• Amharic  
  • English  
  • ቀዳሚ ገጽ
  • የኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
    • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • ልዩ ጽ/ቤት
    • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት
    • የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች
    • የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
    • የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጒዞ
  • ቃለ በረከት
  • ዜና መዋእል
  • አርዕስተ ሊቃነ ጳጳሳት
  • ያግኙን
  • Menu Menu

የካቲት 5 ቀን 2010 ዓ.ም የዐቢይ ጾም መግቢያ ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ወምእመናት በሙሉ፣ መሐሪና ይቅር ባይ የሆነው እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥር ዓመተ ምሕረት የጾመ ኢየሱስ ሱባዔ በሰላም አደረሳችሁ!!

ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምሕላ
ጾምን ለዩ ምሕላንም አውጁ፣
(ኢዩ. 2፥15)

ሁሉን ያስገኘ ሁሉንም ባርኮ ለፍጥረቱ ያደለ፣ የምሕረትና የበረከት አምላክ እግዚአብሔር፣ ለፍጥረቱ ምግብ የሚሆን ፍሬ በረከትን በየዐይነቱ በምልአት እንደሰጠ ዓይናችን ያያል፣ እጃችን ይዳስሳል፣ ኅሊናችንም ያውቃል፡፡ እግዚአብሔር ተንቀሳቃሽ የሆኑትን ሕያዋን ፍጥረታት ወደ ህልውና ከማምጣቱ በፊት ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ በገጸ ምድር፣ በከርሠ ምድር፣ በዐውደ ምድርና በጠፈረ ሰማይ አስቀድሞ ፈጥሮአል ፤ እግዚአብሔር ሕያዋን ፍጥረታትን በምድር ላይ ከፈጠረ በኋላ ለፍጥረታቱ እነሆ ይህንን ሁሉ ሰጥቻችኋለሁ ፣ ብሉ፣ ብሎ ባርኮ ሰጥቶአቸዋል፣ ከዚህም ጋር መጥኖ መመገብ፣ የሚጠቅመውንና የማይጠቅመውን ለይቶ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አሳውቆአል፡፡

ይሁን እንጂ ፍጡራን በተለይም ሰዎች ይህንን ትእዛዘ እግዚአብሔር ባለመጠበቃቸው ለውድቀት መዳረጋቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ እግር የተፈጠረው ለመራመድ ነው ተብሎ በገደልና በባሕር በእግር መራመድ እንደማይቻል ሁሉ ሆድ የተፈጠረው ለመብላት ነው ብሎ ሁሉን፣ አግበስብሶ መብላት ከጥቅሙ ይልቅ ጒዳቱ እንደሚበልጥ በስካር፣ በአደንዛዥ ዕፅ፣ በመቃምና በማጤስ በተሸነፉ ወገኖች የሚታየው የሕይወት ምስቅልቅልና የኢኮኖሚ መቃወስ አፍ አውጥቶ የሚመሰክር ማስረጃ ነው፤ ሰው ይቅርና እንስሳት እንኳ ከመጠን በላይ ከተመገቡ ብዙ ጒዳት ይደርስባቸዋል፤ በሌላም ላይ ያልተጠበቀ ጕዳት ያደርሳሉ፤ በመሆኑም ሰዎች ከጕዳት፣ ከስሕተትና ከውድቀት ይድኑ ዘንድ የማይጠቅመውን መተው፣ የሚጠቅመውንም መጥኖ መመገብ አስፈላጊ መሆኑ ከማንም የተሠወረ አይደለም፣ ለዚህም ተመራጩ ዘዴ ጾምን መጾም እንደሆነ በተግባር የሚታይ ነው፤ መጥኖ መመገብ ሰውን ወደ ትዕግሥት፣ ወደ ማስተዋል፣ ወደ ዕለታዊ የግል ተግባር፣ ወደ መቻቻል፣ ወደ ርኅራኄ፣ ወደ ሰላምና ወደ ፍቅር፣ ፈጣሪንና ሕጉን ወደማሰብ ይገፋፋል፣ ሰው መጥኖ በተመገበና በጠጣ ቊጥር በብዙ መልኩ ከግብረ ኀጢአት ባርነት ነፃ የመውጣት ዕድሉ ሰፊ ነው፣ በተጨማሪም መንፈሳዊ፣ ሞራላዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኀይልን ከፍ የማድረጉ ጉዳይ፣ እንደዚሁም ጤንነቱን ከበሽታ የመከላከል ዐቅም ከፍ እንደሚል የጤና ባለሙያዎች ይመሰክራሉ፤ ስለሆነም ጾም ከሃይማኖታዊ ጥቅሙ ባሻገር ለሰው ልጅ የተሟላ ጤንነት ያለው ጠቀሜታ ከፍ ያለ እንደሆነ እናስተ ውላለን፡፡

