ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ

፩. ሃይማኖተ ኦሪት

በአንድ እግዚአብሔር ማመን ሃይማኖተ ኦሪት ወይም ሃይማኖተ አይሁድ ይባላል፡፡ ኢትዮጵያ ነገ ደካም፣ ነገደ ሴም፣ ነገደ እስራኤል[1] የተባሉ ሕዝቦች ከሰፈሩባት ጊዜ ጀምሮ ሃይማኖተ እግዚአብሔር (እግዚአብሔርን ማመን) የታወቀባት ሀገር መሆንዋን ብዙዎች የታሪክ ምንጮች ያስረዳሉ[2] እነዚህ ነገዶች የመምለኬ እግዚአብሔር የኖህ ልጆች ናቸው፡፡ ከአባታቸው የወረሱትን ሃይማኖተ እግዚአብሔር ይዘው ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር፡፡  በተለይም ክብረ ነገሥት የተባለውን ታሪክ መጽሐፍ መሠረት አድርገው የተጻፉ ታሪክ መዛግብት ቀጥተኛ ጊዜውን በመግለጽ በአንድ እግዚአብሔር ማመን በኢትዮጵያ የተጀመረው በአንድ ሺሕ ዓመት ቅድመ ልደተ ክርስቶስ መጀመሪያ በንግሥተ ሳባ እና በልጅዋ በቀዳማዊ ንጉሥ ምኒልክ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡[3] መጽሐፍ ቅዱስ ንግሥተ ሳባ ንጉሥ ሰሎሞንን ለመጐብኘት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዳ እንደ ነበረች ያስረዳል፡፡[4] ክብረ ነገሥት የተባለው የታሪክ መጽሐፍ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ አጕልቶ በመግለጽ ንግሥተ ሳባ ከንጉሥ ሰሎሞንን ፀንሳ ወደ ኢትዮጵያ መመለስዋን፣ በኋላም ልጅዋ ምንልክ ተወልዶ ለአካለ መጠን ሲደርሥ ወደ ኢየሩሳሌም  በመሄድ ከአባቱ ጋር ተገናኝቶ በሚመለስበት ጊዜ በአባቱ መልካም ፍቃድ ከሕዝበ እስራኤል የተወጣጡ የበኲር ልጆች የሰዶቅ ልጅ አዛሪያስን፣ ሌዋውያን መምህራነ ኦሪትን፣ ካህናትንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ እንደተመለሰና በአክሱም እንደተቀመጠ ዘርዝሮ ያስረዳል፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ ሃይማኖተ ኦሪትን (ሃይማኖተ አይሁድን) አምኖ ካህናተ ኦሪት፣ ሌዋውያን በአክሱም ታቦተ ጽዮንን ያገለግሉ፣ ሕገ ኦሪትን ያስተምሩ ነበር[5] ይህ ይታወቅ ዘንድ ከሕገ ኦሪት፣ ሥርዐተ አይሁድ፣ ባህለ አይሁድና ልማደ አይሁድ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሠርጸው ይገኛሉ፡፡[6] ይህ ሃይማኖተ ኦሪት፣ ሥርዐተ አይሁድና አይሁዳዊ ባህል ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብና ሕዝበ እስራኤል የረዥም ታሪክ ትስስር እንዲኖራቸው አድርጎአቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር የኢትዮጵያ ሕዝብ ለብዙ ዘመናት ሃይማኖተ ኦሪትን (ሃይማኖተ አይሁድን) አምኖ መኖሩን ያስረዳሉ፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅድመ ሃይማኖተ ክርስትና በሃይማኖተ ኦሪት (ሃይማኖተ አይሁድ) ለረዥም ዘመናት መኖሩን በሁለት ዐበይት የታሪክ ነጥቦች መረጋገጥ ይቻላል፡፡

 

  1. ከዚህ በላይ የተገለጹት ሕገ ኦሪት፣ ሥርዐተ አይሁድና ባህለ አይሁድ በኢትዮጵያ ሕዝብ ህልውና (አኗኗር) ሠርጸው መገኘታቸው ነው፡፡
  2. ኅጽዋ ለንግሥት ሕንደኬ (የንግሥት ሕንደኬ ጃንደረባ) ለአምልኮተ እግዚአብሔር (ለእግዚአብሔር ለመስገድ ) ወደ ኢየሩሳሌም መሄዱና ከብሉይ ኪዳን ክፍል መጽሐፈ ኢሳይያስን ሲያነብብ መገኘቱ ነው ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሌሎቹ የአፍሪካ ሕዝቦች ቀድሞ በሃይማኖተ እግዚአብሔር የተመሠረተ ስለነበረ ሃይማኖተ ክርስትናን ለመቀበል ያዳገተው አንድም ነገር አልነበረም፡፡

፪. ሃይማኖተ ክርስትና በኢትዮጵያ

፪.፩. ኅጽዋ ለሕንደኬ

በኢትዮጵያ የሃይማኖተ ክርስትና ታሪክ መነሻው በግብረ ሐዋሪያት ምዕራፍ ፰፡፹፮-፵ የተመዘገበው መልእክተ መንፈስ ቅዱስና ሐዋርያዊ ተልእኮ ነው፡፡ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሕንደኬ የምትባል ንግሥት በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ነግሣ እንደነበረ “ኅጽዋ ለሕንደኬ” በሚባል የሚታወቅ አንድ የዕቃ ግምጃ ቤት አዛዥ(ሹም) እንደነበራት ያስረዳል፡፡ ደሀው ኅጽዋ ለንግሥት ሕንደኬ (የንግሥት ሕንደኬ ጃንደረባ) ለእግዚያብሔር ሊሰግድ በ፴፬ ዓ/ም ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር[7] የኢትዮጵያ ሕዝብ ከላይ እንደተገለጸው ከአንድ ሺህ ዓመት ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ጀምሮ ሕገ ኦሪትን፣ ሥርዐተ ኦሪትን ማክበርና እግዚአብሔርን የማምለክ ልምድ ነበረው፡፡ ኅጽዋ ለንግሥት ሕንደኬ ለአምልኮተ እግዚያብሔር ወደ ኢየሩሳሌም በሄደበት ጊዜ መልአከ እግዚአብሔር ከሰባቱ ዲያቆናት አንዱ የሆነው ፊልጶስን “ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ የሚወስደውን መንገድ ሂድ” ብሎት ሲሄድ ይህን ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አገኘው፡፡ ኢትዮጵያዊ የንግሥቲቱ ጃንደረባ ለእግዚአብሔር ሰግዶ ሲመለስ በሠረገላው ተቀምጦ መጽሐፈ ኢሳይያስን ያነብ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ጃንደረባው የተቀመጠበትን ሠረገላ ተከተለው ብሎ አዘዘ፡፡ ፊልጶስም ይህን የመንፈስ ቅዱስን ትዕዛዝ ተቀብሎ ሮጦ ሠረገላውን ደረሰበት፡፡

ፊልጶስ በትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 53 ከቍ. 7-8 ያለውን ቃለ ትንቢት ሲያነብ ሰምቶ ጃንደረባውን “የምታነብበውን ታውቃለህን” ብሎ ጠየቀው ጃንደረባውም ያስተማረው ሰው እንዳልነበረና የንባቡን ጥልቅ ምሥጢር እንደማያውቅ ገልጾ መለሰለት፡፡ ፊልጶስም እንደማያውቅ  ከገለጸለት መነሻ ሐሳብ ከልደቱ እስከ ዕርገቱ ድረስ ያለውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ አስረዳው፡፡ ጃንደረባው ቀድሞውም በሃይማኖተ እግዚአብሔር የሚኖር ነበር፡፡ በፊልጶስ ትምህርት ረክቶ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር እንደሆነ ወዲያውኑ በፍጹም ልቡ አመነ፤ በአፉም መሰከረ፡፡ አያይዞም ፊልጶስ እንዲያጠምቀው ጥያቄ አቀረበ፡፡ ፊልጶስም ጃንደረባው ለመጠመቅ ሙሉ ፍቃደኛ መሆኑንና በመንፈስ ቅዱስ የተላከበት ዐላማ መሆኑን በመገንዘብ ወዲያውኑ ውኃ ካለበት ወንዝ ወስዶ አጠመቀው፡፡ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባም የተነገረውን የእግዚአብሔር ቃል በመረዳቱ፤ ሃይማኖተ ክርስትናን በማመኑና በመጠመቁ ደስ እያለው ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡[8] ይህ በግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ ፰፡፳፮የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ የተለዩ መሠረታውያን ነጥቦች መኖራቸውን እንገነዘባለን፡፡ ከነዚህ አንዱ መሠረታዊ ሐሳብ ፈቃደ እግዚአብሔር ነው፡፡ ከላይ በተገለጸው የግብረ ሐዋሪያት ክፍል (ግብ.ሐዋ ፰፥፹፮) ፊልጶስ ከኢየሩሳሌም ተነሥቶ ወደ ጋዛ እንዲሄድ መልአከ እግዚአብሔር መንገሩና መንፈስ ቅዱስ በዚህ በጋዛ መንገድ ላይ የሚጓዘውን የጃንደረባው ሰረገላ ተከትሎ እንዲሄድ ፊልጶስን ማዘዙ ክርስትና ሃይማኖትና ጥምቀት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከሐዋርያት በቀጥታ እንዲተላለፍ የእግዚያብሔር ፈቃድ መሆኑን ያሳያል፡፡ ሁለተኛው የዚህ ክፍል መሠረታዊ ሐሳብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖትና የልብ ቅንነት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊው የንግሥት ሕንደኬ ጃንደረባ ለእግዚአብሔር ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዱና መጽሐፈ ኢሳያስን ሲያነብብ መገኘቱ ከሚያሳየው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖት በተጨማሪ ፊልጶስ ጃንደረባውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሥጢረ ሥጋዌ ባስተማረው ጊዜ እንደ አሕዛብ ወይም እንደ አይሁድ ሳይጠራጠር፣ ሳይከራከር በአንድ ጊዜ በፍጹም ልቡ አምኖ፣ በአፉም መስክሮ መጠመቁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሌላው ዓለም ቀድሞ በሃይማኖተ እግዚያብሔር የተመሠረተ ቅንና ጽኑዕ ልቡና ያለው ሕዝብ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ሃይማኖተ ክርስትናን አምኖና ተጠምቆ ወደ አገሩ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ ፊልጶስ ያስተማረውን ትምህርተ ክርስትና ያጠመቀውን ጥምቀት ከቤተ መንግሥት ጀምሮ በኢትዮጵያ አስተምሮአል፡፡[9] ኅጽዋ ለሕንደኬ ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ ተመልሶ ካስተማረበት ከ፴፬ ዓ/ም ጀምሮ ሃይማኖተ ክርስትና እና ጥምቀት በኢትዮጵያ እንደተመሠረተ የማያጠራጥር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐቅ ነው፡፡

አባ ጊዮርጊስ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ሊቅ መጽሐፈ ምሥጢር በተባለው ድርሠታቸው “ጥምቀትን ያመጣልን የንግሥት ሕንደኬ መጋቢ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ነው” በማለት ጃንደረባው አምኖና ተጠምቆ ወደ አገሩ ከመጣ በኋላ ይህን ሃይማኖተ ክርስትና እና ጥምቀት ማስተማሩን ገልጸዋል፡፡[10] ይህን የአባ ጊዮርጊስ ገለጻ በመከተል የጻፉ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ብዙዎች ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል አክሊለ ብርሃን ወልደ ቂርቆስ የተባሉ “መርሐ ልቡና” በተባለ መጽሐፋቸው የሚከተለውን ጽፈዋል፡፡

“ጌታችን ባረገ 3ኛው ዘመን የገርሳሞት ንግሥት (በግብረ ሐዋርያት ሕንደኬ የተባለችው) የእርሷ ባለሟል መኰንን ጃንደረባ ስለጌታችን ስለኢየሱስ ክርስቶስ ነገር ወደ ኢየሩሳሌም ተልኮ ሄዶ አምኖ ተጠምቆ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ሃይማኖትንና ጥምቀትን አስተማረ”፡፡(ግብ ሐዋ 8፡26-39)

ነገር ግን በዚያ ጊዜ የተጻፈ ወንጌል ስላላገኘን በቃል ያለ ይረሳል በመጽሐፍ ያለ ይወረሳል እንደተባለ የወንጌል ትምህርት በቃል ብቻ ሲነገር ነበረ፡፡እያደረ ግን እየጠፋባቸው እምነትንና ጥምቀትን ብቻ ይዘው እስከ 317 ዓ/ም ተቀመጡ፡፡ በ317 ዓ/ም አብርሀና አጽብሐ ሁለት ወንድማማቾች በነገሡ በ11ኛ ዐመት በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ሃይማኖትና ጥምቀት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ሠለጠነ እንጂ አባ ሰላማ ቀድሞ ያልነበረውን ጥምቀት ያመጣ አይመስልም››[11]

በጽሑፍ የተገለጸው ይህ ሐሳብ ክርስትና ሃይማኖትና ጥምቀት ከአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን በፊት በ1መቶ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ መመሥረቱን ያረጋግጣል፡፡በሌላም በኩል ከተለያየ የዓለም ክፍል የተሰበሰበ ልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝብ በበዓለ ኃምሳ ቀን በዓሉን ለማክበር በኢየሩሳሌም በተገኘ ጊዜ ኢትዮጵውያንም በዚያ በዓል ተገኝተው እንደነበሩና በሐዋርያው ጴጥሮስ ስብከት እንዳመኑ ወደ ሀገራቸው ወደ ኢትዮጵያም ተመልሰው ሃይማኖተ ክርስትናን እንዳስተማሩ ዮሐንስ አፈወርቅ በስብከቱ መግለጹን ጠቅሰው የጻፉ ጥቂቶች አይደሉም[12] በተመሳሳይ ሁኔታ ሩፊኖስ፣ ሶቅራጥስ፣ ቴኦዶሪቶስና ሶዞሚኖስ የተባሉ የታሪክ ጸሓፊዎች በአንደኛ መቶ ክፍለ ዘመን ድሕረ ልደተ ክርስቶስ ማቴዎስ ሐዋርያ ወደኢትዮጵያ መጥቶ ወንጌለ ክርስቶስን ማስተማሩን እንደገለጹ ጠቅሰው የጻፉ ምሁራን አሉ፡፡[13] በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ሕዝብ በኅጽዋ ለሕንደኬ ትምህርት፣ በቅዱስ ጴጥሮስ የበዓለ ሐምሳው ስብከት በአመኑ ኢትዮጵያውያን ምእመናን ከአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድሕረ ልደተ ክርስቶስ ጀምሮ ሃይማኖተ ክርስትናን አምኖ፣ ጥምቀተ ክርስትናን ተጠምቆ ይኖር ነበር፡፡ ነገር ግን እስከ አራተኛ መቶክፍለ ዘመን ድኅረ ልደተ ክርስቶስ ቍርባን፣ ክህነት፣ ጠቅላላ የምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አፈጻጸም አልነበሩትም፡፡ ይህ ይሟላ ዘንድ አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት በአጋጣሚ ሳይሆን በጥበበ እግዚአብሔር የሚከተለው ታሪክ ሊፈጸም ችለዋል፡፡

፪.፪.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ)

በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድኅረ ልደተ ክርስቶስ ሜሮጵዮስ የተባለ ፈላስፋ ፍልስፈናን የሚያስተምራቸው ሁለት ዘመዶቹ ወጣቶችን አስከትሎ ከጢሮስ ወደህንድ ለመሄድ በቀይ ባሕር(ብሕረ-ኤርትራ) በመርከብ ጉዞ ጀምሮ ነበር፡፡ እነዚህ ሁለት ወጣቶች ኤዶስዮስና ፍሬምናጦስ ይባሉ ነበር፡፡ ሁሉም በቀይ ባሕር በመርከብ ሲጓዙ በዚያ ጊዜ የኢትዮጵያ የባሕር ወደብ(የባሕር ጠረፍ) በነበረቺው በአዱሊስ አጠገብ ዓርፈው ነበር፡፡ ነገር ግን ሜሮጵዮስ የግድያ አደጋ አጋጥሞት እዚው ሞተ፡፡ የሜሮጵዮስን ገዳዮች በተመለከተ የተለያዩ የታሪክ አባባሎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ የታሪክ ጸሓፊዎች ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ቅኚ ግዛትን ትቃወም ስለነበረ በዚህ መርከብ ውስጥ የነበሩ ሜሮጵዮስና የመርከቡ ቀዛፊዎች የሮማ ሰላዮች መስለዋቸው የኢትዮጵያ ጠረፍ ጠባቂዎች እንደ ገደሉዋቸው ይገልጻሉ፡፡[14] ሌሎች የታሪክ ጸሐፊዎች ግን ሜሮጵዮስን የገደሉ ሽፍቶች እንደነበሩ ይተርካሉ[15] ይሁን እንጂ ሁለቱም የታሪክ ምንጮች ሜሮጵዮስን በቀይ ባሕር ወደብ በአዱሊስ መገደሉን ያረጋግጣሉ፡፡

ሁለቱን ወጣቶች ግን ኢትዮጵያውያን ሰዎች ከሞት አዳኑአቸው፡፡ ወደ አክሱም ወስደውም ለንጉሠ አክሱም አስረከቡአችው፡፡ ንጉሡም በፍቅር ተቀብሎ ኤዶስዮስን የግቢው አዛዥ፣ ፍረምናጦስን የአክሱም የጽሕፈት ክፍል ኀላፊና የልጆች አስተማሪ አድርጎ ሾማቸው፡፡

