የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ዐበይት የሥራ ክንውኖችና አባታዊ መመሪያዎች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በቅዱስ ፓትርያርክነት ሥልጣን ከተሠየሙበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ በቅዱስ ሲኖዶስ እያስወሰኑ ለቤተ ክርስቲያናችን በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መቀላጠፍ ዐይነተኛ ጠቀሜታ ያላቸው መመሪያዎችን አስተላልፈዋል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጒዞ
መድኀኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላካዊ የማዳን ሥራውን ወደ ዓለም እንዲያዳርሱ ዐሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርትን ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል መርጦ ለሦስት ዓመት ከአራት ወር ከዐሥር ቀን አምላካዊ ትምህርተ ወንጌልን አስተምሮአቸዋል፡፡ ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ አምላካዊ ትምህርቱን ሰምተው፣ መለኮታዊ ገቢረ ተኣምሩን አይተው፣ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ተረድተዋል፡፡ (ዮሐ. 6) ካመኑ በኋላ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፤ ያመነ የተጠመቀ ይድናል@ ያላመነ ግን ይፈረድበታል”፡፡ (ማር.16፥15-16) ብሎ አዘዛቸው፡፡ በክርስትና ትምህርት ይህ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠው ወንጌልን ለዓለም ሁሉ የማስተማር (የመስበክ) ተልእኮ “ዐቢይ ተልእኮ” (great mission) ተብሎ ይጠራል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት የተከበረው የጸሎተ ሐሙስ በዓል እንደተለመደው በጾም፣በጸሎት፣ በኅጽበተ እግር ሥነ ሥርዐትና በሥርዐተ ቅዳሴ ተከብሯል፡፡ሙሉ ሥነ ሥርዐቱ በቅዱስ ፓትርያርኩ የተመራ ሲሆን ቀኑ የትሕትና የፍቅር ስለሆነ ይህንን የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትሕትና ተግባር ሁሌም ከልባችን ጽላት ላይ በመጻፍ ምእመናን የሕይወታቸው መርሕ እንዲያደርጉት አሳስበዋል፡፡



ግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ
“ረከብነ ጸጋ ወተሰየምነ ሓዋርያተ ከመ ናስምዖሙ ለኣሕዛብ ወይእመኑ በስሙ፡- ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሓዋርያነትን ተቀበልን” (ሮሜ.፩÷፭)
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወኣምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወሰብዓቱ ዓመተ ምሕረት
“ወኣርኣይከኒ ፍኖተ ሕይወት፡- የሕይወትን መንገድ ኣሳየኸኝ” (መዝ.፲፭÷፱-፲፩)
የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
ወርኀ ጾሙን የተራበውን በመመገብ የተራቈተውን በማልበስ በኃላፊነት ያለን የኅብረተሰብ መሪዎችም ፍትሕንና እኩልነትን በማስፈንና ከነገሮች ሁሉ በፊት ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ በመስጠት ጾሙን እንድናሳልፍ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን::