• Amharic  
  • English  
  • ቀዳሚ ገጽ
  • የኢ/ኦ/ተ/ቤ
    • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
    • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • ልዩ ጽ/ቤት
    • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት
    • የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች
    • የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
    • የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጒዞ
  • ቃለ በረከት
  • ዜና መዋእል
  • አርዕስተ ሊቃነ ጳጳሳት
  • ያግኙን
  • Menu Menu

መስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም ቅዱስነታቸው ዘመን መለወጫ በዓል አስመልከቶ የሰጡት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትገኙ፤
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትኖሩ፤
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
በሕመም ምክንያት በየጸበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

ሰማይንና ምድርን፣ በውስጣቸው የሚገኙ ፍጥረታትን የሚታዩትንና የማይታዩትን የፈጠረ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ 2013 ዓመተ ምሕረት ወደ ዘመነ ማርቆስ ወንጌላዊ 2014 ዓመተ ምሕረት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡
“ዘይሔድሳ ለምድር በበረከቱ
እግዚአብሔር አምላክ ምድርን በበረከቱ ያድሳታል።”
(ድጓ)

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን እኛም እንደምንገነዘበው እግዚአብሔር አምላክ በፍጡራን አእምሮ ሊመጠን በማይችል በረከቱ ምድርንና በውስጧ ያሉትን ፍጥረታት ሁሉ በማያቋርጥ ሂደት እያደሰ ይኖራል ፡፡እግዚአብሔር አምላክ፥ ፍጥረታት እየታደሱ እንዲተካኩ በማድረጉ የቀደመው ሲያልፍ አዲሱ ሲተካ የሕይወት ጒዞ የማያቋርጥ ሆኖ እንዲቀጥል አድርጎአል ፡፡ከጌታችን ከአምላካችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት የነበረው አሮጌ ዘመን ዓመተ ፍዳ፣ ዓመተ ኩነኔ፣ በእርሱ መሥዋዕትነት ሲያሳልፍ ከልደተ ክርስቶስ ጀምሮ ያለውንም የምሕረት ዘመን ብሎ አድሶታል ፡፡ወደፊትም በዳግም ምጽአቱ ሰማይንና ምድርን በማሳለፍ የተሻለ ሕይወት ለሰው ልጆች መስጠቱ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ከቅዱስ ወንጌል ተምረናል (ማቴ. 24-25)። በመሆኑም ፍጥረታትን የማሳለፉ ተግባር የእግዚአብሔር ቀዋሚ ሥራ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ማርጀትና ኅልፈት የሌለበት ነው፤ በመጻኢው ዓለም ለሰው ልጆች ያዘጋጀው ሕይወትም ማርጀትና ኅልፈት የሌለበት፣ ሁል ጊዜ ሐዲስ ሆኖ የሚኖር ነው፡፡የሃይማኖታችን ጽኑ ተስፋም በአዲሱ ዓለም ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ይሁንና ወደ አዲሱ ዓለም ለመድረስ በየዘመኑ አዳዲስ ሥራዎችን በመሥራት እግዚአብሔርንና ፍጡራኑን በትጋት ማገልገል ያስፈለጋል፡፡ በዚህ ዓለም በፍጡራን ዐቅም ሊታደስ የማይችል ነገር ቢኖር ሃይማኖት ብቻ ነው፡፡ ከሃይማኖት በቀር ሌላው ሁሉ ለሰው ልጅ በሚጠቅም መንገድ ሊሻሻል፣ ሊስተካከልና ይበልጥ ሊጠቅም የሚችልበትን ዘዴ ተከትሎ ማሻሻል ተገቢ ይሆናል ፡፡
ዓለም ከተፈጠረ፣ ዘመን ከተቈጠረ አንሥቶ እስካሁን ባለበት ብቻ ቆሞ የኖረበት ዘመን የለም፤ በየጊዜው አዳዲስ የአሠራር ስልቶች እየተፈጠሩ፣ በቀጣይም በሌላ አዲስ ስልት እየተተኩ ይኖራሉ፤ ይህም ቀዋሚ የሆነ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው ፡፡ከዚህ አኳያ በተሰናባቹ በ2013 ዓመተ ምሕረት ማብቂያና በአዲሱ 2014 ዓ.ም. መግቢያ ላይ ቆም ብለን ልናስበው የሚገባ ነገር አለ ፡፡ይኸውም በተሰናባቹ ዓመት የነበረንን አጠቃለይ ሥጋዊና መንፈሳዊ ተግባር መመርመር ሲሆን ያልሠራንባቸው አጋጣሚዎች ካሉም በአዲሱ ዘመን አካክሰን በመሥራት ያመለጠንን ሁሉ በእጥፍ ሠርቶ ለመተካት ጠንክሮ መሥራት ያስፈለጋል ፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅድስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት፤