ለንጉሠ አክሱም ኢዛና እና ሳይዛና የተባሉ ሁለት ሕፃናት ልጆች ነበሩት፡፡ ኤዶስዮስና ፍረሚናጦስ ከነዚህ ሁለት ሕፃናት ጋር ሆነው በአክሱም ቤተ ቀጢን በተባለ ቦታ ላይ በነበረው ትምህርት ቤት ግእዝ ቋንቋንና በዚያ ጊዜ የነበረውን የቤተክርስቲያን ትምህርት ሁለቱ ለሰባት ዓመታት ተምረዋል፡፡ በዚህ መካከል ንጉሡ ብዙ ሳይቆይ ታምሞ ከዚህ ዓለም ተለየ (ሞተ)፡፡ ንግሥቲቱ አሕየዋ (ሶፊያ) ከንጉሡ ሞት በኃላ በልጆቹ በኢዛናና ሳይዛና ስም መንግሥቱን ታስተዳድር ጀመር፡፡ ታላቁ የንጉሥ ልጅ ኢዛና ለአካለ መጠን ደርሶ ዙፋኑን በወረሠ ጊዜ ፍሬሚናጦስና ኤዶስዮስ ወደ አገራቸው ለመመለስ የስንብት ጥያቄ አቀረቡ፡፡[16] በጥያቄው መሠረትም እንዲሄዱ ተፈቀደላቸው፡፡ ኤዶስያስ ወደ ሀገሩ ወደ ጢሮስ ሄደ፡፡ ፍሬሚናጦስ ግን በአክሱም ሃይማኖተ ክርስትና፣ ጥምቀት እንጂ ቍርባን፣ ክህነትና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን የሚያከናውኑ (የሚፈጽሙ) ካህናት ወደ አብያተ ክርስትያናት ሄዶ ጳጳስ ማምጣት እንደ ሚያስፈልግ በመገንዘብ ይህን ሐሳቡ ለንገሥታቱ ለአብርሀ፣ ለአጽብሐ አቀረበላቸው፡፡ ንግሥቲቱም ሆነ ወጣቶቹ ነገሥታትም ሐሳቡን ተቀብለው ፍሬሚናጦስ የኢትዮጵያን ቋንቋና ባህል በዚያውም ልክ የውጪውን ቋንቋና ባህል ያውቅ ስለነበረ እሱ ወደ እስክንድሪያ ሄዶ ካህናትን ጳጳስን እንዲያመጣላቸው ላኩት፡፡ፍሬሚናጦስም የነገሥታቱን መልእክት ይዞ በ325 ዓ/ም ወደ እስክንድሪያ ሄደ፡፡ የኢትዮጵያ ነገሥታት የላኩትንም መልእክት ለእስክንድርያው ፓትርያርክ ለቅዱስ እለስክንድሮስ አቀረበ፡፡ ነገር ግን ቅዱስ እለስክንድሮስ በወቅቱ ታምሞ ስለነበረ ብዙ ጊዜ ሳይቆይ በ328 ዓ/ም ዐረፈ፡፡ ጉዳዩ ግን በእርሱ ለተተካው ለቅዱስ አትናቴዎስ ቀርቦለት ፍሬሚናጦስ መንፈሳዊ ሕይወትና ዕውቀት ያለው አባት ስለነበረ በ330 ዓ/ም በቅዱስ አትናቴዎስ አንብሮት እድ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጳጳስ ሆኖ ተሾመ፡፡ ፍሬሚናጦስ የነበረው ስሙም አባ ሰላማ ተብሎ ተሰየመ፡፡[17]

አቡነ ሰላማ መዓርገ ጵጵስናን ተሾሞ ወደ አክሱም በመጣ ጊዜ ነገሥታቱ ኢዛናና ሳይዛና በክብር በደስታ ተቀበሉት፡፡ አቡነ ሰላማ ጵጵስናን ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ ወንጌለ ክርስቶስን የማስተማር ሥራው ተያያዘው፡፡ በመጀመሪያ ነገሥታቱ ኢዛናንና ሳይዛናን ከበፊቱ በበለጠ አስተምሮ አጥምቆአቸዋል፡፡ የክርስትና ስማቸውንም “ኢዛናን አብርሀ እና ሳይዛናን አጽብሐ” ብሎ ሰይሞአቸዋል፡፡ ቤተክርስትያን በዓራቱ የኢትዮጵያ ማዕዘን እንድትሰፋ፣ወንጌለ ክርስቶስ ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲደርስ ከፍተኛ ሐዋሪያዊ ትጋት አድርጎአል፡፡ የወንጌል የዕውቀት ብርሃን በኢትዮጵያ ስለአበራም የኢትዮጵያ ሕዝብ “ከሣቴ ብርሃን” በሚል ቅጽላዊ ስያሜ ሰይሞታል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅና ቅዱስ ያሬድ ይህን የአቡነ ሰላማ ሢመተ ጵጵስናንና ሐዋሪያዊ ተልእኮን ሲገልጽ፦

‹‹አሶተ ሥላሴ ዜነወ
ብዕለ ሐዋርያት ዲቤሁ ተክዕወ፤
ይክሥት ብርሃነ ተፈነወ
አባ ሰላማ ዘድልው ለጵጵስና
ሢመተ ክህነቱ ርቱዕ በሕገ ቀኖና”፡፡

በአማርኛ

‹የሥላሴን ሥልጣን አበሠረ፤
የሐዋርያት ሀብት በላዩ ላይ ፈሰሰ፤
ብርሃንን ሊገልጽ ተላከ
ለጵጵስና የተገባ አባ ሰላማ
የክህነቱ ሹመት በቀኖና ሕግ የተገባ ነው”፡፡

“አባ ሰላማ ለብሔረ አግዓዚ ኮነ ብርሃነ
ወበምጽአቱ ገብረ ሰላመ@ ሐዋርያ ዘተፈነወ ውስተ ምድርነ”

በአማርኛ ሲተረጐም
”አባ ሰላማ ለአግዓዚ ምድር ብርሃን ሆነ
በመምጣቱም ሰላም አደረገ ወደ ምድራችን የተላከ ሐዋርያ ነው፡፡ ”

 

በማለት በሰማያዊ ዜማው መስክሮአል፡፡ አቡነ ሰላማ ካሣቴ ብርሃን ከዚህ በላይ በተገለጸው ትጋቱና በተመሰከረለት ሢመተ ጵጵስናው ወንጌለ ክርስቶስን አስተምሮ ብዙ ሕዝብን ካጠመቀ በኋላ ጠንካራና በሁለመናው የተደራጀ መንበረ ጵጵስናን በአክሱም አቋቋመ፡፡ የክህነት አገልግሎት በስፋት እንዲሰጥ ከዲቁና ክስከ ኤጲስ ቆጶስነት ባሉት መዓርጋተ ክህነት የሐዲስ ኪዳን ካህናትን ሾመ፡፡

ሢመተ ካህናት

አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ሊቀ ጳጳስ ወንጌለ ክርስቶስን ከማስተማር ሐዋሪያዊ ተግበሩ ጎን ለጎን በአክሱም የብሉይ ኪዳን ደብተራ (ድንኳን) አገልጋዮች የነበሩትን ካህናተ ኦሪት አስተምህሮ ከሃይማኖተ አይሁድ ወደ ሃይማኖተ ክርስትና ከመለሳቸው በኋላ ካህናተ ሐዲስ ኪዳን አድርጎ ሾሞአቸዋል፡፡ በአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን አንብሮተ እድ እንደተሾሙ በታሪክ የሚታወቁ የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን የሐዲስ ኪዳን ካህናት የሚከተሉት ናቸው፡፡

 

 

ዲያቆናት ቀሳውስት ኤጲሶቆጶሳት
የብሉይ ኪዳን ስማቸው የሐዲስ ኪዳን ስማቸው
፩  ፊንሐስ ተንሥአ ክርስቶስ ተክለ ሃይማኖት እንበረም-ሕዝበ ቀድስ
፪  አሮን ስምዖን ገብረ መስቀል
፫  አዛርያስ ማቴዎስ
፬  አቤሜሌክ ዘእግዚእ
፭  ላእከሄኖክ አማኑኤል
፮  መልከጼዴቅ አሐዱ አምላክ
፯  ሳዶቅ ማዕቀበ እግዚእ[18]

 

በሚል ስያሜ የሐዲስ ኪዳን ካህናት አድርጎ ሾሞአቸዋል፡፡ እዚህ ከተገለጹት ካህናት መካከል የሁለቱ ቀሳውስት የብሉይ ኪዳን ስማቸው አልተገኘም፡፡ በኋላ ሁሉንም ዲያቆናት ቀሳውስት አድርጎ ሾሞአቸዋል፡፡ በቅዳሴ በሥርዐተ ቍርባንና ሕዝቡን በማስተማር እንዲረዱት አድርጎአቸዋል፡፡ ብፁዕ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን በመንፈስ ቅዱስ አየተመራ ይህን ሐዋርያዊ ተልእኮውን በተሳካ መልኩ በማከናወን ተጋድሎውን ከፈጸመ በኋላ በ፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሐምሌ ፳፮ ቀን ዐረፈ፡፡ ይህ ሐዋርያዊ ሰንሰለት ተያይዞ አሁን እስከ አሉ ቅዱሳን ፓትርያሪኮች፣ሊቃነ ጳጳሳት ኤጲስ ቆጶሳት ቀሳውስትና ዲያቆናት ደርሶአል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዚህ ሐዋርያዊ ታሪክ አካል ናቸው፡፡

 

 

 

[1] የካም፣ የሴም፣ የኢስራኤል ወገኖች፣ ዘሮች ማለት ነው፡፡

[2] የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ( ) የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት

[3] W.budg(1922) the qeen of sheba and her only son Menylik, ምክረ ሥላሴ ገ/አማኑኤል (2005) የእግዚአብሔር መንግስት በምድር ላይ ጠቅላላ የቤተ ክርስትያን ታሪክ)ገጽ .151

[4] የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር (   ) የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍት

[5] ኅሩይ ወልደ ሥላሴ(፲፱፻፹፩)(1991) ዋዜማ ገጽ፲፮-፲፯

[6] አባ ጎርጎርዮስ የሸዋ ሊቅ ጳጳስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ገጽ 15

 

[7] ምክረ ሥላሤ ገ/አማኑኤል(ቀ.ዶ.ር(2005) የእግዚያብሔር መንግስት ታሪክ በምድር ላይ (ጠቅላላ የቤተክርስትያን ታሪክ) ገጽ.156

[8] ማሕበረ ሐዋርያት ፍሬ ሃይማኖት (፲፱፻፶፫) ወንጌል ቅዱስ ሀእግዚአነ ወአምላክነ ወመድኀኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ገጽ ፻፺፫.

[9] sergew Hable selassie (1997) establishment of the Ethiopian church, in the church of Ethiopia, a panorama of history and spiritual life.P.3.

[10] የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ (!)1) መጽሐፈ ምሥጢር ገጽ.

[11] አክሊለ ብርሃን ወልደ ቂርቆስ (  ) መርሐ ልቡና ገጽ 23፣24

[12] Sergew Hable Slassie(1997) The establishment of the Ethiopian church ,A panorama of history and spiritual life.p.3

[13] ምክረ ሥላሤ ገ/አማኑኤል(ቀ.ዶ.ር(2005)የእግዚያብሔር መንግስት ታሪክ በምድር ላይ (ጠቅላላየቤተክርስትያን ታሪክ) ገጽ.157

 

[14] ዝኒ ከማሁ

[15] ዝኒ ከማሁ

[16]                       ( ) መጽሐፍ ስንክሳር ሐምሌ !6 ቀን

[17] ትንሣኤ አሳታሚ ድርጅት (!)8) መጽሐፈ ድጓ

[18] ዝኒ ከማሁ

የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት

መግቢያ፤ የቅድስት ሀገር የኢትዮጵያ እምነት ቅድመ ክርስትና

 ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ከክርስትና በፊት ስለ ነበራት ሃይማኖት በሁለት ዐይነት መንገድ ይነገራል፡፡ አንደኛው የኢትዮጵያ አቅኒዎች የመምለኬ እግዚአብሔር የኖኅ የልጅ ልጆች ሳባና ሰብታ ቀጥሎም የሴም ወገን ሳባውያን ስለ ነበሩ አያታቸው ኖኅ ያመልከው የነበረውን አንድ እግዚአብሔርን ማምለክ አላቋረጡም ነበር፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ እግዚአብሔርን ሳታመልክ የኖረችበት ጊዜ እንደሌለ ታውቋል፡፡ (ዘፍ ፪፥፲፭) ሀገራችን በተፈጠሮና በትውፊት ያገኘችውን አምልኮተ እግዚአብሔር ጠብቃ ከ2ሺ5)$5-9)*2 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ኖራለች፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ከ2ሺ03-9)*2 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የነበረችው የኢትዮጵያ ንግሥት ማክዳ በታሪክ የሰማችውን የሰሎሞንን ጥበብ ለማየትና በዘመኑ የነበረውን የኢትዮጵያን ሥልጣኔ ለማስተዋወቅ የብሉይ ኪዳንንም እምነትና ትምህርት ሥርዐቱንም ከመሠረቱ ለመረዳት ወደ ኢየሩሳሌም ተጒዛ ምኒልክ የሚባል ልጅ ከሰሎሞን ፀንሳ ተመለሰች፡፡

የንግሥተ ሳባ ልጅ ቀዳማዊ ንጉሥ ምኒልክም ተወልዶ ካደገ በኋላ የአባቱን አገር ኢየሩሳሌምን ጎብኝቶ ሲመለስ ጽላተ ሙሴንና ሥርዐተ ኦሪትን እስከ ሰሎሞን ዘመን ድረስ የተጻፉትን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አብረው መጥተዋል፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የብሉይ ኪዳን እምነት ከትምህርቱ፣ ከሥርዐተ አምልኮና ከመዓርገ ክህነቱ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ገብቶአል፡፡ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትም ወደ ጥንታዊው የኢትዮጵያ ቋንቋ ግእዝ መተርጎም የተጀመሩት ያን ጊዜ ነበር፡፡ (የኢትዮጵያ በእምነት በሦስቱ ሕግጋት) ኢትዮጵያ የብሉይ ኪዳን እምነትን መቀበልዋን የሚያስረዳ ታሪክ ብቻ አይደለም እስከ ዛሬ ድረስ በሕዝቡ ዘንድ የሚታዩት የብሉይ ኪዳን መገለጫ የሆኑ ትውፊቶችም ዋና ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ- ሕርምተ መባልዕት፣ ግዝረት በስምንተኛ ቀን፣ ሥርዐተ ማሕሌትና መሣሪያዎቹ፣ ክብረ ታቦትና የበዓላት አከባበር እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ ከዚህም ጋር በቅድስት ሀገር በኢየሩሳሌምና በአካባቢው ያላት የቦታ ይዞታ ኢትዮጵያ ከሌሎች አገሮች ቀድማ የብሉይ ኪዳን እምነት ባለቤት ከሆነችው ከኢየሩሳሌም ጋር የረዥም ጊዜ የእምነትና የታሪክ ግንኙነት እንደነበራት የሚያስረዳ ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስም ኢትዮጵያ በአንድ አምላክ የምታምን መሆንዋን ደጋግሞ ይናገራል፡፡ ሰለዚህም ዋናዎቹ ጥቅሶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” (መዝ. ፷፯፥፳፩)      “የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁም” (አሞ. ፱፥፯) “ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ ቊርባኔን ያመጡልኛል” (ሶፎ. ፫፥፲) የሚሉት ይገኛሉ በአጠቃላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ፱፻፹፪ ዓመት ቅድመ ልደተ ክርስቶስ እስከ ፴፬ ዓመተ ምሕረት ድረስ የብሉይ ኪዳንን እምነትና ሥርዐት ጠብቃ ኖራለች፡፡ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዕሥራ ምእት)

ክርስትና በኢትዮጵያ፤

 

እግዚአብሔር በነቢያት አድሮ ለሕዝቡ ያናገረው ትንቢት ሁሉ በየጊዜው ተፈጽሞአል፡፡ ያልተፈጸመ ቢኖርም እንደሚፈጸም የታመነ ነው፡፡ እነሆ #ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች$ ተብሎ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ኢትዮጵያ በ”4 ዓ.ም. የክርስትና እምነትን ተቀበለች፡፡ ይህም የሆነው (በሐዋርያት ሥራ %.!6-# እንደምናነብበው) የኢተዮጵያ ንግሥት የገርሳሞት (ህንደኬ) ሙሉ ባለሥልጣን የነበረ ቀደም ብሎ በተቀበለው የብሉይ ኪዳን እምነት መሠረት በዓለ ፋሲካን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ በነበረበት በወንጌላዊው በቅዱስ ፊልጶስ ትምህርት አምኖ በተጠመቀ ጊዜ ነው፡፡ ባለሟሉ ወይም ጃንደረባው ወደ ሀገሩ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ከቅዱስ ፊልጶስ ስለ ከርስቶስ የሰማውንና የተረዳውን ለወገኖቹ ለኢተዮጵያውያን እንዳስተማረ የጥንት ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሓፊው አውሳብዮስ የሚከተለውን ጽፎአል #የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሥልጣን ምሥጢረ ቃለ እግዚአብሔርን ከወንጌላዊው ከቅዱስ ፊልጶስ ተምሮ ያመነ፣ አይሁዳውያን ካልሆኑ ወገኖች የመጀመሪያው የክርስትና እምነት ፍሬ ነው፡፡ ለወገኖቹም የመጀመሪያው ሰባኬ ወንጌል የሆነ ሐዋርያ እርሱ ነው፤ የወንጌልን ዘርና ክርስትናን ምስክርነት ለመጀመሪያ ጊዜ በምድረ ኢትዮጵያ ዘርቷል፤ በእርሱም አማካኝነት በመዝሙር 87.”1 ላይ ስለ ኢትዮጵያ የተነገረው ትንቢት ተፈጽሟል$ (አውሳብዩስ 2ኛ መጽሐፍ ቁ.1)፡፡ ምናልባትም የዚህ ኢትዮጵያዊ ባለሟል ወይም ጃንደረባ ታሪኩና የሠራቸው ሥራዎች በአግባቡ ባለመጻፋቸውና ባለመዘከራቸው ነው እንጅ የጌታችን ወንጌል ከሐዋርያት ሰምተው እንዳስፋፉት የሐዋርያት ተከታዮች አንዱ ተደርጎ ይቈጠርና ይዘከር ነበር፡፡

 

ከጃንደረባው የሀገር ባለሥልጣን በማስከተልም ቅዱሳን የጌታችን የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ቅዱስ ማቴዎስ፣ ቅዱስ ናትናኤል፣ ቅዱስ በርተሎሜዎስና ቅዱስ ቶማስ በኢትዮጵያ ቅዱስ ወንጌልን መስበካቸው በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች በእነ ሩፊኖስና ሶቅራጥስ ተመስክሮአል፡፡ የክርስትና እምነት ከሥርዐተ ጥምቀቱና ከወንጌል ትምህርቱ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ቢገባም አንድ የራሱ የሆነ መንበር ያለው ጳጳስ በቋሚነት ባለመኖሩ በተለይም ሥርዐተ ቊርባንና ሌላውም ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ሳይፈጸም እስከ 3)” ዓ/ም ድረስ ቆይቶአል፡፡ ይሁን አንጅ የክርስትና ሃይማኖት ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጥንቱ የሀገራችን ግዛት በሞላው እየተሰበከና እየተስፋፋ ለመኖሩ ምስክር ነው፡፡

 

በ3)” ዓ/ም በትውልዱ ጢሮሳውያዊ፣ በዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የነበረው ቅዱስ ፍሬምናጦስ በንጉሡ በኢዛና ፈቃድ ወደ እስክንድርያ ተልኮ በ!ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ በቅዱስ አትናቴዎስ ሢመተ ጵጵስና ተቀብሎ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ፡፡ አባ ፍሬምናጦስ በመዓርገ ጵጵስና ከብሮ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሰላማ ተብሎ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ በመሆን ወደ ሀገራችን ሲመጣ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አቡነ ሰላማ ከሚለው በተጨማሪ “ከሣቴ ብርሃን” ብለው በሚል ሰይመዉታል፡፡ እስከ አሁንም ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን በሚል መጠሪያ ስም ይታወቃል፡፡ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃንም ሐዋርያዊ ተልእኮን በመቀጠል፤ ካህናትን በመሾም ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ በምልአት መፈጸም ተጀመረ፡፡

 

