የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ዐበይት የሥራ ክንውኖችና አባታዊ መመሪያዎች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በቅዱስ ፓትርያርክነት ሥልጣን ከተሠየሙበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ በቅዱስ ሲኖዶስ እያስወሰኑ ለቤተ ክርስቲያናችን በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መቀላጠፍ ዐይነተኛ ጠቀሜታ ያላቸው መመሪያዎችን አስተላልፈዋል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጒዞ
መድኀኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላካዊ የማዳን ሥራውን ወደ ዓለም እንዲያዳርሱ ዐሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርትን ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል መርጦ ለሦስት ዓመት ከአራት ወር ከዐሥር ቀን አምላካዊ ትምህርተ ወንጌልን አስተምሮአቸዋል፡፡ ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ አምላካዊ ትምህርቱን ሰምተው፣ መለኮታዊ ገቢረ ተኣምሩን አይተው፣ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ተረድተዋል፡፡ (ዮሐ. 6) ካመኑ በኋላ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፤ ያመነ የተጠመቀ ይድናል@ ያላመነ ግን ይፈረድበታል”፡፡ (ማር.16፥15-16) ብሎ አዘዛቸው፡፡ በክርስትና ትምህርት ይህ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠው ወንጌልን ለዓለም ሁሉ የማስተማር (የመስበክ) ተልእኮ “ዐቢይ ተልእኮ” (great mission) ተብሎ ይጠራል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት የተከበረው የጸሎተ ሐሙስ በዓል እንደተለመደው በጾም፣በጸሎት፣ በኅጽበተ እግር ሥነ ሥርዐትና በሥርዐተ ቅዳሴ ተከብሯል፡፡ሙሉ ሥነ ሥርዐቱ በቅዱስ ፓትርያርኩ የተመራ ሲሆን ቀኑ የትሕትና የፍቅር ስለሆነ ይህንን የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትሕትና ተግባር ሁሌም ከልባችን ጽላት ላይ በመጻፍ ምእመናን የሕይወታቸው መርሕ እንዲያደርጉት አሳስበዋል፡፡



ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምህላ አስተጋብኡ ሕዝበ ሊቃውንተ ሕዝብ፤ ጾምን ቀድሱ፣ጉባኤውንም አውጁ፤ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ኣምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ (ኢዩ ፩÷፲፬)
በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወደ ፓትርያርክነት ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ በርካታ ዘመን ተሸጋሪ የሆኑ ሥራዎች በቅዱስ ሲኖዶስ እያስወሰኑ እንዲሠሩ አድርገዋል፡፡ ከዚህ አኳያ እጅግ የጎሉና በትውልዱ ሊታወሱ ከሚገባቸው ታሪካውያን ሥራዎቻቸው መካከል ጥቂቶቹን ብቻ ከዚህ ቀጥሎ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡ 1. የመገናኛ ብዙኃን መቋቋምን በተመለከተ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ […]
በቅዱስነታቸው ዘመነ ፓትርያርክነት የተላለፉ በታሪክ የሚዘከሩ መመሪያዎች፤
ሀ. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሪ ዕቅድ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ በፓትርያርክነት ተሹመው ርእሰ መንበርነቱን እንደያዙ ባስተላፉት የመጀመርያው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የመክፈቻ አባታዊ መልእክታቸው ቤተ ክርስቲያንዋ እንደተቋም ከማእከል ጀምሮ በደረጃ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ድረስ የሚወርድ ዘመናዊና የተጠና መሪ […]