የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ዐበይት የሥራ ክንውኖችና አባታዊ መመሪያዎች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በቅዱስ ፓትርያርክነት ሥልጣን ከተሠየሙበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ በቅዱስ ሲኖዶስ እያስወሰኑ ለቤተ ክርስቲያናችን በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መቀላጠፍ ዐይነተኛ ጠቀሜታ ያላቸው መመሪያዎችን አስተላልፈዋል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጒዞ
መድኀኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላካዊ የማዳን ሥራውን ወደ ዓለም እንዲያዳርሱ ዐሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርትን ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል መርጦ ለሦስት ዓመት ከአራት ወር ከዐሥር ቀን አምላካዊ ትምህርተ ወንጌልን አስተምሮአቸዋል፡፡ ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ አምላካዊ ትምህርቱን ሰምተው፣ መለኮታዊ ገቢረ ተኣምሩን አይተው፣ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ተረድተዋል፡፡ (ዮሐ. 6) ካመኑ በኋላ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፤ ያመነ የተጠመቀ ይድናል@ ያላመነ ግን ይፈረድበታል”፡፡ (ማር.16፥15-16) ብሎ አዘዛቸው፡፡ በክርስትና ትምህርት ይህ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠው ወንጌልን ለዓለም ሁሉ የማስተማር (የመስበክ) ተልእኮ “ዐቢይ ተልእኮ” (great mission) ተብሎ ይጠራል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት የተከበረው የጸሎተ ሐሙስ በዓል እንደተለመደው በጾም፣በጸሎት፣ በኅጽበተ እግር ሥነ ሥርዐትና በሥርዐተ ቅዳሴ ተከብሯል፡፡ሙሉ ሥነ ሥርዐቱ በቅዱስ ፓትርያርኩ የተመራ ሲሆን ቀኑ የትሕትና የፍቅር ስለሆነ ይህንን የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትሕትና ተግባር ሁሌም ከልባችን ጽላት ላይ በመጻፍ ምእመናን የሕይወታቸው መርሕ እንዲያደርጉት አሳስበዋል፡፡



ታኅሣሥ 29 ቀን የ2007 ዓ.ም የልደት በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ
‹‹ወውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ ወኀደረ ላዕሌነ
ያ ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእኛ ላይም አደረ።››
(ዮሐ. 1፥14)
ከጥቅምት 12 እስከ 26 ቀን 2007 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡
ምልአተ ጉባኤው ከጥቅምት 12-26 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ ባደረገው ምልአተ ጉባኤ በተመረጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና የሕግ ባለሙያዎች ሲደከምበት የቆየውን የተሻሻለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያን አጽድቋል፡፡ በ33ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተወያይቶ ባጸደቀው የዐቋም መግለጫና በሌሎችም በርካታ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ በስፋትና በጥልቀት ሲወያይ ከሰነበተ በኋላ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ስብሰባውን በጸሎት አጠናቋል፡፡
ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ
ቤተ ክርስቲያንን በንጹሕ ደሙ የዋጀ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምእመናንን በቅዱስ መንፈሱ መሪነት እየጠበቀ ከዚህ ጊዜ ስላደረሰን ክብርና ምስጋና ለእርሱ እናቀርባለን፡፡