በዚህም ወንድማማች የነበሩት እና በጋራ በኢትዮጵያ ዙፋን ላይ የተሾሙት ነገሥታቱ ኢዛና እና ሳይዛና በይፋ ተጠምቀው ስማቸውም በግእዝ ቋንቋ አብርሀ እና አጽብሐ ተባሉ፤ ትርጒሙም “ጌታችን አንትሙሰ ብርሃኑ ለዓለም” (ማቴ. 5፥02) እንዳለው የክርስትና ብርሃን በመላው ሀገራችን መፈንጠቁን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚሁ በማያያዝም ነገሥታቱ በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ የወርቅ፣ የብር፣ የነሐስ ሳንቲሞችን ላይ የመስቀል ቅርጽ አንዲቀረጽ አደረጉ፤ የኢትዮጵያ ይፋዊ የመንግሥት ሃይማኖቷ ክርስትና መሆኑን ዓለም እንዲያውቅ አደረጉ፤ በሀገር ውስጥም በርካታ አብያተ ክርስቲያናትን አሳነጹ፤ የክርስትና ሃይማኖትም ብሔራዊ ሃይማኖት ሆነ፤ የክርስትናውን እምነትና ትምህርት በሚገባ ለተማሩትና ብቁ ለሆኑት የዲቁናና የቅስና መዓርግ ተሰጣቸው፤ የብሉይ ኪዳን መሥዋዕት ይሰዋባቸው የነበሩት ጥንታውያን ቅዱሳት መካናት አብያተ ክርስቲያንናት ሁነው መሥዋዕተ ሐዲስ የሚሠዋባቸው በመሆን አገልግለታቸውን ቀጠሉ ሌሎችም ክርስትናን የተቀበሉ ምእመናን ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ተሠሩ፤ ወንጌልም በየአውራጃው (በየአድያሙ) ተሰበከ፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትም ተተረጎሙ፡፡

 

በዚህ ዘመነ ቅዱሳን በሆኑት በነገሥታቱ አብርሀ እና አጽብሐ፣ በሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ምክንያት ሀገራችን መንግሥቷ ክርስቲያዊ መሆኑና የራስዋ የሆነ ሊቀ ጳጳስ ያላት ሀገር መሆኗ በመላው ዓለም ታወቀ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጵጵስና ክብር ያለው ከሮማውያን ግዛት ውጭ ያለ ሉዓላዊ መንበር መሆኑ ታወቀ፡፡

 

በ5ኛው ምእት ዓመት (4)’) ከጥንቱ የሶርያ ግዛት፣ ከታናሽ እስያና ከአርማንያ በርካታ ቅዱሳን መነኮሳት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር፣ ከእነርሱም እንደ አባ ሊባኖስ፣ ማኅበረ ጻድቃን፣ ማኅበረ በኵር፣ ማኅበረ ደጉኤ፣ እና ጻድቃነ መጠራ ይገኙበታል፤ በተለይም ዘጠኙ ቅዱሳን ተብለው የሚታወቁት አበው ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ብዙ መንፈሳዊ ተግባርን አከናውነዋል፡፡ እነርሱም አባ ጰንጠሌዎን፣ አባ ጽሕማ፣ አባ አሌፍ፣ አባ ገሪማ ፣ አባ አረጋዊ፣ አባ አፍጼ፣ አባ ሊቃኖስ፣ አባ ጉባና አባ ይምዓታ ይባላሉ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ከሠሯቸውም ተግባራት መካከል ጥቂቶቹ-

 

  • ሥርዐተ ምንኵስናን፤ ገዳማዊ ሕይወትን፣ ከሥርዐተ ምናኔን አቋቁመዋል፤
  • በቅዱስ ፍሬምናጦስ ጊዜ ያልተተረጎሙ መጻሕፍትን ተርጒመዋል፤
  • ገዳማትን በየቦታው አቋቁመዋል እስከ አሁንም በስማቸው ይጠራሉ፤
  • በከሣቴ ብርሃን ሰላማ ጊዜ የተቋቋመችውን ቤተ ክርስቲያን በስብከተ ወንጌል፣ በሥርዐተ ገዳም ማጠናከርና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

 

በዚህም የተቀደሰ ተግባራቸው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን ተብለው ይከበራሉ፡፡ በስማቸውም ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ታንጾላቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ በ6ኛው ምእት ዓመት (5)5 ዓ/ም በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ፤ ይህም የታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅ የቅዱስ ያሬድ መነሣት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከጥንት ጀምራ እስካሁን ድረስ የምትጠቀምባቸውን ጸዋትወ ዜማ በ3 ዐይነት ስልተ ድምፅና እጅግ ባማረ ጣዕመ ዝማሬ ያዘጋጀ እስካሁን ተወዳዳሪ የሌለው የመንፈሳዊ ዜማ እና የዜማ መጻሕፍት ደራሲ ነው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት፣ “አልቦ እምቅድሜሁ፣ ወአልቦ እምደኀሬሁ፣ ማሕሌታይ ስብእ ዘከማሁ” ከእርሱ በፊት፣ ከእርሱም በኋላ እንደ እርሱ ያለ ማሕሌታዊ የለም በማለት አድንቀዉታል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ያዘጋጃቸው 3 ዐይነት ስልተ ድምፅም ግእዝ ዕዝልና አራራይ ናቸው፡፡ ዛሬ ማንኛውም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚፈጸመው ቅዱስ ያሬድ ባዘጋጀው ሰማያዊ ዝማሬ መላእክት፣ መንፈፈሳዊ ዜማና ሥርዐተ ዜማ ነው፡፡

 

ከ02ኛው እስከ 05ኛው ምእት ዓመት የነበረው ዘመን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በብዛት የተነሡበት፣ በዮዲት ጊዜ የፈረሱት አብያተ ክርስቲያናት የተጠገኑበትና የታደሱበት ዘመን ነበር፡፡ በዓለም እጅግ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፉት የጻድቁ ንጉሥ የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የታነጹት በዚህ ክፍለ ዘመን ነበር፡፡ ቅዱስ አቡነ ኢየሱስ ሞኣ የደብረ ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም ታላቅ ትምህርት ቤት ያቋቁመበት፣ ታላቁና ሐዲሱ ሐዋርያ ጻድቅ ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫና ሌሎችም ብዙ ቅዱሳን የተነሡት በዚህ ክፍለ ዘመን ነበር፡፡ ይህ ዘመን ስብከተ ወንጌል በመላ ኢትዮጵያ የተስፋፋበት፣ ገዳማዊ ሕይወት በተለይም ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል እንደ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ አቡነ ፊሊጶስ፣ አቡነ መድኀኒነ እግዚእ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘገዳመ ዋሊ፣ አቡነ ገብረ ኢየሱስ ዘደብረ ሳን፣ የጣና ገዳማት፣ በዐባይ ሸለቆ ዙሪያ ታላላ አድባራት የታነጹበት፤ ጌታችን የተሰቀለበትና በከበረ ደሙ ፈሳሽነት የተቀደሰው እውነተኛው መስቀለ ክርስቶስ በዐፄ ዳዊት ዘመን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በኋላም በልጃቸው በታላቁ ንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብ ዳግማዊ ቈስጠንጢኖስ አማካኝነት በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም የተቀመጠበት ዘመን፣ ትምህርትና ዕቅበተ እምነት የተጠናከረበት፣ መንፈሳዊያን መጻሕፍት ከዐረብኛ ወደ ግእዝ የተተረጎሙበትና በብሔራውያን ሊቃውንት ብዙ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት የተደረሱበት ነበር፡፡

 

ከዚህ በኋላ 06ኛው ክፍለ ዘመን ለቤተ ክርስቲያናችን ከባድ የፈተና ጊዜ ነበር፡፡ የውጭ ሳይሆን የውስጥ ጠላት የሆነው ግራኝ መሐመድ የክርስትና ሃይማኖትን በሚቃወም በውጭ ኀይል እየተረዳ በ1ሺ5)”9 ዓ.ም. ከምሥራቅ ኢትዮጵያ ተነሥቶ በቤተ ክርስቲያናችንና በሀገራችን ህልውና ላይ እጅግ አሠቃቂ መከራ አድርሶአል፡፡ እጅግ ብዙ ካህናትንና ምእመናንን ገድሎአል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትንና ንዋያተ ቅዱሳትን አጥፍቷል፡፡ በጭካኔና በክፉ ማስፈራራት አንዳንድ ክርስቲያኖችንም ወደ እስልምና እንዲገቡ በማስገደድ ተከታዮቹ አድርጓቸው ነበር፣ እምቢ ያሉትም በሰማዕትነት አልፈዋል፡፡ ይሁን እንጂ ያን ጊዜ የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱ የጠነከረ፣ ሥነ ምግባሩ የቀና፣ ሃይማኖቱም የጸና ስለ ነበረ በፖርቱጋሎች ኀብረት በእግዚአብሔር ኀይል ግራኝ መሐመድን ለመደምሰስ ችሏል፡፡

 

ከግራኝ መሐመድ በኋላም ጀስዊት የተባሉ የካቶሊክ ሚስዮኖች የኢትዮጵያን ሕዝብ የካቶሊክ ሃይማኖት ተቀባይ ለማድረግ ባደረጉት ሙከራ የብዙ ሰዎች ደም ፈስሶአል፡፡ ይልቁንም በዐፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግሥ (1ሺ5)(5-1ሺ6)!3 ዓ.ም.) የካቶሊክ ሚሲዮናውያን በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ ብጥብጥ ፈጥረው ነበር፡፡ በኋላም ዓፄ ፋሲል ወደ ሥልጣን ሲመጡ “ፋሲል ይንገሥ፣ ተዋሕዶ ሃይማኖት ይመለስ፣ የሱስንዮስ ሃይማኖት ይርከስ” ብለው ብጥብጡን በሰላም፣ ጥፋቱን በልማት፣ በመለወጥ ጎንደርን የሃይማኖትም የመንግሥትም መናኸሪያ አድርው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሰፊ ሥራን ሠርተዋል፡፡

 

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭና የውስጥ ኀይላት በየጊዜው እየተነሡ ሊያዳክሙአት ቢሞክሩም የሚደርስባትን ሙከራና ፈተና ሁሉ ኀይልዋ በሆነው በክርስቶስ ድል እያደረገች ኖራለች፡፡ ቤተ ክርስቲያናች ከ4ኛው እስከ !ኛው መቶ ክፈለ ዘመን ድረስ ከእስክንድርያ ተሾመው በሚመጡ ብፁዓን ጳጳሳት የበላይ መንፈሳዊ አመራር ሥር ቆይታለች፡፡ ይሁን እንጂ ከእስክንድርያ ወደ ኢትዮጵያ ይመጡ የነበሩ ጳጳሳት ሥልጠናቸው ክህነትና ቡራኬ መስጠት፣ ነገሥታትን እየቀቡ ማንገሥ ብቻ ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ማንኛውም አስተዳደር ግን እስከ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቀዳማዊ ዕጨጌ ድረስ በሊቃነ ካህናት ሲሆን ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት በኋላ የእርሳቸው መንበር ወራስያን በሆኑት ዕጨጌዎች ነበር፡፡

 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስቀድሞ በቅዱስ ሐርቤ (1ሺ1)07-1ሺ1)$7 ዓ.ም.) በኋላ በዐፄ ዮሐንስ ራብዓዊ (1ሺ8)%3-1ሺ8)’1 ዓ.ም.) ከሊቃውንቷ መካከል መርጣ ጳጳስ ለመሾም ለእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ደጋግማ ያቀረበችው ጥያቄ በ!ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አጋማሽ ላይ መልስ አግኝቶአል፡፡   በዚህም መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ በንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ ዘመን በ09)!1 ዓ.ም. ግንቦት !5 ቀን ከራስዋ ሊቃውንት መካከል አራት አበውን መርጣ ካይሮ ላይ በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል በብፁዕ ወቅዱስ ዮሐንስ 09ኛ አንብሮተ እድ እንዲሾሙ አድርጋለች፡፡ እንዲሁም በ1ሺ9)!2 ዓ.ም. የግብጹ ፓትርያርክ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ስለ ዕጨጌ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ሳዊሮስ ጳጳስ ብለው ሾመዋቸዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ኢትዮጵያ የኢጣሊያ ቅኝ ግዛት ቤተ ክርስቲያንዋንም ካቶሊክ ለማድረግ፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቃውንትንም ለማጥፋት ከ09)!8-09)”3 ዓ.ም. ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ላይ ወረራ አደረገች፡፡ በዚህም ጊዜ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትና ቅርሳቅርሶች ተቃጠሉ፤ ንዋያተ ቅድስት ተዘረፉ፤ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ መነኮሳትና ዲያቆናት ምእመናንም ተገደሉ፡፡

 

ይሁን እንጂ ቤተ ክርስቲያናችን ይህን የግፍ ዘመን በትዕግሥት አሳልፋና እንደገና ተደራጅታ ለሕዝቡ አገልግሎቷን ቀጥላለች፡፡ ከጠላት ወረራ በኋላም ቀደም ሲል ከተሾሙት አምስት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት መካከል ሦስቱ ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለዩ በአንድ ጳጳስ ብቻም ብዙ መንፈሳዊ ተግባርን ማከናወን ስለማይቻል፣ እንደገና ሐምሌ 08 ቀን 09)# ዓ.ም. ካይሮ ላይ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዮሳብ ዳግማዊ አንብሮተ እድ አምስት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ተሾሙ፡፡ ከሊቀ ጳጳስ ቄርሎስ ግብጻዊ ሞት በኋላም ጥር 6 ቀን 09)#3 ዓ.ም. ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሊቀ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ተብለው በፓትርያርክ ዮሳብ ዳግማዊ ተሠየሙ፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ አኳኋን ከኀይል ወደ ኀይል ከእድገት ወደ ተሻለ እድገት እየተራመደች ቆይታ በ09)$1 ዓ.ም. ሰኔ !1 ቀን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ የኢትዮጵያ መጀመሪያው ፓትርያርክ ሆነው ተሾሙ፡፡ እነሆ ይህ ራስን ችሎ በራስ የመተዳደር መብትና ሥልጣን ሊገኝ የቻለው በግርማዊ ቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥልሴ ክፍተኛ ጥረት በቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ድጋፍ፣ ፍላጎትና በእስክንድርያውያንም ስምምነት መሆኑ ምን ጊዜም ታሪክ የማይረሳው እውነት ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራስዋን ችላ በራስዋ ፓትርያርክ መተዳደር ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ስድስት ፓትርያርኮችን ሾማለች፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በሀገር ውስጥ $5 አህጉረ ስብከት ያሏት ሲሆን፣ በውጭ ሀገርም ” የሚሆኑ አህጉረ ሰብከትን በኢየሩሳሌም፣ በካሪቢያን ደሴቶችና በላቲን አሜሪካ፣ በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በአፍሪካ፣ በካናዳና በሌሎችም አሏት በአጠቃላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሌለችበት የዓለም ክፍል የለም፡፡ የተከታዮችዋ ምእመናን ቍጥርም ፶፭ ሚሊዮን በላይ ሲሆን በርካ ገዳማት አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት፣ ከፍተና የትምህርት ተቋማት አሏት፡፡

 

#ይትባረከ እግዚአብሔር ዘአልዐላ ለጽዮን እምኵሉ ዓለማት$ ቤተ ክርስቲያንን ከሁሉ ይልቅ ከፍ ከፍ ያደረጋት እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፡፡

 

የኢትዮጵያ መንበረ ጵጵስና (ሊቀ ጵጵስና) ከአቡነ ሰላማ እስከ አቡነ ባስልዮስ

 

ኤጲስ ቆጶስና ወይም ጵጵስና በሐዲስ ኪዳን ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች የተሠጠ ሥልጣን ነው፡፡ኤጰስ ቆጶስ έπίσκοπος ጠባቂ (እረኛ) መምህር ማለት ሲሆን፤ ትርጒሙ ከቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ተመርጠው በከፍተኛ ሥልጣነ ክህነት አገልግሎት እንዲሰጡ የተሾሙ የቤተ ክርስቲያን መጋቢዎችንና መሪዎችን፣ በሁሉም ጉዳይ ላይ ኀላፊነት ያላቸውን አበው ይመለከታል፡፡ በሂደትም በሥልጣነ ክህነት የሚወረስ የሐዋርያዊ ትውፊት apostolic succession  መሠረት ሁኗል፡፡ በሐዲስ ኪዳን έπίσκοπος የቤተ ክርስቲያን ዐቢይ ካህን (በአማርኛው ትርጉም ሽማግሌ፣ በጥንቱ ግእዝ ጠርዘ ቤጢ(ቴ)ል) በግሪኩ πρεσβύτεροι ፕሪስቢተሮስ፣  ከሚለውና በየሐዋ ሥራ 04፥@3 በየቤተ ክርስቲያኑ የተሾሙ አገልጋዮችን ከሚመለከተው ቃል ጋር ተናቦ ይገኛል፡፡ (የሐዋ.  01፥# እና 05፥@2)፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ጢሞቴዋስና ቲቶ የላካቸው መልእክታት ውስጥ የኤጲስ ቆጶስና ሥልጣን ከሹመት መስፈርቱና ከአገልግሎቱ ጋር ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡ (ቲቶ 1፥5)

 

የኤጴስ ቆጶስና ሥልጣን በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከፍተኛውን የመንፈሳዊ ሥልጣን በመያዝ እያደገ ትልቁን የቤተ ክርስቲያን መዋቅርን የሚወክል ሁኖል፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት ከተጠቀሱት መመሪያዎች በተጨማሪ በሐዋርያውያን አበው በተለይም በቅዱስ አግናጥዮስ የቀኖና ሥራዎች ውስጥ ኤጲስ ቆጶስና ወይም ጵጵስና በሰፊው ተብራርቶ ይገኛል፡፡ ኤጲስ ቆጶስና በቀኖና ትርጒም የሐዋርያት ሥልጣንና የቤተ ክርስቲያን ሉዓላዊነት መገለጫ ሆነ፣ በሥርዐተ አምልኮትም ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት የሚፈጽሙ ሲሆኑ በቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎት (ማለትም የመንፈሳዊ፣ የሀብት፣ የንብረት፣ የሰው ኀይል፣ የመሳሰሉት ሁሉ) በበላይነት የሚመሩ፣ የሚያስተዳድሩና የሚጠብቁ ናቸው፡፡ የኤጲስ ቆጶስና ሥልጣን ከአንዱ ትውልድ ወደ ቀጣዩ ተውልድ የሚተላለፍበት ቀኖናዊ ሥርዐትም ከሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት መውራረስ ጋር ተያይዞ የሚፈጸም ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማዕረገ ኤጲስ ቆጶስናም ከዚህ ሐዋርያዊ ትውፊት ሲያያዝ የመጣና ጥንታዊ፣ ሐዋርያዊና ቀኖናዊ መሠረት ያለው ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ጳጳስ በሚል የተገለጸው በቀኖና (ሥርዐት) መጻሕፍት ኤጲስ ቆጶስ የሚለውን ሥልጣን መሆኑን እገልጻለሁ፡፡

 

ሀ. የጵጵስና መዓርገ ክህነት በዘመነ አክሱም

 

