የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች

የቤተ ክርስቲያናችን ዓላማ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ማስተማርና መንፈሳዊ አገልግሎትን ለእግዚአብሔርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ማበርከት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ሳይዛባ፣ ሳይፋለስ፣ ፈሩን ሳይለቅ በነበረበት ለማስቀጠል የመንበረ ሐዋርያት ወራሾች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በዓመት ሁለት ጊዜ በቋሚነት እየተሰበሰቡ፣ ስለአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እየገመገሙ፣ እየመከሩና እየወሰኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እምነትዋንና ሥርዓቷን እንዲጠብቁ ቅዱሳን አበው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ደንግገዋል፡፡

በፌስቡክ ያግኙን

ከጥቅምት 11 ቀን እስከ 25 ቀን 2015 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቍጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልአተ ጉባኤው የመክፈቻውን ሥርዓተ ጸሎት ከፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2015ዓ.ም. ጀምሮ የተለመደውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡ ምልአተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ እድገት ለሀገራችን ማኅበራዊና ልማታዊ ክንውን እንዲሁም ለመላው ሕዝባችን ሰላምና አንድነት ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡

ጥቅምት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

“ወሑሩ ባሕቱ ኀበ አባግዕ ዘተኀጒላ እምቤተ እስራኤል ነገር ግን ከቤተ እስራኤል ወገን ወደ ጠቦት በጎች ሂዱ” ማቴ. 0፥6፡፡

ከግንቦት 10 ቀን እስከ ግንቦት 25 ቀን 2014 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቊጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልአተ ጉባኤው የመክፈቻው ሥርዐተ ጸሎት ከተፈጸመበት ግንቦት 9 ቀን 2014ዓ.ም. ጀምሮ የተለመደውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ሲያካሂድ ሰንብቶ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሚበጁ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

“ወሩጹ ኀበ ሰላም ምስለ ኵሉ -- ከሁሉ ጋር ወደ ሰላም ሩጡ።” (ዕብ. 12፥14)

ከጥቅምት 11 ቀን እስከ 18 ቀን 2014 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቍጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልአተ ጉባኤው የመክፈቻው ሥርዐተ ጸሎት ከፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ የተለመደውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ሲያካሄድ ሰንብቶ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሚበጁ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡

ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

“ዕቀብ ማፀንተከ ዘተወፈይከ ከመ ትስብክ ቃሎ ቀዊመከ ቆመህ ቃሉን ትሰብክ ዘንድ የተቀበልከውን አደራ ጠብቅ” 1ኛ ጢሞ. 4፥14)፡፡