ጌታችንም በመዋዕለ ጾሙ ያስተማረን ይኸው ነው፤ እሱ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጹሞ በተራበ ጊዜ ፈታኙ ጠላት በተለመደ መሣሪያው በምግብ በማስጎምጀት ሊፈትነው ሲሞክር ከፍ ባለ ሞራላዊና መንፈሳዊ አቋም ሰው በእግዚአብሔር ቃል እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ብሎ ሐሳቡን ውድቅ በማድረግ አሳፍሮ መልሶታል፡፡ ጌታችን በዚህ አምላካዊ ትምህርቱ ዲያብሎስንና የጥፋት መሠሪያዎቹን ሁሉ መመከት የሚቻለው በምግብ ኀይል ሳይሆን በጾም ኀይል መሆኑን በተግባርም በትምህርትም አሳይቶናል፡፡ ከዚህም የተነሣ ክርስቶሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችን ከክርስቶስ ባገኘችው ትምህርት የጾም ወቅቶችን ለይታ ጸሎተ ምሕላን በማድረስ፣ መጥኖ በመመገብ፣ ለግብረ ኀጢአት የሚያነሣሡና ወደጥፋት የሚገፋፉ ምግቦችን በመተው፣ ጾምን፣ ጸሎትን፣ ምህላን፣ ምፅዋትን፣ ምሕረትን፣ ይቅርታን፣ ለእግዚአብሔር መታዘዝን፣ መደበኛ ተግባር አድርጋ ሰባቱን አጽዋማት በየዓመቱ ትጾማለች፤ በዚህም ወደፈጣሪዋ ወደ እግዚአብሔር በምታቀርበው ጸሎት፣ አምልኮና ስግደት የእግዚአብሔር በረከትና ጥበቃ እየታደጋት በአንድነትዋ፣ በነፃነትዋና በገናናነትዋ ጸንታ ለሦስት ሺሕ ዘመናት ዘልቃለች ፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፡ ወርኀ ጾም መንፈሳዊ ኀይላችንን የምናጎለብትበት፣ የፈቃደ ሥጋ ውጤቶች የሆኑ ጥልን፣ መለያየትን፣ የርስ በርስ መጠራጠርን የምናደክምበት፣ብሎም መንግለን የምንጥልበት፣ በአንጻሩም የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች የሆኑ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ ይቅር ይቅር መባባልን፣ አርቆ ማየትን የምንለማመድበት፣ ስለጥቃቅን ጊዜያዊ ችግሮች ሳይሆን፣ ስለሃይማኖትና ስለሀገራዊ ዘላቂ ጥቅሞች አብዝተን የምናስብበትና መፍትሔ የምናበጅበት ጊዜ ነው፤ እንደሚታወቀው በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችን አንድነት ፈተና፣ ለሕዝባችን ልማትና ብልጽግና እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ግጭቶች በተደጋጋሚ እየተከሠቱ ብዙ ወገኖች ሀብታቸው፣ ንብረታቸው ከሁሉ በላይ ደግሞ መተኪያ የሌለው ሕይወታቸው ጕዳት እየደረሰበት ነው፤ እንደዚህ ያለው ድርጊት የክርስቶስ ወንጌለ ሰላም ለሁለት ሺሕ ዘመናት ያለመቋረጥ በተሰበከባት በኢትዮጵያ ምድር መከሠቱ ከሃይማኖታችን ዕድሜ ጠገብ ጸጋ ጋር የማይሄድ ነው፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ አሳዛኝ ድርጊቱ እየተፈጸመ ያለ በራስ ወገን ላይ መሆኑ እጅግ የሚያሳፍር ነው፡፡ እየጎዳም ያለው ራሳችንን ነው፤ የሚወድመው ንብረትም፣ የሚጠፋው ሕይወትም የእኛው የራሳችን ነው፡፡ እነዚህ ጎጂ ድርጊቶች በፍጥነት ካላረምናቸው ባለፉት የሰላምና የልማት ዓመታት የታዩት ተስፋዎች እንደገና እንዲጨልሙና የኋልዮሽ እንድንጓዝ የሚያደርጉን አደገኛ አዝማሚያዎች ናቸው፣ በመሆኑም መላው ሕዝባችን በተለይም ወጣት ልጆቻችን በዚህ ቅዱስ ወርኀ ጾም ወደ ልባችሁ መለስ በሉና ነገሮችን በአርቆ አስተዋይነትና አእምሮን በማስፋት ተመልከቷቸው፣ እየተከሠቱ ያሉ ስሕተቶች የምንወዳት ኢትዮጵያን ይጎዱ እንደሆነ እንጂ በምንም ተአምር አይጠቅሟትም፤ ስለሆነም የችግሩን ጕዳት በማገናዘብ በየአካባቢው ያላችሁ የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በአጠቃላይ፣ ሕዝባችን ተደጋጋሚ ስሕተቶችን በመፈጸም ወገንንና ሀገርን እንዳይጎዳ በዚህ ቅዱስ የጾም ወቅት የሰላም አጀንዳን ዕለታዊ ሥራ አድርጋችሁ ወጣቱን ትውልድና ሕዝቡን እንድትመክሩ፣ እንድታስተምሩ ቤተ ክርስቲያናችን በእግዚአብሔር ስም ጥሪዋንታስተ ላልፋለች፡፡