ኢትዮጵያ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሕገ ልቡና እና በሕገ ኦሪት አምልኮተ እግዚአብሔር ይፈጸምባት የነበረች ሀገር ለመሆኗ በርካታ የእምነትና የታሪክ ምስክሮች ይገኛሉ፡፡ በመንግሥትና በእምነት ሉዓላዊነት ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ የነበራትን ገናናነትና ጥንካሬ ጠብቃ ወደ ሐዲስ ኪዳን ስትሻገር፣ እንደ ብሉይ ኪዳን ሁሉ በሐዲስ ኪዳን ታሪክም የመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ ትገኛለች፡፡ በሐዲስ ኪዳን ጌታችን በተወለደ ጊዜ ነገሥታትና ጠቢባን (ሰብአ ሰገል)  ለተወለደው ንጉሥ እጅ መንሻ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ሂደዋል ሊቃውንትም “የሳባና የዐረብ ነገሥታት እጅ መንሻን ያመጣሉ” (መዝ. &1፥9-0) የተባለውን ትንቢት በመያዝም ከእነዚህ ሰብአ ሰገል ከተባሉ ጠቢባን ነገሥታት አንዱ፣ የአክሱም ንጉሥ ባዜን ሲባል መቃብሩም በአክሱም እንደሚገኝ ይናገራሉ፡፡

 

ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ ድኅነት በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞትን በሞቱ ሽሮ፣ በሦስተኛው ቀን ተነሥቶ፣ በዐርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐርጎ፣ በኃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት በመላኩ ቤተ ክርስቲያን ለመላው ዓለም ስትበሠር፣ በመጀመሪያው የበዓለ ኃምሳ ቀን ቅዱስ ጴጥሮስ ተነሥቶ ሲሰብክ ትምህርቱን ከሰሙት ሰዎች ውስጥ ኢትዮጵያውያንም ነበሩ፡፡ (የሐዋ.ሥራ 2፥8-04) ይህንንም ክሥተት የቊስጥንጥንያ ፓትርያርክ የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በበዓለ ኃምሳ ስብከቱ “ኢትዮጵያውያን በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ተገኝተዋል የጴጥሮስንም ትምህርት ሰምተው ተረድተዉታል” በማለት ገልጾታል፡፡ (ዮሐንስ አፈወርቅ ትርጓሜ፥ ግብረ ሐዋርያት)

 

ከበዓለ ኃምሳ በኋላ ሐዋርያት ክርስትናን ይሰብኩ በነበረበት በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን፣ ኢትዮጵያ ንግሥት ህንደኬ መንግሥት ሀብት ኀላፊና ባለሟል፣ ለአምልኮተ እግዚአብሔር ወደ ኢየሩሳሌም ሂዶ በነበረበት ጊዜ፣ ክርስትናን ተቀብሏል፤ ይህም (በሐዋርያት ሥራ 8፥@6-$) ተዘግቦ ይገኛል፡፡ የሳባ ንግሥት ማክዳ ለብሉይ ኪዳን ሕገ ኦሪት ወደ ኢትዮጵያ መግባት ምክንያት እንደሆነች ሁሉ፣ የሕንደኬ ጃንደረባም ለክርስትና ወደ ኢትዮጵያ መግባትና መስፋፋት ምክንያት ሆነ፤ በ#4 ዓ.ም. በአክሱም ዘመነ መንግሥት ታማኙ የሕንደኬ መንግሥት አዛዥ ወንጌላዊው ፊልጶስን ከጎኔ ተቀመጥና አስተምረኝ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ፣ እነሆ ውኃ እንዳልጠመቅ ማን ይከለክለኛል ብሎ፣ በእምነት በመጠመቅ ሐዲስ ኪዳንን ተቀብሏል፡፡ ይህ የመንግሥት ባለሥልጣን ስለ ጌታችን “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ” በማለት የሰጠው የእምነት ምስክርነትም አንተ ብፁዕ ነህ ከተባለ ከቅዱስ ጴጥሮስ ቀጥሎ ሁለተኛው ምስክርነት ነው፡፡

 

በ3ኛው ና በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሓፊ የነበረው አውሳብዮስ፣ ኢትዮጵያዊው የንግሥት ሕንደኬ መንግሥት አዛዥ ከኢየሩሳሌም ውጭ የመጀመሪያው የክርስትና ፍሬ ነው፤ እርሱም ኢትዮጵያውያን ክርስትናን እንዲሰሙ ምክንያት ኖነ ኢትዮጵያውን ክርስትናን በመስማታቸውም በዳዊት ነቢይ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጃለች የተባለው ትንቢት ተፈጸመ ማለቱ አስቀድሞ የተገለጸ ሲሆን (Eusebius Pamphilius: Church History, Life of Constantine, Oration in Praise of Constantine፣ )፡፡ የወንጌላዊው ዮሐንስ ደቀመዝሙር ሊቁ ሔሬንዮስም ዘሊዎን በ)* ዓ/ም ስለግኖስቲክ መናፍቃን በጻፈበት ጽሑፉ ጃንደረባው ስምዖን ባኮስ አስቀድሞ አንድ አምላክ ወደተሰበከባት ኢትዮጵያ ሂዶ ራሱ ያመነውን ክርስትናን ሰበከ በማለት ተናግሯል (Adversus Haereses, Againest the Heresies: ቅጽ ሁለት መጽሐፉ 3፥02:8) የእስክንድርያው አርጊንስም ጃንደረባው ኢትዮጵያዊ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሁኖ በአክሱም አካባቢ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ማስተማሩ በታሪክ ተጽፏል የታሪክ ተመራማሪው ኤድዋርድ ኡሌንዶርፍ ኢትዮጵያና መጽሐፍ ቅዱስ በተባለው መጽሐፉ፤ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ በኢትዮጵያ ማስተማሩ በዘመኑ አግሊጶስ የተባለውን ገዥ ከነቤተሰቡ ማጥመቁን ጽፏል፣ ይኽው ታሪክ በምዕራቡ ዓለም በሰፊው የታወቀ ሲሆን በሰሜናዊ የኢጣልያ ክፍል ፒዛ በተባለችው ቦታ ባለች አንዲት ካቴድራል ውስጥ በዐሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን በነበሩ ታዋቂ ሠዓሊያን ተሥሎ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ሩፊኒስና ሶቅራጥስ የተባሉ የጥንት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ዕጣ ሲጣጣሉ ኢትዮጵያ ለሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ መድረሷን ወዲያውም ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ ፈጥኖ ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ ማስተማሩን፣ እጅግ ብዙ ተኣምራትን መሥራቱንና በመጨረሻም ከብዙ አገልግሎት በኋላ በዚያው ማረፉን ገልጸዋል፡፡ Matthew was allotted Ethiopia; (Socrates and  Sozomenus Ecclesiastical Histories p.57) ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የክርስትና ሃይማኖት ክርስትናን ከታማኙ የመንግሥት አዛዥ በሰሙና በሐዋርያው ማቴዎስ በተጠመቁ ኢትዮጵያውያንና በአክሱም ከተማ በሚኖሩ ክርስቲያኖች ተጠብቆ እስከ 4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ ቆይቷል፡፡

 

የአኵስም እጅግ የመጠቀ የውጭ ንግድ ዝነኛ የነበረው የውጊያ ስልት፣ እስከ ደቡብ ዐረብ የደረሰው ግዛቷ፤ በመላው ዓለም ትኩረት ያገኙና በዘመኑ ከነበሩት ኀያላን ነገሥታት አቻ ያደረጋት ብዙ ሁኔታ ነበር፡፡ ወደቦቿ ለመላው የምሥራቁና የምዕራቡ ዓለም የንግድ ቀጠና ዋና መሸጋገሪያዎች ነበሩ፡፡ በዘመኑ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የራስዋ ሳንቲም ያላት ብቸኛ መንግሥት ነበረች፤ ከዚህ የተነሣም በአክሱም ከ4)%1 ዓ/ም የቄልቄዶን ጉባኤ በፊት አንድነት የነበራቸው የሮም፣ የቊስጥንጥንያና የፋርስ ክርስቲያኖች ቤተ መቅደሶች እንደነበሩ ፕሮፌሰር ሞንሮሂ የተባሉ የታሪካዊ ቅርሶች ቊፈራ ባለሙያ በጻፉት መጽሐፍ ገልጸዋል፡፡ ፕሮፌሰር ዳቪድ ፊሊፕሰንም በሁለተኛውና ሦስተኛው ክፍለ ዘመን የተሠሩ የአብያተ ክርስቲያናት ፍራሾችና የክርስትና ንዋየ ቅድሳት በዘይላ፣ አዶሊስ፣ እንዲሁም በአክሱም አካባቢ መገኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ ዶክተር ስርግው ሐብለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የታሪክ ፓኖራማ በሚለው መጽሐፈ ክርስትና ከመጀመሪያው ጳጳስ ፍሬምናጦስ በፊት በኢትዮጵያ እንደነበር፣ የግሪክና ሮም ነጋዴዎችም በአክሱምና በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች አብያተ ክርስቲያናት እንደነበሯቸው ጽፈዋል፡፡ (Panoram of Ethiopian Church)

 

ለ. ከእስክንድርያ የተሾሙት የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

 

4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ መረጤዎስ የተባለ የግሪክ ፈላስፋ ልጆች  ፍሬምናጦስና ኤዴሲዮስ የተባሉ ሁለት በዜግነታቸው ግሪካውያን በትውልዳቸው ሶርያውያን የሆኑ ወጣቶች ወደ አክሱም ቤተ መንግሥት ደረሱ፡፡ የኗሪነት ጥገኛነት የሰጣቸው ንጉሠ ነገሥት አልዓሜዳም በቤተ መንግሥት እንዲቀመጡ ፈቀደላቸው፤ ወጣቶቹም በአክሱም የግእዝ ቋንቋን አጠኑ፡፡ ከሁለቱ አንዱ የሶርያ ክርስቲያን የነበረው ፍሬምናጦስ በቋንቋ ችሎታው ተመርጦ አልጋ ወራሾች የነበሩትን ኢዛናንና ሳይዛናን የውጭ ሀገር ቋንቋን ማስተማር ጀመረ፤ ንጉሡ ካረፈ በኋላ ኤዴሲዮስ ወደ ሀገሩ ሲመለስ፣ በአክሱም ያየውንና የሰማውን በዘመኑ ለነበረው መነኵሴ የታሪክ ጸሓፊ፣ ተርጓሚ፣ ለአቄላው ሩፊኖስ ተናገረ፡፡ ፍሬምናጦስ ግን በአክሱም ከሐዋርያት ጊዜ ጀምሮ የቆየ ክርስትና መኖሩን፣ ይሁንና ጳጳስ (ኤጲስ ቆጶስ) አለመኖሩን እንዲያሳውቅና ጳጳስ እንዲያስመጣ ከአክሱም ነገሥታት በተላከው መሠረት በቅርብ ለነበረው መንበረ ማርቆስ ቀርቦ ለቅዱስ አትናቴዎስ አሳወቀ፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስም በተነገረው ልዩ ዜና እጅግ ተደስቶ በእስክንድርያ የነበሩ ሊቃውንትንና ኤጲስ ቆጶሳትን ሰብስቦ በማማከር፣ በዕውቀቱና በቅድስናው የተማመኑበትን ፍሬምናጦስን ፈቃደኛነቱን በመጠየቅ፣ ሥርዐትንና ቀኖናን ሁሉ አስተምረው፣ አመንኩሰውና በጵጵስና መዓርግ ሹመው ወደ አክሱም ላኩት፡፡ (F. L. cross, A. Livingstone, the oxford dictionary of the Christian church (2nd ed. 1974)፡፡

 

አክሱም የሊቀ ኤጲስ ቆጶስ (ሊቀ ጳጳስ) መቀመጫ በመሆኗ የክርስቲያን መንግሥት ከተማ ሆነች፤ የሮም ንጉሥ ካልእ ቈስጠንጢኖስ የሰኮትራ ካህን የነበረ አርዮሳዊ ቴዎፍሎስን ወደ ኢትዮጵያ በመላክ አባ ፍሬምናጦስ አቡነ ሰላማ ወደ እስክንድርያ ሄዶ ሃይማኖቱን እንዲያስመረምር የተማሕፅኖ ደብዳቤ ለአብርሀ ወአጽብሐ ሐሳብ አቀረቡ፤ ኢትዮጵያውኑ ግን ለሮሙ ንጉሥ ለዳግማዊ ቈስጠንጢኖስም መልስ ነፈጉት፤ ይልቁንም የተላከውን ሰው ወደ ቤተ መንግሥት እንዳይደገባ ተደርጎ ነበር፡፡ ነገሥታቱ የኤጲስ ቆጶሱን ህልውና በጽናት ጠበቁ፡፡ ከቅዱስ አትናቴዎስና ለኒቅያ ጉባኤ ያላቸውን ታማኝነት በግልጽ አሳዩ፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስም ወደ መንበሩ ከተመለሰ በኋላ ኢትዮጵያውያኑ ነገሥታት ላሳዩት ጠንካራ አቋማቸው የምስጋና መልእክት ልኳል፡፡ የዚህ መንበር መገኝት ለሀገራችን የክርስትና እምነት መጠንከርና መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ ይህም በመላው የሮምና የግሪክ ግዛቶች በሚኖሩ ክርስቲያኖች ዘንድ ተሰማ፡፡ በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኮስመስ አዳዌ-ውቅያኖስ የተባለ አውሮፓዊ ተጓዥ፣ በኢዛና ዘመን የተጻፉ የቅዱሳት መጻሕፍት ጥቅሶች ያሉባቸው የድንጋይ ላይ ጽሑፎች በአክሱማውያን ወደቦች ዳርቻ ማግኘቱን ዘግቧል፤ በመግለጫውም አክሱም በዚያን ዘመን ኀያልና ጠንካራ የክርስቲያን መንግሥት የነበራት መሆኑን ገልጾአል፡፡ ኮስመስ ዐዳዌ ውቅያኖስ Kοσμaς Ιυδικοπλευστης (547-49 (Χρισςιτιαυ τοπογραψια (Christian Topography) በተባለው መጽሐፉ በስድስተኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ አክሱምን በጎበኘበት ወቅት ባለ ጒልላት የሆኑና ግዙፍ ቤተ መቅደሶች፣ በየማዕርጉ ያሉ የካህናት መኖሪያዎች፣ ከመዳብ የተሠሩ ሐውልቶች እንዳየ ገልጧል፤ በአርኬዎሎጅ ቊፈራ የጥንት ቤተ መቅደሶችና ቤተ መንግሥቶች ፍራሾች በብዛት ተገኝተዋል፡፡

 

ከዚህ ላይ ሊታለፍ የማይገባው ጉዳይ የሊቀ ጵጵስናው መንበር እንደተጠበቀ ሁኖ የኢትዮጵያ የክርስትና ማእከልነት በመላው ዓለም በመሰማቱ ከእስክንድርያ ውጭ በርካታ ቅዱሳን መነኮሳት ወደ አክሱም ይጎርፉ ነበር፤ ከእነዚህም የመጀመሪያው አባ ሊባኖስ ሲሆኑ፤ ጻድቁ የመሠረቱት ደብረ ሊባኖስ የተባለው ገዳም በሐም ይገኛል፤ ከዚያም ማኅበረ ደጕኤና ማኅበረ ጻድቃን በመቀጠልም የተስዐቱ ቅዱሳን (የዘጠኙ ቅዱሳን) መምጣት በስፋት ይታወቃል፤ የእነዚህ አባቶች መምጣትም ከመንበረ ጵጵስናው በተጨማሪ በኢትዮጵያ በርካታ ገዳማት እንዲቋቋሙ፣ ሥርዐተ ምንኵስና እንዲስፋፋ፣ በርካታ መጻሕፍት እንዲተረጎሙ፣ ስብከተ ወንጌል እንዲስፋፋ፣ ምክንያት ሆኗል ኢትዮጵያም ከሌላው የክርስትና ዓለም በሰፊው እንድትገናኝ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነበረው፡፡

 

በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በደቡብ ዐረብ ናግራን (የመን) የነበሩ ክርስቲያኖች፣ በአንድ አይሁዳዊና ሠራዊቱ ተወርረው ይደርስባቸው ከነበረ መከራ የታደጋቸውም፣ በዚሁ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ የነገሠው ንጉሠ ነገሥት ካሌብ ነበር፡፡ ጻድቁና ንጉሡ ካሌብ የመን-ናግራን ድረስ ሁለት ጊዜ ዘምቶ ክርስቲያኖችን በመታደጉና በነበረው ቅድስና፣ የሮማና የግሪክ ክርስቲያኖችን ጨምሮ በመላው ዓለም ክርስቲያኖች ዘንድ የቅድስና ማዕረግ የተሰጠው ጻድቅ ንጉሥ ነው፡፡ ንጉሡ ዘመቻውን እንደጨረሰ በየመን-ናግራን ለሚኖሩ ክርስቲያን ዜጎቹ አብያተ ክርስቲያናትን አንጾ፣ ካህነትን አሹሞ፣ ሃይማኖትን አጽንቷል፤ ከዘመቻው እንደተመለሰም ንግሥናውን ትቶ፣ መንግሥቱን ለልጁ ለገብረ መስቀል አስረክቦ፣ ዘውዱን ለሌላው ልጁ ሙሴ ወደ ኢየሩሳሌም በመላክ ቀራንዮ እንዲቀመጥለት አድርጎ መንኵሷል፡፡ ንጉሥ ካሌብም የመጀመሪያው መናኝ ንጉሥ ነው፡፡ በዚህ ጊዜም በኢትዮጵያና በእስክንድርያ የነበሩት መናብርት ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ ምክንያቱም የመጀመሪያውን ናግራን ክርስቲያኖች መልእክት ወደ ኢትዮጵያ የደረሰው በእስክድርያው ፓትርያርክ አማካኚነት ሲሆን መልእክቱን ለዐፄ ካሌብ ያደረሱት በአክሱም የነበሩት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ ይሁን እንጅ በንጉሡ የናግራን ዘመቻ ወቅት ስለነበሩት ሊቀ ጳጳስ ብዙም አልተጻፈም፡፡

 

ከስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ ከኢትዮጵያ ውጭ በተከሠቱ ልዩ ልዩ የሃይማኖትና የመንግሥት አስተዳደር ለውጦች አማካኝነት የአክሱም ንግድ፣ ሥልጣኔ፣ እና ኀያልነት እየተዳከመ ሄደ፡፡ በተለይ የኢኮኖሚ መዳከም ለሥልጣኔው ውድቀት ከፍተኛ አስተዋፅኦን አድርጓል፤ ድክመቱም እየቆየ አክሱምን ለከፍተኛ ዐመፅና ወረራ ዳረጋት፣ ከኵሽ ዘመን ጀምሮ ለዐራት ሺህ ዘመናት ያህል ተጠብቆ የቆየው የአኵስም ሥልጣኔ በዐርባ ዓመታት የዮዲት-ጒዲት ወረራ ከፍተኛ ጒዳት ደረሰበት፡፡ የሰሜን አፍሪካና የክርስቲያኑ መካከለኛ ምሥራቅም እንዲሁ በእስላም ዐረቦች ወረራ ሥር ወድቆ ነበር፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያና የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሰሜን አፍሪካ እስክንድርያም ሆነ ከክርስቲያን ሀገሮች ያላት ግንኙነት እየቀነሰና ችግር እየገጠመው ሲመጣ ጳጳሳትን ከእስክንድርያ የማስመጣት ሂደት ለብዙ ተደራራቢ ችግሮች ተጋለጠ፤ ግንኙነቱ ግን አልተቋረጠም ነበር፡፡

