• Amharic  
  • English  
  • ቀዳሚ ገጽ
  • የኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
    • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • ልዩ ጽ/ቤት
    • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት
    • የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች
    • የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
    • የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጒዞ
  • ቃለ በረከት
  • ዜና መዋእል
  • አርዕስተ ሊቃነ ጳጳሳት
  • ያግኙን
  • Menu Menu

ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ በሰማዕትነት ስለተሠዉ ኢትዮጵያውያን የቅዱስነታቸው መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

ግፉዓን ይትማሠጥዋ ለመንግሥተ ሰማያት በሃይማኖታቸው ምክንያት ግፍ የሚደርስባቸው መንግሥተ ሰማያትን ይናጠቋታል፡፡ (ማቴ. 11፣12)

በሰሜን አፍሪካ ሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ የተፈጸመው የግድያ ወንጀልን በተመለከተ ከኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በድጋሚ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ፡፡ ራሱን አይ ኤስ እያለ በሚጠራው አሸባሪ ቡድን ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በሰሜን አፍራካ በሊቢያ ውስጥ በሜዲትራንያን ባሕር አካባቢ በንጹሓን የቤተ ክርስቲያናችን ልጆች ላይ ግፍ በተሞላበት አሠቃቂ ሁኔታ ግድያ እንደፈጸመ ታውቆአል፡፡ በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው የሁሉም ሃይማኖቶች ተልእኮ ሰውን ማዳን እንጂ ሰውን መግደል እንዳይደለ ይታመናል፡፡

ይሁን እንጂ በማንኛውም ሃይማኖት ተቀባይነት የሌለው ንጹሓን ዜጎችን በሃይማኖት ምክንያት በአሠቃቂ ግድያ የመግደል ወንጀል በዓለማችን መታየት ከጀመረ ሰነባብቶአል፡፡ ኢትዮያውያን ወገኖቻችንም በተለያየ ጊዜና በተለያየ አካባቢ የዚህ ዐይነቱ ግድያ ሰለባ መሆናቸውን አልቀረም፡፡ ከዚህ አንጻር በዚህ ሰሙን በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች በሆኑት ልጆቻችን ላይ የተፈጸመው አሠቃቂ ግድያ ከምንም ጊዜ በላይ ቤተ ክርስቲያናችንን ያሳዘነና ያሳሰበ ጉዳይ ሆኖ ተገኝቶአል፡፡

በመሆኑም የኢትዮያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተፈጸመው ድርጊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የዓለም ሃይማኖቶች ላይ የተቃጣ የወንጀል ተግባር መሆኑን በማመን መላው የሀገራችን ሕዝቦችና የሃይማኖት ተቅዋማት እንደዚሁም መላው የዓለም መንግሥታትና ማኅበረ ሰብ ይህንን ድርጊት በጽኑ ከመቃወምና ከማውገዝ በተጨማሪ ትርጒም ያለው ለውጥ የሚያመጣ ፈጣንና ዘላቂ መፍትሄ እንዲያፈላልግ እየጠየቀ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቶአል፡፡

1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተከታይ ልጆችዋ ላይ በአይ ኤስ አሸባሪዎች የተፈጸመው አሠቃቂ ግድያ ደረቅ የወንጀል ተግባር በመሆኑ በጽኑ ታወግዛለች፤

2. በሁሉም እንደሚታወቀውና በተግባርም እንደታየው የአሸባሪዎች የጥፋት ዕልቂት ሃይማኖትን፣ ቀለምን፣ ጾታንና አካባቢን ሳይለይ በአጠቃላይ በሰው ዘር ላይ የዘመተ የጥፋት ተልእኮ ስለሆነ የዓለም መንግሥታትና በአጠቃላይ የዓለም ማኅበረ ሰብ፣ እንደዚሁም ሁሉ የሃይማኖት መሪዎችና የፀረ ሽብር ተቅዋማት ለዓለማችን የሰላም መረጋገጥና ለሰው ልጆች በሕይወት የመኖር መብት መከበር ተባብረው እንዲሠሩ ቤተ ክርስቲያናችን በአጽንዖት ትጠይቃለች፤

3. የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም ዐቀፍ ማኅበረ ሰብና ከየሀገሩ መንግሥታት ጋር በመሆን የሚያካሂደውን የፀረ ሽብር እንቅስቃሴ አጠናክሮ በመቀጠል የዜጎች ሕይወት በአሸባሪዎች እንዳይቀጠፍ ከእስከ አሁኑ በበለጠ እንዲንቀሳቀስ ቤተ ክርስቲያናችን ትጠይቃለች፤ በዚህም ቤተ ክርስቲያናችን ከመንግሥትና ከሕዝብ ጎን ተሰልፋ የሚጠበቅባትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆንዋን ታረጋግጣለች፣

