• Amharic  
  • English  
  • ቀዳሚ ገጽ
  • የኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
    • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • ልዩ ጽ/ቤት
    • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት
    • የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች
    • የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
    • የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጒዞ
  • ቃለ በረከት
  • ዜና መዋእል
  • አርዕስተ ሊቃነ ጳጳሳት
  • ያግኙን
  • Menu Menu

መጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የኮሮና ቫይረስ እንዳይስፋፋ ምእመናን በቤታቸው ሆነው እንዲጸልዩ መግለጫ ሰጠ፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

በዓለም ላይ ተስፋፍቶ የቆየውና በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ የገባው የኮረና ቫይረስ በሽታ ዕለት ዕለት እየተስፋፋ ጥቂት የማይባሉ ወገኖቻችን በወርሽኙ መያዛቸው ታውቋል፡፡ በመሆኑም ይህ ወረርሽኝ እንዳይስፋፋና በቀጣይም ሌሎች ወገኖቻችን እንዳይያዙ መከላከሉ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ በመሆኑ ቋሚ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ስብሰባ በማድረግ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን የሕዝቡን ሁሉ ምሕላና ጸሎት፣ የካህናቱን አስተበቊዖት በርኀራኄው ሰምቶ፣ በቅዱሳኑ ቃልኪዳን፣ በወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም አማላጅነት ቍጣውን በምሕረቱ መዓቱን በትግዕሥቱ አሳልፎ ፍጹም ደኅንነትን እንደሚሰጠን እያመንን፡-

1. በአሁኑ ጊዜ እየደረሰ ያለው የወረርሽኝ በሽታን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለውን የጤና አጠባበቅ ምክርና ትምህረት እንዲሁም በፍትሕ መንፈሳዊ እንደተደነገገው ቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት በማድረግ ወረርሽኑን ማስቆም እንዲቻል በመላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጣም በተወሰኑ ካህናት መንፈሳዊ አገልግሎቱ እንዲሰጥ ሌሎች ካህናትና ምእመናን ለጊዜው በየቤታቸው በጸሎት እንዲወሰኑ፣ በአገልግሎት ላይ ለሚገኙ አገልጋይ ካህናትም በቤተ ክርስቲያኑ ቅጽረ ግቢ እንዲወሰኑ ሆኖ አስፈላጊው ሠርከ ኅብስት የምግብ አቅርቦት እንዲዘጋጅላቸው እንዲደረግ፣
2. በአሁኑ ጊዜ የወረርሽኙን ፍጥነት ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት እንዳለ ሆኖ በቀጣይ በበሽታው እየተያዙ ለሚመጡ ወገኖቻችን ማቆያ ቦታ ማዘጋጀቱ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር ከአዲስ አበባ ጀምሮ በመላው አህጉረ ስብከት የሚገኙ፡ (ሀ) መንፈሳዊ ኮሌጆች (ለ) የካህናት ማሠልጠኛዎች (ሐ) ዘመናውያን ት/ቤቶች አስፈላጊው ዝግጅት እንዲደረግላቸውና መሟላት የሚገባቸው ሁሉ ተሟልቶ ለሕሙማን ማቆያ እንዲውሉ ለማድረግ ወረርሽኙ እስከሚያበቃ ድረስ አገልግሎት መስጫ እንዲሆኑ የሚመለከተው አካል ተረክቦ እንዲያስተናግድባቸው ተወስኗል፡፡
3. በአሁኑ ጊዜ በወረርሽኙ ምክንያት መንግሥት ሕሙማንና የተቸገሩ አካላትን ለመርዳት እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ከመንበረ ፓትርያርክ ለጊዜው ብር3,000,000 (ሦስት ሚሊየን ብር) በመንግሥት ደረጃ ለተቋቋመው ርዳታ አሰባሳቢ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እንዲሰጥ፣
4. በቤተ ክርስቲያናችን ሥር ለሚገኙ የሕጻናትና ማሳደጊያ ቦታዎች የሚገኙ ሕጻናትን እና ችግረኞችን በምግብና በንጽሕና መጠበቂያ መደጐም የሚያስፈልግበት ጊዜ በመሆኑ አስፈላጊው ርዳታ የማሰባሰብ ሥራ እንዲሠራና እንዲረዱ በቤተ ክርስቲያናችን ሥር በተቋቋመው ተስፋ ግብረ ኀይል በኩል የማስተባበሩ ሥራ እንዲሠራ፣
5. ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አሁን የያዝነውን የጾምና የጸሎት ጊዜ ምክንያት በማድረግ በቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ቅዳሴውን በመምራትና በመባረክ መቆየታቸውን ቋሚ ሲኖዶስ ተገንዝቧል፡፡ ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን ያለው ወረርሽኝ በእጅጉ እየተስፋፋ በመሆኑና የተለየ አባታዊ ጸሎትና ሱባኤ የሚያስፈልግ ሆኖ በመገኘቱ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ከዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለዓለም ሰላምና ለሕዝቦች ደኅንነት ሲባል ለጊዜው ለብቻቸው በልዩ የጾምና የጸሎት የሱባኤ ጊዜ እንዲቆዩ ቋሚ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ዓለማችንንና ሀገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን ለሕዝባችንም ምሕረትንና ፈውስን ይስጥልን !አሜን !

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/007-3.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/logo-am.svg tc32020-04-01 09:54:362025-01-27 09:55:57መጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የኮሮና ቫይረስ እንዳይስፋፋ ምእመናን በቤታቸው ሆነው እንዲጸልዩ መግለጫ ሰጠ፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ምርቃት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጡ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማስመልከት ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወኣምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመተ ምሕረት

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • April 2025
  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ካህናትና ምእመናን ከኮሮና ቫይረስ ራሳቸውን እንዲጠብቁ መመሪያዎች አስተላልፏል፡- Link to: መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ካህናትና ምእመናን ከኮሮና ቫይረስ ራሳቸውን እንዲጠብቁ መመሪያዎች አስተላልፏል፡- መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ... Link to: ሚያዝያ 11 ቀን 2012 ዓ.ም የበዓለ የትንሣኤ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ሚያዝያ 11 ቀን 2012 ዓ.ም የበዓለ የትንሣኤ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሚያዝያ 11 ቀን 2012 ዓ.ም የበዓለ የትንሣኤ ቃለ ምዕዳንና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top