 

ሐ. የጵጵስና መንበር ታሪክ በዛጔ ሥርወ መንግሥት

 

በዘመነ አክሱም ማብቂያ በኢትዮጵያ የተከሠተው የጥፋቱ ዘመን የከፋና በርካታ ቅርሶች በእጅጉ ያወደመ ቢሆንም፣ የቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ ክብርና ታሪካዊነት ሳይጠፋ የሀገሪቱ ማእከል ወደ ዛጔ (ዘአገው) ተዛወረ፡፡ የዮዲት ጒዲት መነሣት ለበርካታ ቅርሶች መውደም፣ ለካህናትና ምእመናና እልቂት ምክንያት ከመሆኑ ባሻገር ከተፈጠሩት ችግሮች ውስጥ አንዱና ዋናው በሀገራችን የካህናት ቊጥር እየቀነሰ መምጣት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በተደጋጋሚ የኤጲስ ቆጶስነት መዓርገ ክህነት የሌላቸው ግን ኤጲስ ቆጶሳት ነን በማለት በራሳቸው ፈቃድ የመጡ ሐሰተኛ ሰዎች የፈጠሩት ችግር ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንድ ኤጲስ ቆጶስ ከእስክንድርያ ለማስመጣት የሚያስፈልገው ጊዜና ወጭ፣ እንዲሁም በመንገድ ላይ የሚገጥመውን ችግር ለመቋቋም የነበረው ሥጋት እንዲሁ ከፍተኛ ነበር፡፡

 

ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል በዐሥረኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ የእስክንድርያ ፓትርያርክ የነበሩት ሊቀ ጳጳስ ቆዝሞስ ሣልሳዊ አቡነ ጴጥሮስ የተባሉ አንድ ሊቃ ኤጲስ ቆጶስ ወደ ሀገራችን ልከው ነበር፡፡ በወቅቱ እንደተባለው ኤጲስ ቆጶስ ዘግይቶ ስለነበር በከፍተኛ ደስታ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡ ይሁን እንጂ በክፉ ሐሳብ የተመሩ ሌሉች ሁለት መነኮሳት ነን ባዮች በክፉ ሥራቸው ከአቡነ እንጦንስ ገዳም የተባረሩ አባ ሚናስና አባ ፊቅጦር የተባሉ ሰዎች ኤጲስ ቆጶሳት ነን በማለትና ወደ ሀገራችን በመምጣት ብዙ ችግር ፈጥረዋል፡፡ እውነተኛው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስም በማረፋቸውና ጉዳዩ በእስክንድርያ በኩል ተጣርቶ አቡነ ዳንኤል እስከሚላኩ ድረስ ብዙ በመዘግየቱ ዳግመኛ ተመሳሳይ የካህናት ቊጥር መቀነስና የመንፈሳዊው አገልግሎት መዳከም ችግር ተፈጠረ፡፡

 

በዚህ መሐል በእስክንድርያ አራት ፓትርያርኮች አልፈዋል፣ በመጨረሻም በንጉሠ ነገሥት ጃን ሥዩም ዘመነ መንግሥት (9)^5-0)5 ዓ/ም) የእስክንድርያ ኮፕቲክ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ፊሎቴዎስ በነበሩበት ወቅት ጳጳስ እንዲላክ ደብዳቤን በኑብያው ንጉሥ ጆርጅ (ጊዮርጊስ) አማካኝነት ልከው ነበር፡፡ በመልሱም ከብዙ ዓመታት በኋላ ከላይ የተጠቀሱት ኤጲስ ቆጶስ አቡነ ዳንኤል ተላኩ፡፡ በርግጥ ይህ የኤጴስ ቆጶሳትን ሹመት የማዘግየት ሂደት ከነበሩነት ችግሮች ውስጥ በግብጽ የነበሩት እስልምና አሚሮችና ሡልጣኖችም ሁኔታም የተወሰነ ነበር የኢትዮጵያ ነገሥታት ጳጳሳትን ለማስመጣት ስጦታ ሲልኩ ለአሚሮቹና ለሡልጣኖቹም ይልኩ ነበር፡፡ ሡልጣኖቹና ኤሚሮቹ በዚህ ጉዳዩ የነበራቸው አቋምም በንጉሠ ነገሥት ዐፄ ግርማ ሥዩም ዘመነ መንግሥት (0)&8-0)(2 ዓ/ም) በነበሩት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ ታሪክ ላይ ታይቷል፡፡ (ሉሌ መላኩ %1-^2፣ 09)(7 ዓ/ም)

 

ስለሆነም የዛጔ ነገሥታት በሀገራችን የነበረውን ችግር ለመቅረፍ ብዙ ጥረዋል፡፡ በተለይ ከቅዱሳን ነገሥታቱ አንዱ የነበሩት ንጉሥ ሐርቤ ገብረ ማርያም በ01)07-01)%7 ዓ/ም ቊጥሩ ለበዛው የኢትዮጵያ ክርስቲያን የራሳችን ኤጲስ ቆጶስ እንዲኖረን ለፓትያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ገብርኤል ሁለተኛ ጥያቄ አቀረቡ ጥያቄውን ለፓትርያርኩ እንዲያቀርቡላቸው በተጨማሪ ለሡልጣኑ መልእክት ላኩ፡፡ ምንም እንኳ ጥያቄው ለጊዜው ተቀባይነት ቢያገኝም፣ በኋላ ጥያቄው ርስ በርስ ተማካክረው ጥያቄውን ተቀባይነት እንዳያገኝ አደረጉት፡፡ ንጉሥ ሐርቤም ይህንን በማለታቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር፡፡ እሳቸውም ለጉዳዩ አማራጭ ለመፈለግ በኢየሩሳሌም በርካታ ገዳማትን በመመሥረት ከጥንት ጀምሮ ይኖሩ የነበሩ የኢትዮጵያ መነኮሳትን ድጋፍ መጠየቃቸው ሲታወስ ሁኔታው ያሰጋቸው ፓትርያርክ ገብርኤል ሚያዝያ ዐሥር በሚነበበው ስንክሣር ላይ “የኢትዮጵያ ሰዎች የራሳቸው ጳጳስ እንዲሾምላቸው በመጠየቃቸው እግዚአብሔር ተቈጥቶ ሦስት ዓመት ዝናብ ከለከላቸው በማለት እንዲጻፍ አድርገዋል” (የመጀመሪያው ፓትርያርክ፤ 0()%1፤ ገጽ 05)፡፡ በገድለ ቅዱስ ላሊበላም ጻድቁ ንጉሥ ዐፄ ገብረ ማርያም (ሐርቤ) ሰባት ጳጳሳትን እንዳሾሙ ተገልጧል፡፡

 

ከንጉሥ ሐርቤ በመቀጠልም የራሳችን ጳጳስ እንድንሾም ከመጠየቅ ባሻገር በኢትዮጵያ የነበሩት ሊቀ ጳጳስ ሜትሮጶሊጣን አቡነ ሚካኤልና በረዳታቸው ኤጲስ ቆጶስ አቡነ ሳሙኤል አማካኝነት ለአዲሲቱ ማእከልና በኢየሩሳሌም አምሳል ለተሠራች ደብረ ሮሓ ኤጲስ ቆጶስ አንዲሾሙ የተመረጡ መነኵሴ አቅርበው እንዲሾሙ ጠየቋቸው፡፡ በሂደትም ሜትሮፖሊታኑ አቡነ ሚካኤል በንግሥት መስቀል ክብራ ልመናና ጥያቄ የእስክንድርያ ፓትርያርክን አስፈቅደው ከሊቃውንት ተመርጠው የቀረቡትን ኢትዮጵያዊ መነኵሴ አቡነ ይርድዓ ሚካኤል በሚል ስም የደብረ ሮሐ ጳጳስ አድርገው እንዳሾሙ በቅዱስ ላሊበላ ገድል ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ በሂደትም አቡነ ሚካኤል ከሕዝቡና ከመንግሥት ጋር ባለመስማማታቸው ወደ አስክንድርያ ተመለሱ፡፡ በዚያም ስለገጠማቸው ሁኔታ ለፓትርያርኩ ሪፖርት አቅርበው ነበር፡፡ በተለይ አቡነ ሚካኤል አብረዋቸው ከነበሩት ረዳት ኤጲስ ቆጶስ ጋር በመሆን ስለመሾማቸው የሮሓ ኤጲስ ቆጶስ ለፓትርያርኩ ያቀረቡት ሪፖርት በፓትርያርኩ ዜና መዋዕል የተመዘገበ መሆኑ ነገሩ ምን ያህል እውነት እንደነበር ያረጋግጣል፡፡(Khater A., Burmester OHE, History of the Patriarich of Egyptian Church) በዛጒዌ ሥርወ መንግሥት የራሳችን ኤጴስ ቆጶስ እንዲኖረን ከፍተኛ ጥረቶች ተደርገዋል፣ እነዚህም በኋላ ለተደረጉት ስኬታማ ውጤቶች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነበራቸው፡፡

 

ሐ. ድኅረ ዛጔ የመንበረ ኤጲስ ቆጶስነት መዓርግ ታሪክ

 

በዘመናት ሄደት ምንም እንኳን ባይሳካም ከዛጒዌ ነገሥት በተጨማሪ ድኅረ ዛግዌ የተነሡ ነገሥታትም ተመሳሳይ ጥያቄን በማንሣት ሲሞክሩ መኖራቸው አልቀረም ፡፡ ለምሳሌ የሚጠቀሱትም ዐፄ እስክንድር ናቸው፡፡ ዐፄ እስክንድር በርከት ያሉ ጳጳሳት እንዲመጡላቸው የጠየቁ ሲሆን አያታቸውን ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን በመጥቀስ በሳቸው ዘመን ከመጡት ተጨማሪ እንዲመጡላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ ይህንንም ሁኔታ በዘመኑ በኢትዮጵያ ሲጓዝ የነበረው ፖርቱጋላዊው ጸሓፊ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ ገልጾታል፡፡ በመጨረሻም ለስኬት የቀረበውን እርምጃ የወሰዱት ንጉሥ ነገሥት ዐፄ ዮሐንስ አራተኛ (08)^3-08)*1 ዓ/ም) ነበሩ፡፡ ዐፄ ዮሐንስ አራት ሊቃነ ጳጳሳት ከእስክንድርያ አስመጡ፡፡ በርግጥ በመጀመሪያ የተጠየቀው አንድ ግብጻዊ ሊቀ ጳጳስና በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ኤጲስ ቆጶሳት ቢሆንም በኋላ ሁሉም ግብጻውያን እንዲሆን የእስክንድርያ ሲኖዶስ ስለወሰነ በዚሁ መሠረት በአራት አህጉረ ስብከት ተሰይመው መንፈሳዊ አገልግሎት የሚፈጽሙ ኤጰስ ቆጶሳት ተሹመው ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡ እነሱም በሐምሌ ወር 08)&3 ዓ/ም ኢትዮጵያ ደረሱ እነሱም ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በሊቀ ጳጳሳት ደረጃ ሆነው በመቀሌ ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ተቀምጠው የትግራይና የወሎ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ለሸዋ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ለቤጌምድር፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ለጎጃም ኤጲስ ቆጶስ እንዲሆኑ ተደረገ፡፡

 

ከእነዚህ ግብጻውያን ኤጲስ ቆጶሳት መካከል እስከ ዳግማዊ ምኒልክ መንግሥት ድረስ በሕይወት የቆዩት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ነበሩ፡፡ እሳቸውም አቡነ ጴጥሮስን ተክተው ሊቀ ጳጳስ ተደርገው የነበረ ቢሆንም፣ ኅዳር @5 ቀን 09)(1 ዓ/ም በማረፋቸው በምትካቸው የመጨረሻውና )0ኛው ግብፃዊ ኤጲስ ቆጶስ እንዲሾሙ በግብጽ በኩል ተወሰነ፡፡ ይሁን እንጅ አሁንም ኢትዮጵያውያን የራሳችን ኤጲስ ቆጶሳት ይሾሙልን የሚለው ጥያቄ በርትቶ በመጠየቁ በ09)@1 ዓ.ም በፍትሕ መንፈሳዊ የተቀመጠው ሥርዋጽ (ልብ ወለድ ቀኖና) ማለትም ኒቅያ $7 በሐሰት የኒቅያ ጉባኤ ውሳኔ አስመስለው በማስገባት “ወሰብአ ኢትዮጵያ ኢይሢሙ ላዕሌሆሙ ሊቀ ጳጳሳት እማእምራኒሆሙ ወኢበሥምረተ ርእሶሙ፡፡ እስመ ጳጳሶሙ ይከውን እምታሕተ እዴሁ ለበዓለ እስክንድርያ” “ኢትዮጵያውያን ከሊቃውንቶቻቸው መካከል ለራሳቸው ሊቀ ጳጳሳትን አይሹሙ ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ %” የሚለው የሐሰት ቀኖና ጥያቄ እየቀረበበት መሆኑን ሲረዱ በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት ለእስክንድርያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ አምስተኛ ጥያቄው ቀረበ፡፡ ሆኖም በሦስቱም የኢትዮጵያ ነገሥታት ማለትም በዐፄ ዮሐንስ፣ በዳግማዊ ምኒልክና በንግሥት ዘውዲቱ ዘመናት ሁሉ ፓትርያርክ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ አምስተኛ መልስ ሳይሰጡ አረፉ፣ ዕረፍታቸው በኢትዮጵያ እንደተሰማ ለኀዘን መግለጫ ሰባት ጊዜ መድፍ ተተኮሰ፣ ጥያቄውም ዘግይቶ በድጋሜ አዲስ ለተሸሙት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዮሐንስ በ09)@1 ዓ/ም ቀረበ፡፡

 

በመጨረሻም ግንቦት @3 ቀን 09)@1 ዓ/ም የተደረገው የግብጽ ሲኖዶስ በሰጠው ውሳኔ አንድ ግብጻዊ ሊቀ ጳጳስና በርከት ያሉ ኢትዮጵያውን ሊቃውንት ቆሞሳት በኤጲስ ቆጶስነት እንዲሾሙ ወሰነ፡፡ በውሳኔው መሠረትም አራት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ቆሞሳት መዓርገ ኤጲስ ቆጶስነትን ተሾሙ፡፡ እነርሱም ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጎጃምና የጎንደር፣ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል የምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የወሎ፣ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የትግሬና የሰሜን ኤጲስ ቆጶስ ነበሩ፡፡ አምስተኛ አቡነ ቄርሎስ ግብጻዊ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ ተሾሙ፣ በወቅቱ ወደ እስክንድርያ ሄደው መሾም ሲገባቸው በሕመም ምክንያት ሳይሄዱ ቀርተው የነበሩት ዕጨጌ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካይሮ መሄድ ስላልቻሉ ቀድሞ በተወሰነው መሠረት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ 09ኛ በ09)@2 ዓ/ም ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በመባል በአዲስ አበባ ታዕካ ነገሥት ባዕታ ለማርያም ገዳም ተሾሙ፡፡

 

ከእስክንድርያ የሚመጡት ሊቃነ ጳጳሳት በመልካሙም ይሁን በመጥፎ ጊዜ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ ከእስክንድርያ ወደ ኢትዮጵያ ተሹመው ከመጡ በኋላም የተለየ ችግር ካልገጠመ በስተቀር ወደ ግብጽ አይመለሱም፡፡ ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር የመጣውን ችግር ሁሉ የተካፈሉ ጳጳሳት ነበሩ ለምሳሌ በግራኝ ወረራ ጊዜ የነበሩት ግብጻዊ ሊቀ ጳጳስ ከሕዝቡ ጋር አብረው ተሠውተዋል፤ በኢየሱሳውያን የጥፋት ሚሲዎኖች ዘመን ግብጻዊው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ስምዖን ስለ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያውያን ጋር ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡ በአንጻሩ አልፎ አልፎ ከሊቃውንቱ ጋር ባለመስማማት ክህነትን አንሰጥም በማለታቸው አንዳንድ ቅዱሳን መነኮሳትን ለስደት ዳረጉ ጳጳሳት ሲኖሩ በተለይ @ኛው ክፍለ ዘመን በፋሽስት ጣሊያን ወረራ ጊዜ ከፋሽስት መሪዎች ጋር ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ወደ ሮም የሄዱት ኤጲስ ቆጶሳትም፣ ከተመለሱም በኋላ ኢትዮጵያን ለዘለዓለም አያሳየኝ ያሉት የመጨረሻው ግብጻዊ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስም ይታወሳሉ፡፡

 

በቅድስና ሕይወታቸው መጻሕፍትን በመተርጐምና ለምእመናን መልካም አርኣያ የነበሩ እንደ ሰላማ መተርጒም ብርሃነ አዜብ ዐይነት ኤጲስ ቆጶሳትንም ኢትዮጵያ በቅድስናቸውም በሊቅነታቸውም ትዘክራቸዋለች፡፡ ኢትዮጵያውያንም የራሳቸው መንበር መሥርተው በየዘመኑ ኤጲስ ቆጶስን ለማስመጣት ከፍተኛ መሥዋዕትነት ይከፍሉ ነበር፡፡ በመሆኑም በየዘመኑ በመልካም ሥራቸው ሃይማኖትን በመጠበቅ ልዩ አስተዋጽኦ ያደረጉ አበውን ስንዘክር የራሳችን መንበር እንዲኖረን፣ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው መሪዎች እንዲተዳደሩ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከቀደምት አኃት አብያተ ክርስቲያናት ጋር በአቻነት እንድትቀመጥ ያደረጉ በርካታ ነገሥታትን፣ ሊቃውንትን፣ ምእመናንና ካህናትን ሰናስብና ስንዘክር እንኖራለን፡፡ በተለይ በሃያኛው ክፍለ ዘመን ከጵጵስና መዓርግ አልፎ ኢትዮጵያ ሉዓላዊ የሆነ የራስዋ መንበረ ፓትርያርክ እንዲኖራት፣ የሀገራቸውን ክብርና ራስን በራስ የማስተዳደር ብቃት ለማረጋገጥ፣ የሕዝባቸውን አንድነት ለማጠናከር ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ግርማዊ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ በዘመናቸው ከነበሩት ሊቃውንት፣ ምእመናንና ካህናት ጋር በመሆን ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ትጋትና የተገኘው ወደ ኋላ የማይመለሱበት ስኬት ለዘለዓለም ሲዘከር ይኖራል፡፡ የዚህ ትጋት ውጤትም የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ሕዝቦች ስኬትም ተደርጎ ተቈጥሯል።

 