4. የኢትዮጵያ ሕዝቦች በሃይማኖትና በሌላው ሁሉ ሳንለያይ ከጥንት ጀምሮ ጠብቀን ያቆየነውን በኅብረት፣ በአንድነት፣ በፍቅርና በመቻቻል የመኖር ጸጋ አሁንም አጥብቀን በመያዝ የጋራ ጠላት የሆነውን ግብረ ሽብር የመመከት ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል እናሳስባለን፡፡

5. የመዋች ቤተ ሰቦች የሆናችሁ ወገኖቻችን ሁሉ በዚህ ግፍ የተሞላበት ጭካኔ የተገደሉት ልጆቻችን በዚህ ዓለም የመኖር መብታቸው ባጭሩ ቢቀጭም ጌታችን የተገፉ መንግሥተ ሰማያትን ይናጠቋታል ማለትም ይወርሱአታል ባለው አምላካዊ ቃል እግዚብሔር ዕንባቸውን አብሶ በመንግሥቱ የሚቀበላቸው መሆኑን ዐውቃችሁ፣ እንደዚሁም ልጆቻችን «ወኩን መሃይምነ እስከ ለሞት ወእሁበከ አክሊለ ሕይወት – እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን፤ የሕይወትንም አክሊል እሰጥሀለሁ፤» (ራእ. 210) ያለውን የሐዋርያው ቃል ጠብቀው ሃይማኖታችንን አንክድም በማለት የሃይማኖት ሰማዕትነትን የተቀበሉ የሃይማኖት መስተጋድላን ስለሆኑ የጀግና እናት አታለቅስም እንደተባለው የልጆቻችሁ ሰማዕትነት በእግዚአብሔር መንግሥት ታላቅ ዋጋ ስላላቸው በዚህ ከኀዘናችሁ እንድትጽናኑ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች፡፡

6. ቅዱስ ሲኖዶስ በሃይማኖታቸው ምክንያት ለተሠዉ ክርስቲያኖች ሊሰጥ የሚገባውን የሰማዕትነት ክብር በቀኖናው መሠረት መፈጸም ይቻል ዘንድ በአይ ኤስ አሸባሪ ቡድን በግፍ የተገደሉት ልጆቻችን ቤተ ሰብ የሆናችሁ ሁሉ የመዋቾቹን ስመ ክርስትና፣ ፎቶና ሙሉ አድራሻ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በተቻለ መጠን በፍጥነት እንድታቀርቡ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች፡፡

7. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር ከመውጣት፣ አስተማማኝ የሕይወትና የንብረት ዋስትና ወደሌለበት ሀገር ከመሄድ ተቈጥቦ በሀገሩ ውስጥ ሠርቶ ኑሮውን እንዲመራ ቤተ ክርስቲያን በአጽንዖት ትመክራለች፤

8. ቅዱስ ሲኖዶስ በየትኛውም አካባቢ የሚገኙትን ወገኖቻችንና የቤተ ክርስቲያን ልጆቻችን ከመሰል ጥቃት ለመታደግ እንዲቻል ከመንግሥት ጋር በቅርበት የሚሠራ ዐቢይ ኮሚቴ በአስቸኳይ የሚያቋቁም መሆኑን ይገልጻል፤

9. ከነገ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ለ7 ቀናት ያህል በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ባሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በግፍ ለተገደሉት ወገኖች ጸሎተ ፍትሐት፣ ለሀገራችንና በአጠቃላይ ለዓለሙ ሁሉ ሰላም መጠበቅ፣ ለሰው ልጆች በሕይወት የመኖር መብት መከበር ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖአል፡፡

ወስብሐት ለእግዚብሔር እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/007-3.jpg 664 1000 tc https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/logo-am.svg tc2015-04-21 16:48:032024-12-04 16:51:04ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ በሰማዕትነት ስለተሠዉ ኢትዮጵያውያን የቅዱስነታቸው መግለጫ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ምርቃት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጡ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማስመልከት ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወኣምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመተ ምሕረት

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • April 2025
  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሊቢያ ሀገር በንጹሓን ወገኖች ላይ ስለተፈጸመው አሠቃቂ ግድያ ስለማውገዝ በቅዱስነታቸው የተሰጠ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ Link to: ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሊቢያ ሀገር በንጹሓን ወገኖች ላይ ስለተፈጸመው አሠቃቂ ግድያ ስለማውገዝ በቅዱስነታቸው የተሰጠ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ... Link to: ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ አይኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በግፍ ስለተገደሉት ኢትዮጵያውያን በመስቀል አደባባይ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን አስተላልፈዋል፡፡ Link to: ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ አይኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በግፍ ስለተገደሉት ኢትዮጵያውያን በመስቀል አደባባይ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን አስተላልፈዋል፡፡ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ አይኤስ በተባለው...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top