
የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በቅዱስ ፓትርያርክነት ሥልጣን ከተሠየሙበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ በቅዱስ ሲኖዶስ እያስወሰኑ ለቤተ ክርስቲያናችን በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መቀላጠፍ ዐይነተኛ ጠቀሜታ ያላቸው መመሪያዎችን አስተላልፈዋል፡፡
በቅዱስ ፓትርያርኩ ከተሰጡት ውጤታማ መመሪያዎችና ከተከናወኑት ተግባራት ውስጥ በጒልሕ የሚታወቁ ከዚህ በፊት ያልተደፈሩና በታሪክ ሊታወሱ የሚገባቸው እንዲሁም በመጪው ትውልድ ዘንድ በውጤታማነታቸው ሲዘከሩ መኖር ያለባቸውን ብቻ በጥቂቱ በመምረጥ ከዚህ ቀጥሎ በአጭሩ እናቀርባለን፡፡