አዲሱ ዓመት ሲመጣ የደስታና የተሐድሶ ልቡና ዘመን እንዲሆንልን ከመመኘቱ ጋር በብሩህ ተስፋ መቀበላችን መልካም ነው፤ ይሁንና የሰላምና የእድገት ምኞታችን ወደ ተጨባጭ ፍሬ ሊደርስ የሚችለው በሥራ ብቻ ነው ፡፡በዓለማችን፣ እንዲሁም በአካባቢያችን የምናያቸው ውብና ድንቅ ነገሮች ሁሉ የሥራ ውጤት መሆናቸውን ለአንድ አፍታ እንኳ ቢሆን ልንዘነጋው አይገባም ፡፡ እግዚአብሔር እኛን የፈጠረ እንድንሠራ እንጂ እንድንተኛ አይደለም፤ በሥራ ላይ ቸልተኛነትን የምናሳይ ከሆነ የኑሮአችን መመሰቃቀል ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ፊት መክሊት ቀባሪ ተብሎ መጠየቅም እንዳለ ማሰብ ይገባናል ፡፡ እንደሚባለውም ‹‹ሰው ለመብላት አይኖርም፤ ለመኖር ይበላል እንጂ፡፡ ለሥራ ክብርን አለመስጠት፣ እግዚአብሔር እኛን የፈጠረበትን ዐላማ እንደመዘንጋት የሚያስቆጥር ይሆናል፤ ይህ ደግሞ ለእኛ የሚበጅ አይደለም (ዘፍ. 1፥3)። እግዚአብሔር ከበረከቱ ያጎደለብን አንዳችም ነገር የለም፤ በየጊዜው አዲስ የሆነ ራእይ፣ አዲስ የሆነ አሠራር፣ አዲስ የሆነ ጥበብ፣ አዲስ የሆነ ዘመን፣ አዲስ የሆነ ጤንነት ወዘተርፈ ከመስጠት ያቋረጠበት ጊዜ የለም ፡፡ ይሁንና እርሱ የሰጠንን አዲስ የዘመን ስጦታ በአዲስ አስተሳሰብና አሠራር ተቀብለን ካልተጠቀምንበት አዲስ ዘመን ማለቱ ብቻ ከምኞትና ከቃላት ያለፈ ትርጒም ሊኖረው አይችልም፡፡ ዘመኑ አዲስ ሊሆን የሚችለው እኛ በምናበረክተው ሥራ እንጂ ዘመን በራሱ አዲስ ሊሆን አይችልምና እግዚአብሔር አምላክ የሚወዳችሁና እግዚአብሔርን የምትወዱ ልጆቻችንና ወገኖቻችን በሙሉ አዳዲስ ሥራዎችንና አሠራሮችን በመፍጠር አዲሱን ዓመት በሁለመናው አዲስ አድርገን እናክብረው ፡፡እግዚአብሔር አምላካችን በዓሉን የደስታና የጤና፣ዘመኑን የምሕረትና የሰላም ያድርግልን፡፡
ለሀገራችንና ለመላው ዓለም ሰላምን ይስጥልን፡፡ሕዝባችንን በፍቅርና በአንድነት ያጽናልን፡፡የተዘራውን ዘር፣ የተተከለውን ተክል ይባርክልን፡፡የተወለዱትን ሕፃናት ያሳድግልን፡፡

መልካም የሥራ ዘመን ያድርግልን፤
እግዚአብሔር አምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ ይቀድስ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/001-2-1000.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/a/wp-content/uploads/logo-am.svg tc32021-09-11 14:15:392025-01-28 14:16:18መስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም ቅዱስነታቸው ዘመን መለወጫ በዓል አስመልከቶ የሰጡት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ
Search Search

Recent Posts

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ምርቃት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጡ
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሳዑዲ ዓረቢያ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በማስመልከት ለኢትዮጵያና ለሳዑዲ መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ
  • መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
  • ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወኣምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመተ ምሕረት

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • April 2025
  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ነሐሴ1 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም ቅዱስነታቸው ጾመ ፍልሰታን ምክያት በማድረግ ስለሀገር ሰላምና አንድነት ጥሪ ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን ቡራኬ Link to: ነሐሴ1 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም ቅዱስነታቸው ጾመ ፍልሰታን ምክያት በማድረግ ስለሀገር ሰላምና አንድነት ጥሪ ያስተላለፉት ቃለ ምዕዳን ቡራኬ ነሐሴ1 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም ቅዱስነታቸው ጾመ ፍልሰታን... Link to: መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top