በታሪክ ሂደት የተጀመረው የጵጵስና ሢመት ጥያቂ ወደ ፕትርክና አድጎ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ በዓለ መንበር ሆነች፡፡ የመጀመሪያው ፓትርያርክም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ በእስክንድርያ ተሹመው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ መንበር በርካታ ጳጳሳትን ሾሙ፡፡ ሁለተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስም በሀገራቸው መዓርገ ፓትርያርክነትን በመሾም የመጀመሪያ ሁነዋል፣ ቅዱስነታቸወም እንዲሁ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ቆሞሳትን ጵጵስና ለመሾም በቅተዋል በዚህም ኢትዮጵያውን በራሳችን ፓትርያርክ፣ በሀገራችን መንበር፣ በራሳችን ሲኖዶስ ኤጲስ ቆጶሳት መሾምን ቀጥለዋል፡፡ እስከ አሁንም አምስት ቅዱሳን ፓትርያርኮች ብፁዕ ወቅዱስ ተብለው ተሹመው በርካታ ኤጲስ ቆጶሳትን ሹመዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ስድስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በመላው ዓለም የሰፋች በአፍሪካና በመላው ዓለም ባሉ አህጉረ ስብከት ላይ ፓትርያርክ በመሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ይመራሉ፡፡ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ሉዓላዊነት ይጠብቅልን፡፡

 

 

1. የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጰሳትና ቅዱሳን ፓትርያርች ስም ዝርዝር

 

ሀ/ የብፁዕ አቡነ ሰላማ ጵጵስና መንበር ወራስያን

 

 

  1. ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
  2. ብፁዕ አቡነ ሚናስ
  3. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 1ኛ
  4. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 1ኛ
  5. ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 1ኛ
  6. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ 1ኛ
  7. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል 1ኛ
  8. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ (2ኛ)
  9. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (2ኛ)
  10. ብፁዕ አቡነ ብፁዕ አቡነ ሚናስ
  11. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል 1ኛ
  12. ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ 1ኛ
  13. ብፁዕ አቡነ ስምዖን 1ኛ
  14. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 1ኛ
  15. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል 2ኛ
  16. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል 3ኛ
  17. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ 3ኛ
  18. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል 4ኛ
  19. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል 5ኛ
  20. ብፁዕ አቡነ ስምዖን 2ኛ
  21. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ 4ኛ
  22. ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 3ኛ
  23. ብፁዕ አቡነ አብርሃም
  24. ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
  25. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ 5ኛ
  26. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል
  27. ብፁዕ አቡነ ስምዖን
  28. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
  29. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 2ኛ
  30. ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ
  31. ብፁዕ አቡነ ፊቅጦር
  32. ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
  33. ብፁዕ አቡነ ቆዝሞስ
  34. ብፁዕ አቡነ ዮስጦስ
  35. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል
  36. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል 4ኛ
  37. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል
  38. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 3ኛ
  39. ብፁዕ አቡነ ዮሳብ
  40. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
  41. ብፁዕ አቡነ ቆዝሞስ
  42. ብፁዕ አቡነ ፊላታዎስ
  43. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
  44. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ 6ኛ
  45. ብፁዕ አቡነ ፊቅጦር
  46. ብፁዕ አቡነ ዮስጦስ
  47. ብፁዕ አቡነ በርማያ
  48. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል
  49. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል 5ኛ
  50. ብፁዕ አቡነ ሚናስ
  51. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ 7ኛ
  52. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ 8ኛ
  53. ብፁዕ አቡነ አብርሃም
  54. ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 3ኛ
  55. ብፁዕ አቡነ መቃርስ
  56. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል
  57. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 4ኛ
  58. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል
  59. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል 6ኛ
  60. ብፁዕ አቡነ የሐንስ 9ኛ
  61. ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
  62. ብፁዕ አቡነ ሚናስ
  63. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 5ኛ
  64. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል 11ኛ
  65. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል 7ኛ
  66. ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 4ኛ
  67. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል 8ኛ
  68. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 6ኛ
  69. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ 10ኛ
  70. ብፁዕ አቡነ ሚናስ 5ኛ
  71. ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 5ኛ
  72. ብፁዕ አቡነ ክርስቶዶሎ
  73. ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ
  74. ብፁዕ አቡነ ፊላታዎስ 2ኛ
  75. ብፁዕ አቡነ ሲንትዮስ
  76. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል 9ኛ
  77. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ 11ኛ
  78. ብፁዕ አቡነ ማካኤል 12ኛ
  79. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል 10ኛ
  80. ብፁዕ አቡነ በርቶሎሜዎስ
  81. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 7ኛ
  82. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ 12ኛ
  83. ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 6ኛ
  84. ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ 2ኛ
  85. ብፁዕ አቡነ ክላድያኑ
  86. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 5ኛ
  87. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 5ኛ
  88. ብፁዕ አቡነ ስምዖን 4ኛ
  89. ብፁዕ አቡነ ዮሳብ 2ኛ
  90. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል 13ኛ
  91. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 9ኛ
  92. ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 7ኛ
  93. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 6ኛ
  94. ብፁዕ አቡነ ስምዖን 5ኛ
  95. ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 7ኛ
  96. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል 14ኛ
  97. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ 13ኛ
  98. ብፁዕ አቡነ ክርስቶዶሎ 2ኛ
  99. ብፁዕ አቡነ ሲኖዳ
  100. ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 9ኛ
  101. ብፁዕ አቡነ ክርስቶዶሎ 3ኛ
  102. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ 14ኛ
  103. ብፁዕ አቡነ ዮሳብ 3ኛ
  104. ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ 2ኛ
  105. ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ 4ኛ
  106. ብፁዕ አቡነ ሰላማ 3ኛ
  107. ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ
  108. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 7ኛ
  109. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 10ኛ
  110. ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ 5ኛ

 

 

2. የቅዱሳን ፓትርያርኮች ዝርዝርና ታሪክ

 

ሀ) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ

 

ቀዳማዊ አቡነ ባስልዮስ (፲፰፻፹፬ዓ/ም (ሚዳ ሚካኤል) – ፲፱፻፷፫ ዓ/ም (አዲስ አበባ)) የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመጀመሪያው ፓትርያርክ ነበሩ። አቡነ ባስልዮስ ሲወለዱ የተሰጣቸው ስም ገብረ ጊዮርጊስ ሲሆን መጋቢት ፲፬ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ/ም ከደብተራ ወልደ ጻድቅ ሰሎሞንና ከወይዘሮ (በኋላ እማሆይ) ወለተማርያም ባዩ በሸዋ አውራጃ ሚዳ ሚካኤል ተወለዱ። ደብተራ ወልደ ጻድቅ የይፋት ቀውትጌስ ማርያም ተወላጅ ሲሆኑ፣ እማሆይ ወለተማርያም ደግሞ በመንዝ ላሎ ምድር የተወለዱ ነበር።

 

በሕፃንነታቸው ዘመን መንፈሳዊ ትምህርትን እየተማሩና የኮሶ ማርያምን ቤተ ክርስቲያን እያገለገሉ አድገዋል። አቡነ ባስልዮስ የዐሥራ አራት ዓመት ታዳጊ ወጣት እያሉ በ፲፰፻፺፱ ዓ/ም ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብተው ትምህርታቸውን ከመምህር ገብረ ኢየሱስ ሲከታተሉ ቆይተው በዚያው ገዳም መዓርገ ምንኵስናቸውን እስከተቀበሉበት ድረስ ለሦስት ዓመታት በረድእነት በእርድና አገልግለዋል።

 

በ፲፱፻፱ ዓ/ም በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ትእዛዝ በመናገሻ ግርጌ ለሚሠራው የማርያም ቤተ ክርስቲያን መነኮሳትና ባሕታውያን መኖሪያ ግንባታና እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳደር ረዳት እንዲሆኑ በተጠየቁት መሠረት፣ እያገለገሉና ቅዳሴ እያስተማሩ ለሦስት ዓመታት በመናገሻ ማርያም ደብር ቆዩ። እዚሁም ገዳም መምህር (አበ ምኔት) ሆነው ሲኖሩ የሐዋርያዊነት ሥራ በመሠማራት ቆዩ።

 

በቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ዘመን አባ ገብረ ጊዮርጊስ (አቡነ ባስልዮስ) የመናገሻ አምባ ማርያምን ገዳም እያስተዳደሩ ሳሉ፤ ከዚህም ሥልጣናቸው በተጨማሪ የአዲስ አበባ መንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መምህርነት በየካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ/ም ተሰጣቸው። ከዚያም ቀጥሎ መጋቢት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፭ዓ/ም በኢየሩሳሌም ያሉ የኢትዮጵያን ገዳማት በመንፈሳዊ መሪነት አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመው ለሁለት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ ወደአገራቸው ተመለሱ። የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓ/ም በአቡነ ተክለ ሃይማኖት መንበር፥ ዕጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ ዘነበረ በመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተብለው፥ አምሳ ዘጠነኛው ዕጨጌ ሆነው ተሾሙ። በዚሁ በዕጨጌነታቸው ዘመን የፋሺስት ወረራ ኢትዮጵያን ባጠቃ ጊዜ፣ በጦርነቱ ግምባር ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ተሰልፈው አብያተ ክርስቲያናትንና መጻሕፍትን የሚያቃጥል የምእመናንን ዘር የሚያጠፋ ጠላት መጥቷልና በሃይማኖት፤ በጸሎት፣ በምሕላ በርታ እያሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያጽናኑ ቆዩ። በጦርነቱም ጊዜ የተቀመጡበት በቅሎ በአረር ተመቶ እስኪወድቅና የለበሱትም ካባ አምስት ላይ በጥይት እስኪበሳሳ ድረስ ከንጉሠ ነገሥቱ ሳይለዩ የቈራጥነት ሥራ ሠርተዋል።

 

ሠራዊቱም ድል ህኖ በተፈታ ጊዜ ክንጉሠ ነገሥቱ ጋር በስደት ወደ ኢየሩሳሌም አቅንተው እስከ ድል ጊዜ ድረስ በስደት ቆይተዋል። በዚሁ በስደት ዘመናቸውም ሳሉ በርካታ ሐዋርያዊ መልእክቶችን ለአርበኞችም፤ ለሕዝቡም በመላክ ያጽናኑና ሃይማኖታዊ ቃለ ምዕዳንን  ያስተላልፉ ነበር። ንጉሠ ነገሥቱ በስደት ከነበሩበት ከ’ባዝ’ (ብሪታንያ) ፥ ጥር ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ/ም በጊዜው በስደት ኢየሩሳሌም ለነበሩት በእጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ አንድ ጽላትና ለአገልግሎት የሚበቁ አምስት መነኮሳትን ወደ እንግሊዝ አገር እንዲልኩላቸው በአባ ሐና ጅማ በላኩት ደብዳቤ መሠረት፣ ዛሬ ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም የተባለውን የመድኀኔ ዓለምን ጽላት ንጉሠ ነገሥቱ ወዳሉበት ባዝ የላኩት እሳቸው ነበሩ፡፡ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ፥ ጥር ፲፪ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ/ም በኢትዮጵያ ጠረፍ በኡም-ኢድላ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ-ዓላማ ሲተክሉ ዕጨጌ ገብረ ጊዮርጊስም አብረዋቸው ነበሩ። ከዚያም ንጉሠ ነገሥቱ ፤ በቡሬ፤ በደብረ ማርቆስ፤ በደብረ ሊባኖስ እና በእንጦጦ በኩል አድርገው ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ/ም አዲስ አበባ ሲገቡ ዕጨጌው ሳይለዩ አብረው ነበሩ።

 

ከድል በኋላም ከእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ጋር ፥ በጠላት ወረራ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት እንዲታደስና እንዲቀጥል ለማድረግ በየካቲት ወር ፲፱፻፴፬ ዓ/ም ንግግር ተጀመረ። ሆኖም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን የጵጵስና መዓርግ የመስጠትን ልምዳዊ መብቷን ለኢትዮጵያውያን አልለቅም በማለቷ በድርድሩ ስምምነት እስከተደረሰበት እስከ ሐምሌ ፲፯ ቀን ፲፱፻፵ ቆይቶ፤ በቀድሞው ሥልጣናቸው ሲያገለግሉ የቆዩት ዕጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ ፥ አቡነ ባስልዮስ ተብለው ከአቡነ ቴዎፍልስ፤ አቡነ ሚካኤል፤ አቡነ ያዕቆብ እና አቡነ ጢሞቴዎስ ጋር በእስክንድርያው ፓትርያርክ አቡነ ዮሳብ እጅ ተቀቡ። ግብጻዊው አቡነ ቄርሎስም ካይሮ ላይ ስላረፉ ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ጥር ፮ ቀን ፲፱፻፵፫ ዓ/ም ካይሮ ላይ በአቡነ ዮሳብ እጅ ተቀብተው የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሊቀ-ጳጳሳት ሆኑ። የፓትርያርኩንም ፈቃድ ካገኙ በኋላ በነሐሴ ወር ላይ አምስት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳትን ሾሙ። ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አመራር ላይ ብዙ ጊዜ የወሰደ ድርድር ከተደረገ በኋላ ስምምነት ተደርጎ፥ እሑድ፣ ሰኔ ፩ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓ/ም፤ ንጉሠ ነገሥቱ በተገኙበት ሥነ ሥርዐት ፓፓው አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ በብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ላይ የሢመቱን ሥርዐተ ጸሎት አድርሰው፤ የፓትርያርክነቱን ዘውድ ባርከው ደፉላቸው። ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አቡነ ባስልዮስ በግብጽ ፓትርያርክ እጅ በዚህ መዓርግ ሲቀቡ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ነው። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ እስከ ፲፱፻፶፩ ዓ/ም ድርሰ አርባ ሁለት አብያተ ክርስቲያናትን እንዳሠሩና ዐሥራ ሁለት ትምህርት ቤቶችንም እንዳለሙ አዲስ ዘመን ጋዜጣ፤ የፓትርያርኩን ሞት ተከትሎ ባወጣው የኀዘን ዘገባ ላይ ገልጾታል። ከነዚህም መሐል በተለይም በደብረ ጽጌ ያለውን የአብነት ትምህርት ቤት በግል ገንዘባቸው ነበር የሚያስተዳድሩት (አዲስ ዘመን፣ ጥቅምት 3/1963 ዓ.ም.)። ፓትርያርኩ በተወለዱ በ፸፱ ዓመት ዕድሜያቸው ጥቅምት ፪ ቀን ፲፱፻፷፫ ዓ/ም አርፈው ጥቅምት ፬ ቀን በደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ። አቡነ ቴዎፍሎስ ተተክተው ሁለተኛው ፓትርያርክ ሆኑ።

 

ለ) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዌፍሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ጎጃም በሚገኝው በዝነኛው ደብረ ኤልያስ አካባቢ ከአባታቸው ከአቶ ወልደ ማርያም ውቤ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ዘርትሁን አደላሁ ሚያዝያ ፲፮ ቀን ፲፱፻፪ ዓ/ም ተወለዱ። ሲወለዱም የተሰጣቸው ስም መልእክቱ ወልደ ማርያም ነበር። በልጅነታቸው ንባብ እና ዜማን በመሪ ጌታ ረዳኸኝ እና ግራ ጌታ ሣህሉ እዚያው በተወለዱበት አካባቢ ተምረዋል። ኋላ የቅኔ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ዝንባሌ ስላደረባቸው እዚያው ደብረ ኤልያስ ደብር መምህር ገብረ ሥላሴ በሚባሉ ሊቅ ሥር መማር ጀመሩ። በ፲፱፻፻፳ ዓ/ም ወደ አዲስ አበባ መጥተው ፍትሐ ነገሥትና አዲስ ኪዳንን ከመምህር ተክሌ (ንቡረ ዕድ በኋላ አቡነ ዮሐንስ) ሲከታተሉ ቆይተዋል። በዚህ ጊዜ የሃይማኖት ችግሮችን ለማወቅ ይፈልጉ እንደነበርና ሰፋ ያለ ዕውቀት እንደነበራቸው ይነገራል። በተጨማሪ የሃይማኖት ችግሮችን የሚመለከቱ መጻሕፍትን ሳይታክቱና ሳይሰለቹ ያነቡም ነበር። መልእክቱ ወልደ ማርያም በ፲፱፻፴ ዓ/ም ይህን ዓለም ንቀው ደብረ ሊባኖስ ገዳም መንኵሰው ገቡ። ከጠላት ወረራ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ቀሳውስቱ በዘመናዊ የሃይማኖት ትምህርት እንዲሠለጥኑ በነበራቸው ሐሳብ መሠረት ፳ የሚሆኑ ሊቃውንት መርጠው በቤተ መንግሥቱ አካባቢ እንዲሠለጥኑ አድርገዋል። ከነኚህም አንዱ አባ መልእክቱ ወልደ ማርያም ናቸው። ቀደም ብሎ በኢትዮጵያና በግብጽ በተደረገው ስምምነት መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ሲሾሙ ሊቀ ሥልጣናት መልእክቱ ወልደ ማርያም ለሹመት ከተመረጡት አምስት አባቶች አንዱ ሲሆኑ ወደግብጽ ተጉዘው በእስክንድርያው ፓትርያርክ ዳግማዊ አቡነ ዮሳብ እጅ በካይሮ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን እሑድ ሐምሌ ፲፰ ቀን ፲፱፻፵ ዓ/ም ሊቀ ሥልጣናት መልእክቱ “ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ” ተብለው የሐረርጌ ጳጳስ ሆኑ።

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወፓትርያርክ ዘ ኢትዮጵያ ካረፉ በኋላ ተከታዩን ፓትርያርክ ለመሾም በተደረገው ምርጫ በዕለቱ ተገኝተው የመረጡት ፻፵፮ አባላት ሲሆኑ ሦስቱ ዕጩዎች፦

 

፩) አቡነ ቴዎፍሎስ (የሐረርጌ ሊቀ ጳጳስ) – ፻፳፫ ድምፅ

፪) አቡነ ያዕቆብ (የወለጋ ሊቀ ጳጳስ) – ፰ ድምፅ

፫) አቡነ ጢሞቴዎስ (የሲዳሞ ሊቀ ጳጳስ) – ፲፫ ደምጽ አግኝተዋል።

 

በዚህም መሠረት የፓትርያርኩ ሥርዐተ ሢመት ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፷፫ ዓ/ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናውኗል። በ፲፱፻፷፮ ዓ/ም በኢትዮጵያ ወታደራዊው አብዮት ተለኩሶ ንጉሠ ነገሥቱ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ/ም ከሥልጣን ሲወርዱ የቤተ ክርስቲያኗ ንብረትም ወዲያው ተወረሰ። ፓትርያርኩንም ከሥልጣን ከማውረዱ በፊት ደርግ “የተሐድሶ ጉባኤ” የሚል ኮሚቴ አቋቁሞ በተለያየ ክፍል በሳቸው ላይ የማይገታ ዐመፅና አድማ ማነሣሣት ጀመረ። በዚህ ሁኔታ ለአንድ ዓመት ያህል በትዕግሥት ከቆዩ በኋላ በየካቲት ወር ፲፱፻፷፰ ዓ/ም የደርግ መንግሥት “ሲጠበቅ የቆየ ፍርድ” በሚል አዋጅ ከሥልጣን አውርዶ እሳቸውንና በመጨረሻ በእሳቸው የተሾሙትን ሦስት ጳጳሳት (አምስተኛው ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አንዱ ናቸው) አሰራቸው። በኋላም ሐምሌ ፯ ቀን ፲፱፻፸፩ ዓ/ም እኒህ የቤተ ክርስቲያን መሪ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወፓትርያርክ ዘ ኢትዮጵያ በደርግ እጅ ተገደሉ። ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፷፰ ዓ/ም ሦስተኛው ፓትርያርክ እንዲሾሙ አደረጉ።

