ታላቅ ጉባኤ መጣችሁ፣ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ” በማለት ቅዱስነታቸው ስብከተ ወንጌልን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት “ይህ ዓመት ስብከተ ወንጌል ይበልጥ የምናስፋፋበት፣ የምእመናን ብዛት የምንጨምርበት፣ ሰላምን ፍቅርን የምናጠናክርበት መሆን አለበት፡፡ ይህን ለማድረግ መልካም አስተዳደር ማስፈንና የቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብት በትክክል ሥራ ላይ ማዋል ስንችል በመሆኑ ሁላችንም ለተግባራዊነቱ መትጋት አለብን ብለዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በዚህ የጉባኤው መክፈቻ ንግግራቸው ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማስቀረት በሚደረገው ሀገር ዐቀፍ ጥረት ቤተ ክርስቲያን ምእመናኖቿን በማስተማር ድርሻዋን መወጣት እንዳለባትና በሌላ በኩል በአሁኑ ጊዜ የዓለም ሥጋት በተለይ ደግሞ የአፍሪቃውያን ችግር እየሆነ ያለው የኢቦላ በሽታ ወደ ሀገራችን እንዳይገባ በመላ ሀገራችን የምሕላ ጸሎት እንዲደረግና መንግሥት እያደረገ ባለው የመከላከል ሥራ ሕዝቡ የድርሻውን እንዲወጣ ምእምናን ማስተማር እንደሚገባ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡

ቅዱስነታቸው በዚህ አባታዊ መመሪያቸው ለጉባኤው ተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልእክት “ለቤተ ክርስቲያን ያላችኋት ሀብቶች እናንተ ናችሁ፣ በዚህ ዓመት ወጥታችሁ ወርዳችሁ በሠራችሁት ሥራ ባስመዘገባችሁት የገቢ እድገት ልትመሰገኑ ይገባል፣ ለወደፊቱም ጥረታችሁን አጠናክራችሁ መቀጠል አለባችሁ፡፡ ከዚህ ጋር የምእምናን እንደ ጥንቱ ቤተ ክርስቲያናቸውን እና እምነታቸውን አጠንክረው እንዲይዙ በስብከተ ወንጌል መጠናከርና መስፋፋት ላይ የበለጠ ልንሠራ ይገባል” ብለዋል፡፡ ‹‹መልካም አስተዳደር ምን ጊዜም ከኅሊናችን መጥፋት የለበትም ያሉት ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን በመቀጠል ሥራችን በኀላፊነት፣ በተጠያቂነት፣ በንጽሕናና በቅድስና መሥራት አለብን›› በማለት መልእክታቸውን ቋጭተዋል፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/001-2-1000.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/logo-am.svg tc32014-10-18 14:41:032025-01-28 14:42:3733ኛው ዓመታዊ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከጥቅምት 5-8 ቀን 2007 ዓ/ም አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ምርቃት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጡ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማስመልከት ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወኣምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመተ ምሕረት

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • April 2025
  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: መስከረም 16 ቀን የ2007 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: መስከረም 16 ቀን የ2007 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ መስከረም 16 ቀን የ2007 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል... Link to: ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top