በመጨረሻም፤ መላ ኢትዮጵያውያን በተለይም ሕዝበ ክርስቲያኑ ይህ ጾም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ወይም የተለየ ጊዜ እንደመሆኑ መጠን የተራበውን በማጉረስ፣የተራቆተውን በማልበስ፣ የተጠማውን በማረስረስ፣ በኅብረተሰቡ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ መቻቻልንና ይቅር ይቅር መባባልን በማንገሥ፣ጾሙን ልዩ የይቅርታ ጊዜ አድርገን እንድንቀበለውና እንድንጾመው፣ ካህናቱም ስለ ሀገር አንድነትና ስለሕዝብ ሰላም እያሰባችሁ በየቤ ተክርስቲያኑ ጸሎቱንና ምህላውን በኃዘን ወደ እግዚአብሔር እንድታቀርቡ አባታዊ መልእክ ታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር የይቅርታ ጾም ያድርግልን የኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ያጽናልን ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/001-2-1000.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/logo-am.svg tc32018-02-12 13:35:062025-01-28 13:36:11የካቲት 5 ቀን 2010 ዓ.ም የዐቢይ ጾም መግቢያ ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ምርቃት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጡ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማስመልከት ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወኣምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመተ ምሕረት

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • April 2025
  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ጥር 11 ቀን 2010 ዓ.ም የጥምቀት በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ጥር 11 ቀን 2010 ዓ.ም የጥምቀት በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ጥር 11 ቀን 2010 ዓ.ም የጥምቀት በዓል ቃለ ምዕዳንና... Link to: መጋቢት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓል ሙሉ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: መጋቢት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓል ሙሉ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ መጋቢት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓል ሙሉ ቃለ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top