 

ሐ) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት

 

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከጵጵስናቸው በፊት መጠሪያ ስማቸው አባ መልአኩ ሲሆን፤ የተወለዱት የንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ ታማኝ ወታደር ከነበሩት አባታቸው ከወታደር ወልደ ሚካኤል አዳሙ እና አባታቸው ለውትድርና ጎጃም ሄደው ካገቧቸው ባለቤታቸው ከወይዘሮ ዘውዲቱ ካሳ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ማኅደረ ማርያም ተብላ በምትታወቀው ገዳም አካባቢ ጋዥን በምትባል ቦታ ነው። አባታቸው ወታደር ወልደ ሚካኤል ባደረባቸው ሕመም ልጃቸው አባ መልአኩ ገና ሕፃን እያሉ በሞት ከዚህ ዓለም ተለዩ። በዚህም የተነሣ እናታቸው ወይዘሮ ዘውዲቱ ልጃቸው አባ መላኩ ትንሽ ጠንከር ሲሉ ይዘዋቸው ወደ ጎጃም ተመለሱ እና አባ መልአኩ እዚያው ጎጃም ውስጥ ዘርዘር ሚካኤል በሚባል አካባቢ ማደግ ጀመሩ። ነገር ግን የመጀመሪያ ትምህርታቸውን እንደጀመሩ እናታቸውም በሞት ከዚህ ዓለም ስለተለዩ ተመልሰው የአባታቸው ዘመዶች ወደሚገኙበት ቦታ ወደ ጎንደር ተመለሱ። ዘመዶቻቸውም እዚያው አካባቢ ታዋቂ መምህር ለነበሩት መሪጌታ ወርቅነህ ሰጧቸው። በዚያም ፊደል ከቈጠሩ በኋላ ወደ ደብረ ታቦር ተሻግረው እናቲቱ ማርያም በተባለችው ደብር ያስተምሩ ከነበሩት አለቃ ቀለመ ወርቅ ዘንድ ሄደው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀቁ። ከዚህም በኋላ ወደ አዲስ አበባ መጥተው በወቅቱ የኢትዮጵያ ጳጳስ ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ መዓርገ ዲቁናን ተቀበሉ። ከዚያም ወደ ማኅደረ ማርያም ተመልሰው በዲቁና ሲያገለግሉ ቆዩ።

 

አባ መልአኩ ሕይወታቸው በቤተ ክርስቲያን ትምህርት አጎልምሰው በትሕርምትና እግዚአብሔርን በሕይወታቸው ሁሉ ለማገልገል በመወሰን ከጓደኞቻቸው ጋር ቅኔ ለመማር ወደ ጎጃም ይሄዳሉ። በዚያም በእናታቸው ሀገር አጠገብ ወደሚገኘውና የረዝ ሚካኤል ወደተባለው ቦታ መምህር ልሳነ ወርቅ ከተባሉ መምህር ዘንድ ቅኔንና ዜማን ለስምንት ዓመታት ያህል ተማሩ። የዜማውንና የቅኔውን ትምህርት በሚገባ ካጠናቀቁ በኋላ በተማርኩት ደግሞ ጥቂት ላገልግል በማለት ወደ ደብረ ታቦር ሄዱ። ይሁን እንጂ ወዲያውኑ የኢጣልያ ፋሺስት ጦር ኢትዮጵያን በግፍ በመውረሩ እንዳሰቡት በሰላም ሊያገለግሉ አልቻሉም፡፡ በመሆኑም የአገልግሎት አሳባቸውን በመተው ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደው በብሕትውና እየኖሩ ለመማር ወሰኑ፡፡ ይህንን ውሳኔያቸውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚሔዱበትን ሀገር ለመወሰን ሲያወጡ ሲያወርዱ እና የጓደኛቻቸውን ምክር ሲጠይቁ አንድ ጓደኛቸው በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ አካባቢ አጎቱ በመንግሥት ሥራ ተሰማርቶ እንደሚኖርና አካባቢው በ03ኛው ክፍለ ዘመን ጻድቁ አቡነ ተከለ ሃይማኖት የተጋደሉበት፣ እንደ ደብረ መንክራት አቡነ ተከለ ሃይማኖት ዐይነት ታላላቅ ገዳማት እንዳሉበት፣ ቦታው በጥምቀት የቅድስት ሥላሴን ልጅነት ያላገኙ ሰዎች የሚበዙበት በመሆኑ ለብሕትውናና ለአገልግሎት የሚመች መሆኑን መከራቸው@ አብረው ከሄዱ ለጊዜው አጎቱ ቤት አንደሚያርፉም ይነግራቸዋል፡፡ ቅዱስነታቸውም የጓደኛቸውን አሳብ ተቀብለው በ1926 ዓ.ም ሁለቱም ወደ ወላይታ ጒዞአቸውን ጀመሩ፡፡

 

አድካሚ ከሆነው ከብዙ ቀናት የእግር ጒዞ በኋላ ወላይታ ደርሰው ከጓደኛቸው አጎት ቤት ዐረፉ፡፡ አካባቢውን እስከሚላመዱ በእንግድነት ከቆዩ በኋላም ዝናው ከጎንደር ስቦ ወዳስመጣቸው ደብረ መንከራት አቡነ ተከለ ሃይማኖት ገዳም ገቡ፡፡ እግዚአብሔር እንደነ ጻድቁ አቡነ ዜና ማርቆስና ጻድቁ አቡነ ተከለ ሃይማኖት በአካባቢው ሥራ እንዲሠሩ መርጧቸዋልና ወደ ገዳሙ ሲገቡ በቦታው ረዘም ላለ ጊዜ የቆዩትን አለቃ ደስታ የተባሉትን ባሕታዊ አገኙ፡፡ ከእሳቸውም ጋር በአንድ በኣት ተወስነው መኖር ጀመሩ፡፡ ባሕታዊ አባ መላኩ በወላይታ እየተዘዋወሩ በሚያስተምሩት ወቅት በደብረ መንክራት ገብተው ጥቂት ከቆዩ በኋላ የገዳሙ አበምኔት ከነበሩት መምህር ወልደ ኢየሱስ የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጓሜ በተለይም የማር ይስሐቅንና የመጻሕፍተ ሊቃውንትን ትርጓሜ በጥልቀት ተማሩ፡፡ ቅዱስነታቸው ከመማር ጋር በነበራቸው የቁም ጽሕፈት ችሎታ በመምህራቸው ታዝዘው ቅዱሳት መጻሕፍትን እየጻፉ ለገዳሙ ማኅበር እንዲዳረስ አድርገዋል፡፡ በዚህ ዐይነት የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ሲመረምሩና ሥርዐተ ገዳምን ሲያጠኑ ከቆዩ በኋላ በዚያው መዓርገ ምንኵስናን ተቀበሉ፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከግብጻዊው ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ መዓርገ ቅስናን ተቀብለው ወደ በኣታቸው ተመለሱ፡፡

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተከለ ሃይማኖት ወደ ገዳማቸው ከተመለሱ በኋላ በጾም በጸሎት፣ በስጊድና በትሕርምት በገድልና በልዩ ልዩ ትሩፋት ተወስነው እስከ 1940 ዓ.ም ድረስ በኣታቸውን አጽንተው ቆዩ፡፡ ይህም የተባሕትዎ ጊዜ ከፈጣሪያቸው ከእግዚአብሔር ልዩ ጸጋና በረከት የተቀበሉበትና ለወደፊት ዓላማቸው ሁሉ ልምድ ያገኙበት ወቅት ነበር፡፡ በዚህ ዐይነት ለዓመታት በፍጹም ትሕርምት እና ተጋድሎ እንደ አባቶቻቸው እግዚአብሔርን በጸሎት ከለመኑ በኋላ በ1940 ዓ.ም በኣታቸውን በዚያው ገዳም አድርገው በአውራጃው ልዩ ልዩ ቦታዎች በመዘዋወር ማስተማር ጀመሩ፡፡ ቅዱስነታቸው በሚያስደንቅ ሁኔታ በአውራጃው ውስጥ በሚገኙት ሰባት ወረዳዎች እየተዘዋወሩ ሲያስተምሩ ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ዘንድ በአካባቢው እንዲንቀሳቀሱ የፈቃድ ደብዳቤ ከማግኘታቸው በስተቀር የተቈረጠላቸው ደመወዝ የተሰፈረላቸው እህል አልነበረም፡፡ በቅዱስነታቸው ትምህርት ከሦስት መቶ ሺህ በላይ የሆኑ አማንያን አምነው እንደ ተጠመቁና የክርስቶስ ተከታዮች እንደ ሆኑ ይነገራል፡፡ በጣዕመ ስብከታቸው ይህንን ያህል ምእመን ካፈሩም በኋላ በቤተ መንግሥቱ ዕውቅና የነበረውንና በአካባቢው የሚገኙ ሰባት አውራጃዎች ተወካዮችን በአባልነት የያዘ ‘ የመገበሪያ ቦርድ ‘ የተሰኘ አካል በማቋቋም የአካባቢው ሕዝቦች ገንዘብ እንዲያዋጡ በማገድረግ፣ ከዚህም ጋር የአካባቢውን የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማፋጠንን ቀዳሚ ዓላማው ያደረገውን ‘ብርሃነ ሕይወት’ የተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት አቋቁመው በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ተቋማት አሠርተዋል።

 

በዚህ ዐይነት እየተንቀሳቀሱ እያሉ ደርግ ሁለተኛውን የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን አላግባብ አሰረ፡፡ ሌላ ፓትርያርክም እንዲመረጥ አዘዘ። አስመራጭ ኮሚቴ ተቋቋሞ ከየክፍሉ ለፓትርያርክነት እንዲመረጡ ዕጩ የሚሆኑ አባቶች እንዲጠቈሙ አደረገ። በዚህም ጥቈማ አባ መላኩ ሳያስቡት በእግዚአብሔር ፈቃድ አንዱ ዕጩ ሆነው ተጠቈሙ። በመጨረሻም የማጣሪያ ምርጫ አድርጎ ከተጠቈሙት አባቶች ውስጥ አምስቱ ብቻ እንዲቀሩ ካደረገ በኋላ ከ565 ወረዳዎች ሁለት ሁለት ተወካዮች አንዲላኩና በአምስቱ አባቶች ላያ የፓትርያርክነት ምርጫ ድምፅ እንዲሠጡ ጥሪ አደረገ። እነኝህም አምስቱ ዕጩዎች የሚከተሉት ነበሩ።

 

1. አቡነ እንድርያስ (በወቅቱ የቤጌምድርና ሰሜን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

2. አቡነ ሰላማ (በወቅቱ የጋሞ ጎፋ ሊቀ ጳጳስ)

3. አባ ተወልደ ብርሃን ወልደ ሥላሴ (በወቅቱ የደብረ ቢዘን ገዳም አበምኔት)

4. አባ ዮሐንስ ከሃሊ (ከኢየሩሳሌም)

5. አባ መላኩ ወ/ሚካኤል (በደብረ መንክራት ተክለ ሃይማኖት ገዳም)

 

ባላሰቡት ሁኔታ ለዚህ ኀላፊነት የታጩት አባ መልአኩም መንበሩ ለእኔ አይገባኝም ብለው ተቃውመው እንደነበር ይነገራል። በዚህም የተነሣ ቅዱስነታቸው ቤተ ክህነት ውስጥ ተቀምጠው በዘበኛ እንዲጠበቁ ተደርጎ እንደነበር ይነገራል። በአምስቱ ዕጩዎች ላይ ድምፅ እንዲሰጡ ከየወረዳው በተገኙ 9)9 ወኪሎች በተሰጠ ድምፅ መሠረት አባ መልአኩ 317 ድምፅ በማግኘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሦስተኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመረጡ። ሹመታቸውም እውን ይሆን ዘንድ ሐምሌ 01 ቀን 09)^8 ዓ.ም መዓርገ ጵጵስና ተቀበሉ። በኋላም ነሐሴ @3 ቀን 09)^8 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ አባ ተክለ ሃይማኖት ሣልሳዊ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ’ ተብለው ተሾሙ።

 

መ) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በቀድሞው አጠራር ጎንደር ክፍለ ሀገር በአሁኑ በደቡብ ጎንደር ዞን በአንዳቤት ወረዳ ልዩ ስሙ አረጊት ኪዳነ ምሕረት ገዳም አካባቢ ከአባታቸው ከብላታ ፈንታ ተሰማና ከእናታቸው ከወ/ሮ ለምለም ገሠሠ በ09)# ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜ በአካባቢው ከሚገኙት ከመሪጌታ ላቀው ንባብና ዳዊት ከተማሩ በኋላ በአጭቃን ኪዳነ ምሕረት ደብር ምዕራፍና ጾመ ድጓ ተምረዋል፡፡ ከዚያም ትምህርታቸውን ለማስፋፋት ወደ ጎጃም ክፍለ ሀገር ሄደው ጐንጂ ቴዎድሮስ ገዳም ከመሪጌታ ወርቁ ሁለት ዓመት፤ ወደ ዋሸራ መንክር ኀይላ ቅድስት ማርያም በመሄድ ስመ ጥር ከነበሩት ከታላቁ ሊቅ ከመሪጌታ ማዕበል ፈንቴ ሁለት ዓመት፣ በጠቅላላው አራት ዓመት በመማር የቅኔ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡

 

ከዚያም ወደ ትውልድ ሀገራቸው ተመልሰው በደብረ ታቦር አውራጃ ልዩ ስሙ አጋጥ ጽዮን ደብር ከመሪጌታ ሙጬ ላቀ የምዕራፍ፣ የጾመ ድጓና የድጓ ትምህርታቸውን አጠናቅቀዋል፡፡ ቅዱስነታቸው በነበራቸው ከፍተኛ የትምህርት ፍላጎት ወደ አቋቋም ቤት በመግባት መነጒዘር ኢየሱስ በሚባለው ደብር ከመሪጌታ ሚናስ ለሁለት ዓመታት ያህል የአቋቋም ትምህርታቸውን ተምረዋል፡፡ በመቀጠል ቁት አቡነ አረጋዊ ደብር ከመሪጌታ ውብ አገኝ ዝማሬ መዋሥዕት ተምረዋል፡፡ ከዚያም ከጥንቱ መምህራቸው መሪጌታ ሙጬ ላቀ ዘንድ እንደገና የድጓ ትምህርታቸውን በመቀጠል ጽፈውና አመልክተው ከጨረሱ በኋላ፤ በቀድሞ አጠራር በጋይንት አውራጃ በታች ጋይንት ወረዳ በምትገኘው ቅድስት ቤተልሔም የድጓ ትምህርት ማስመስከሪያ ወደ ሆነችው በመሄድ ለአራት ዓመታት ቆይተው የድጓ ትምህርታቸውን በሚገባ አጠናቀውና አስመስክረው በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱስነታቸው  ከነበራቸው የትምህርት ፍላጎት የተነሣ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት  በአዲስ አበባ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በቅዳሴና በማሕሌት እያገለገሉ ትርጓሜ ሐዲሳትንና አቡሻኸርን ተምረዋል፡፡ ዘመናዊ ትምህርታቸውን በቅድስት ሥላሴ ትምህርት ቤት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ ተከታትለዋል፡፡ በተጨማሪም ለመምህራን የተዘጋጀውን የስብከት ዘዴ ትምህርት ለሁለት ዓመታት ተምረው በሠርተፊኬት ተመርቀዋል፡፡

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በ09)$4 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል የጎንደር ክፍለ ሀገር ሊቀ ጳጳስ መዓርገ ዲቁና ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስነታቸው ሥርዐተ ምንኵስናን ከመምህርነት ጋር አጣምሮ ለመያዝ ያላቸው መንፈሳዊ ፍላጎት ከፍ ያለ ስለነበረና ቤተ ክርስቲያንን በሙሉ ኀይልና በሙሉ ጊዜ ለማገልገል የምንኲስና ሕይወት የበለጠ ተመራጭ መሆኑን ስለ አመኑበት፤ በደሴተ ጣና ካሉት ጥንታውያን ገዳማት አንዱ በሆነው በምኔተ አቡነ ሂሩተ አምላክ ዳጋ ቅዱስ እስጢፋኖስ አንድነት ገዳም ከመምህር ኀይለ ማርያም በ09)^1 ዓ.ም መዓርገ ምንኲስናን ፤ በዚሁ ዓ.ም. ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ የቅስና መዓርግን ተቀብለዋል፡፡

 

ቅዱስነታቸው በነበራቸው ከፍተኛ መንፈሳዊ ሕይወት በባሕር ዳር አውራጃ ልዩ ስሙ በጋሾላ አቡነ ተጠምቀ መድኅን አንድነት ገዳም ገብተው የገዳሙን ሥርዐት እያጠኑ ለገዳማውያን በታዘዘው መሠረት በተግባረ እድ፣ በትምህርት፣ በጸሎተ ማኅበር፣ ለእንግዶች ማረፊያ ቤት በመሥራትና ዐቅመ ደካሞችን በመርዳት ለሁለት ዓመታት ገዳሙን አገልግለዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ከፍተኛ መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን በዋናነት የጀመሩት በማስተማር ሲሆን፤ የድጓ ትምህርታቸውንም ካስመሰከሩ በኋላ ወደ ተወለዱበት ገዳም ሄደው ለሰባት ዓመታት ያህል ድጓ አስተምረዋል፡፡ በተጨማሪም በአዲስ አበባ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በቅዳሴና በማሕሌት ሰፊ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡ የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ ሁነው ተሹመው በአስተዳደሩበት ወቅትም ለቤተ ክርስቲያኑ አገልጋዮች መኖሪያ ቤት፣ ለሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችም የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከነሙሉ ድርጅቱ አሠርተው ቤተ ክርስቲያኑ የነበረበትን ችግር እንዲቃለል አድርገዋል፡፡ተጀምሮ የነበረውም የቤተ ክርስቲያኑ ሕንጻ እንዲጠናቀቅና በአካባቢ የሚገኙ ምእመናንም በሰበካ ጉባኤ ተደራጅተው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ባላቸው በቂ የቤተ ክርስቲያን ዕውቀትና ባሳዩት የመንፈሳዊ አገልግሎት ሥራ ወዳድነት ቤተ ክርስቲያናችን ጥር 03 ቀን 1971 ዓ.ም. ባደረገችው የ03 ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ በቅዱስ ሲኖዶስ፣ በካህናትና በምእመናን በከፍተኛ ድምፅ ተመርጠው የኡጋዴን አውራጃ ኤጲስ ቆጶስ ሁነው ተሾመዋል፡፡ በዚህም አውራጃ፡- በሱማሌ ጦርነት ፈርሰው የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት በማሠራትና በማሳደስ፣ በጦርነቱ ምክንያት የተሸበረውንና የተደናገጠውን ሕዝብ በማጽናናት በሃይማኖቱ እንዲጸና፣ ሀገሩን እንዲወድ በማስተማር ሐዋርያዋ ተልእኳቸውን ፈጽመዋል፡፡

 

ከዚያም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ በቀድሞ አጠራር ወደ ጎንደር ክፍለ ሀገር ተዛውረው የጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው ተመድበዋል። ቅዱስነታቸው የጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሁነው ሲመደቡ ሀገረ ስብከቱ የራሱ የአስተዳደር ቢሮ ሕንጻ አልነበረውም። የሊቀ ጳጳሱ መኖሪያ አርጅቶ ነበር። በሊቀ ጵጵስና ዘመናቸው የመንበረ ጵጵስናውን ሕንጻ ከማሳደሳቸውም በተጨማሪ ከዐሥራ ሰባት ክፍሎች በላይና አንድ ሁለገብ አዳራሽ አስገንብተው መንበረ ጵጵስናው በክፍለ ሀገሩ ከሚገኙት የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የላቀ ደረጃ እንዲኖረው አድርገዋል፡፡ በወቅቱ እንዲህ ያለ የተሟላ መንፈሳዊ አስተዳደር ያለው ሀገረ ስብከት ስላልነበረ የእርሳቸው ሥራ በታላቅ አክብሮት ይነሣ ነበር። ቅዱስነታቸው የጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ ባስመዘገቡት የሥራ ብቃት አምስት ጊዜ በብሔራዊ ደረጃ ከ09)&5 እስከ 09)&9 ዓ.ም. ድረስ በተከታታይ በአንደኛ ደረጃ ተሸልመዋል። ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያናችን ካፈራቻቸው ሊቃውንት አንዱ ይልቁንም ትልቅ ጥረትና ትዕግሥት የሚጠይቀውን የድጓ ሊቅና መምህር በመሆናቸው፤ በየቦታው ወድቀው ያለ ደጋፊ የነበሩትን የአብነት መምህራንን በማሰባሰብ ከፍተኛ የሆነ የአብነት ትምህርት ቤት መስፋፋት እንዲከናወን አድርገዋል። በመሆኑም በክፍለ ሀገሩ ያሉ የአብነት መምህራን የወር ደመወዝ እንዲያገኙ በማድረግ ሊቃውንቱን አበረታተዋል፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶችና የሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉ የአራቱ ጉባኤ መምህራንና ተማሪዎች በቂ ቀለብ እንዲያገኙ አድርገዋል።

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ለ12 ዓመታት በፓትርያርክነት ሲመሩ የቆዩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ዐረፍተ ዘመን ገቶአቸው ግንቦት @8 ቀን 09)* ዓ.ም መለየታቸውን ተከትሎ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርእሰ መንበር ለመሰየም ባደረገው ምርጫ ነሐሴ @2 ቀን 09)* ዓ.ም. በዕጩነት ከቀረቡት ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት መካከል በቅዱስ ሲኖዶስ የተዘጋጁትን መመዘኛዎች በማሟላትና ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በመሆን ተመርጠዋል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ የአጠቃላይ መንፈሳዊ ሰበካ ጉባኤ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከየሀገረ ስብከቱ ሰበካ ጉባኤ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ተወካዮች እና ከቀደሙት የአንድነት ገዳማትና አድባራት ተወካዮች በድምሩ )9 መራጮች ሲሆኑ፤ ከእነዚህ መካከል )1 ድምፅ አግኝተው በከፍተኛ ድምፅ በመመረጥ ነሐሴ @9 ቀን 09)*ዓ.ም. በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው ተሹመዋል፡፡

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በ09)*3 ዓ.ም. በሀገራችን ኢትዮጵያ ከተደረገው የመንግሥት ለውጥ ጋር በተያያዘ ተሰድደው ኖረዋል፡፡ በመቀጠልም ቅዱስነታቸው በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ሰሜን አሜሪካ ያቀኑት ወደ ዋሺንግተን ሲያትል ነበር። ከዚያም በካናዳ፣ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በአትላንታ፣ በዴንቨርና በኦሃዮ ግዛቶች ማረፊያቸውን እያደረጉ በመላው ሰሜን አሜሪካ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን አከናውነዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ከሀገራቸው ቅድስት ኢትዮጵያና ሕዝባቸው ለሃያ ስድስት ዓመታት ተለይተው በሐዋርያዊ አገልግሎትና በጸሎት ቆይተዋል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በተደጋጋሚ ብዙ ጥረቶች ሲያደርግ ቆይቶ ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ነውና ሐምሌ @5 ቀን @)0 ዓ.ም. ክቡር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር በሆኑበት ወቅት  ቅዱስነታቸውን በስደት ከነበሩት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ወደ አገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አንድነትም እውን ሆኗል፡፡ በመንበረ ፕትርክናቸው ሆነው ከዚህ ዓለም ድካም እስካረፉበት ድረስ ስለሀገራቸው፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን፣ እና ስለ ሕዝብ አንድነት ሲጸልዩ ሲባርኩ ቆይተዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ባደረባቸው ሕመም በጸሎትና፣  በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ በሚዘከርበት ዕለት የካቲት @5 ቀን @)04 ዓ.ም ከዚህ  ዓለም ድካም ወደማያልፈው ዓለም ተሻግረዋል፡፡

 

ሠ) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ

 

አምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ (ዶ/ር) አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ተብለው ይጠሩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባታችን ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ በትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን በዐድዋ አውራጃ በአባ ገሪማ ገዳም አጥቢያ ኅዳር 3 ቀን 09)@8 ዓ.ም እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከመልካም፣ ክርስቲያን ቤተሰብ ተወለዱ፡፡ ከ6 ዓመት ዕድሜአቸው ጀምሮ በአባ ገሪማ ገዳም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እምነትነና ሥርዐት በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሥርዐተ ገዳማት  አኗኗር እያጠኑ አደጉ፡፡ ከአባ ገሪማ ገዳም ሌላ በተምቤን ውስጥ በጭኽ እና በአባ ኀደራ ገዳማት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርትን አጠናቅቀው በብፁዕ አቡነ ማርቆስ የዲቁና ቀጥሎም በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የቅስና መዓርግ ተቀብለዋል፡፡ በኋላም ከሕፃንነታቸው ጀምረው እያገለገሉና እየተማሩ በአደጉበት በአባ ገሪማ ገዳም መንኵሰዋል፡፡ በ09)$8 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው በሁለተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፈቃድ አዲስ አበባ በሚገኝው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተው ትምህርታቸውን በአዳሪነት ተከታትለዋል፡፡ በኮሌጁም ከሃይማኖት ትምህርት በተጨማሪ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሚገባ አጠናቅቀዋል፡፡

 

ቅዱስነታቸው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ዘንድ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን የአንድምታ ትርጓሜ (ኮሜንታሪ)፣ ጸዋትወ ዜማ፣ የግእዝና አማርኛ ሰዋስው ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተምረዋል@ የኮሌጁ መረጃ እንደሚጠቁመው  የቅዱስነታቸው የትምህርት ደረጃ በክፍል ከ1-5ኛ እንደነበረ ነው፡፡ ቅዱስነታቸው ተማሪ በነበሩበት ጊዜ በትምህርት ውጤት በሚያሳዩት ከፍተኛ ችሎታ ከቀድሞው ንጉሠ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ ከክፍል 1ኛ በመውጣት 3 ጊዜ ሽልማት ተቀብለዋል፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ ኮሌጁን በሚጐበኙበት ጊዜ  ያነጋግሯቸውና በትምህርታቸው ያበረታቱዋቸው ነበር፡፡ በመስከረም 09)^4 ዓ.ም. በሁለተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የጵጵስና መዓርግ ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስነታቸው ከላይ እንደተጠቀሰው በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የቤተ ክርስቲያንና ትምህርታቸውንና ሁለተኛ ደረጃ የዘመናዊ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ አቅራቢነትና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ፈቃድ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸው በአሜሪካ አገር ለ06 ዓመታት  ታዋቂነት ባላቸው በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በዚሁ መሠረት፣ ዲፕሎማ ግንቦት፡ 09)%5 ዓ.ም የቴዎሎጂ ምሩቅ በቅዱስ ቭላድሚር የሩሲያ ኦርቶዶክስ ሲሚናሪየም (ኒውዮርክ) ልዩ ትኵረት በኦሪየንታል እና በምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቴዎሎጂ፤ ባችለር በዲቪኒቲ (ነገረ መለኮት) ግንቦት 09)%9 ዓ.ም በበርክሌይ ዲቪኒቲ ት/ቤት በየል (ኒውሄቭን) በኦሪየንታል በምሥራቅና በምዕራብ አብያተ ክርስቲያናት መካከል በቴዎሎጂ አመለካከት እና ልዩነት በተለይም በነገረ መለኮት (በዲቪኒቲ) ላይ ያለውን ልዩ የጥናት መስክ በማዳበር አግኘተዋል፡፡ በማስከተልም የቴዎሎጂ ማስተርስ፡- ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ዲቪኒቲ  ግንቦት 09)^5 ዓ.ም፣ የፊሎሶፊ ዶክተር፡- ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ዲቪኒቲ በዲቪኒቲ ግንቦት 09)*1 ዓ.ም. በነገረ ማርያም ላይ ሰፊ ጽሑፍ በመጻፍ በከፍተኛ መዓርግና ክብር አጠናቅቀዋል፡፡ ከዚህም ጋር የቅዱስነታቸው የቋንቋ ችሎታ ከትግርኛ፣ ከአማርኛ፣ ከግእዝና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች በተጨማሪ በጀርመንኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በዕብራይስጥና በግሪክ ቋንቋዎች ለምርምርና ለንባብ በቂ የሆነ ችሎታ ነበራቸው፡፡

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለማሳደግና አስተዳደርዋንም ፈር ለማስያዝና ወጣቶችን በሰንበት ት/ቤቶች ለማደራጀት በነበራቸው ራእይ ያላቸውን ችሎታ በመገንዘብ የቅዱነታቸው የቅርብ ረዳት በመሆን አገልግለዋል፡፡ ለ7 ዓመታት በቀድሞው ወታደራዊ ማርኪሲስት መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነት አጠንክረው በመያዛቸው ታስረው የነበረ ቢሆንም በዚያ በከባድና በጥብቅ እስር ላይ በነበሩበት ሁኔታ 5) ያህል ቅዱሳት መጻሕፍትን ለእስረኞች ማስገባት ችለዋል፡፡ በውጭ ሀገርም ከ09)^9 ዓ.ም ጀምሮ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በአኃት አብያተ ክርስቲያናት ቋሚ ኮሚቴዎችና በሚከተሉት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ወክለዋል፡፡ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፤ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት የከተማና የኢንዱስትሪ ተልእኮ፤በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፌዝ ኤንድ ኦርደር (እምነትና ሥርዐት) ኮሚሽን፤ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማእከላዊ ኮሚቴ፤ በመሆን አገልግለዋል፡፡ በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ስብሰባዎች በኡፕሳላ ስዊድን፣ ሞምባሳ፣ ቫንኮ ቫር፣ በሞንቶሪያል /ካናዳ/ጄኔቫ፣ አክራና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በመወከል ተሳትፈዋል፡፡ እንዲሁም በልዩ ልዩ ዓለም ዐቀፍ ስብሰባዎች በመገኘት ከፍተኛ ተሳትፎና አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ በሞንትሪያል ዓለም ዐቀፍ ኤግዚቢሽን የኢትዮጵያን ልኡካን ለ8 ወራት መርተው ነበር፡፡ በ 09)*5 ዓ.ም በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ለ7 ዓመታት ምክር ቤቱ በአማካሪነት ለማገልገል ተሰይመው በአቪያን ፈረንሳይ በተካሄደው የመጀመሪያው ስብሰባ ተሳትፈዋል፡፡

 

ከእስር ከተፈቱ በኋላ በ 09)&7 ዓ.ም ጀምሮ ቅዱስነታቸው መከራና ሥቃይን በመሸሽ ለተሰደዱ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ የሚከተሉትን አብያተ ክርስቲያናት አቋቁመዋል፡፡ እነዚህም፡- የመድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በኒውዮርክ ከተማ፣ የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ዳላስ፣ የደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ፣ ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በሳንዲያጎ ካሊፎርኒያ፣ ታምፓ፣ ፍሎሪዳ፣ ፎኤኒክስ፣ አሪዞናና ሌላም ቤተ ክርስቲያን በላስ ቤጋስ፣ ኔቫዳ፡፡ በተጨማሪም በአሜሪካ በስደት ላሉ ኢትዮጵያውያን የመጽሐፍ ቅዱስንና የቤተ ክርስቲያንን እምነትና ሥርዐት ለማስተማር በመድኀኔ ዓለም፣ ቅድስት ማርያም፣ ኪዳነ ምሕረት፣ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ስድስት መንፈሳዊ ማኅበራትን አቋቁመዋል፡፡ በውጭ ሀገር በነበሩበት ወቅት ቅዱስነታቸው በግሪክ፣ በግብጽ፣ በሱዳንና ኬንያ በስደት ካሉ ማኅበረሰብ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ቀሳውስት በመመልመል በአሜሪካ አዲስ በተመሠረቱት አብያተ ክርስቲያናትና ማኅበራት እንዲያገለግሉ አድርገዋል፡፡

 

ከስደት መልስ በኋላ በ 09)*4 ዓ.ም. በሰኔ ወር ቅዱስ ሲኖዶስን ወክለው በተገኙ በአብዛኛው አባላት፤ በቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታላለቅ ገዳማትና ካቴድራሎች አስተዳዳሪዎች፤ የቤተ ክህነት ቢሮ መምሪያ ኀላፊዎች፤ በአጠቃላይ ከአብያተ ክርስቲያናት በተውጣጡ ቀሳውስት፤ ምእመናንና ወጣቶች ከተመረጡ በኋላ ቅዱስነታቸው ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ በሐምሌ 5 ቀን 09)*4 ዓ.ም. አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በመሆን ተሹመዋል፡፡ ቅዱስነታቸው የፓትርያርክነቱን ኀላፊነት ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ባላቸው ከፍተኛ ዓለም አቀፋዊ ዕውቀትና ልምድ ቤተክርስቲያናችን በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ያላትን ግንኙትና ዕውቅና ከፍ እንዲል በማድረግ የላቀ ሥራ ሠርተዋል፡፡ ከግብጽ ኮፕቲክ ጋር ሻክሮ የቆየውን ግንኙነት እንደገና ወደ መልካም ግንኙነት እንዲመለስ አድርገዋል፡፡ በነበራቸው ዓለም ዐቀፍ ታዋቂነትና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በአንድ ጊዜ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤትና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት በመሆን በዓለም ዐቀፍ ደረጃ መርተዋል፡፡ በነበራቸው ከፍተኛ የቋንቋ ችሎታና ተናግሮ የማሳመን ብቃት የኤች. አይ. ቪ ኤድስ ወረርሽን በተመለከተ በተጠራው የተባበሩት መንግሥታት ተጋብዘው ከመሳተፋቸውም በላይ ባደረጉት ታሪካዊና አስደናቂ ንግግር ከፍተኛ ተቀባይነትን በማግኘታቸው ለኢትዮጵያውያን የጠየቁት ድጋፍ ተቀባይነት አግኝቶ ፕሮጀክቱን በመላ ኢትዮጵያ እንዲዘረጋ በማድረግ ኢትዮጵያውያንን ከወረርሽኙ ታድገዋል፡፡ ለዚህም ሥራቸው ከአሜሪካ መንግሥት ሁለቴ መኪና ተሸልመዋል፡፡ ቅዱስነታቸው ለስደተኞች ባደረጉት እንክብካቤም በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ተሸልመዋል፡፡ በአገር ውስጥም በሕዝቦች መካከል ሰላም ፍቅርና አንድነት እንዲሰፍን ያላሰለሰ ጥረት አድርገዋል፡፡

 

በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ለተጐዱ ወገኖች የመጀመሪያው ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጭ በመሆን ኀላፊነታቸውን በሚገባ ተወጥተዋል፡፡ ቅዱስነታቸው ለማኅበራዊነት ሥራ የሚሰጡት ትኵረት ከማንም በላይ በመሆኑ ሕዝቡ በኀዘኑ በሕመሙና በደስታው ቀድመው በመገኘት በማስተማር በመምከርና በመጽናናት ተወዳዳሪ የሚገኝላቸው አልነበሩም፡፡ ከሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ እስከ ተራው ሕዝብ ድረስ ታመመ ወይም ችግር ደረሰበት የሚል ከሰሙ ጊዜ ሳይሰጡ ወዲያውኑ ሁሉንም እርግፍ አድርገው በመተው ይደርሳሉ የሚያስፈልገውንም ሁሉ እንዲሟላለት ያደርጋሉ፡፡

 

ከአስተዳደር አንጻር ሲታይ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት አንሥቶ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ በመላ ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ በሰጡት ትምህርትና ባደረጉት ቅስቀሳ የቤተ ክርስቲያኗ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ እንዲያድግ አድርገዋል፡፡ ኮሌጆች ማሠልጠኛዎች የአብነት ት/ቤቶች፣ ዘመናዊ ት/ቤቶች የሕፃናት ማሳደጊያዎችና የአረጋውያን መጦሪያዎች በየቤተ ክርስቲያኑ እንዲቋቋሙ መሠረቱን ጥለዋል፡፡ በዚህም በርከት ያሉ ት/ቤቶች በየቤተ ክርስቲያኑ እንዲከፈቱ አድርገዋል፡፡ የሰንበት ት/ቤት በሁሉም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እንዲቋቋም እንዲስፋፋና እንዲያድግ፣ የሠርክ ስብከተ ወንጌል እንዲጠናከር፣ ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን በስፋት እንዲሰባሰቡና ሃይማኖታዊ ዕውቀት ኖሮአቸው ቤተ ክርስቲያንና ሀገርን እንዲረከቡ በከፍተኛ ደረጃ ቀስቅሰዋል፡፡ በተግባርም አሳይተዋል@ እያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የገቢ ማስገኛ የሚሆን ልማታዊ ሥራ እንዲሠራ በሰጡት አመራር ብዙ የልማት ግንባታዎች ተገንብተዋል፡፡ ምንም ዐይነት ካርታ ያልነበራቸው የአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት ከመንግሥት ጋር በመነጋገር ለሁሉም ካርታ እንዲሰጣቸው አድርገዋል፡፡ በደርግ ጊዜ የተወረሱ የቤተ ክርስቲያን ሕንጻዎችና ቤቶች ከመንግሥት ጋር ተነጋግረው ሙሉ በሙሉ እንዲመለሱ አድርገዋል፡፡ የሊቃነ ጳጳሳትና አህጉረ ስብከት ብዛት በ3 እጥፍ እንዲያድግ አድርገዋል፡፡ የመንበረ ፓትርያርኩ ግቢም ሕንጻ በሕንጻ እንዲንበሸበሽ አድርገዋል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስነታቸው በሃያ ዓመታት ዘመነ ፕትርክናቸው እጅግ በጣም ጒልሕና ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ ሥራዎችን ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር አበርክተው ያለምንም ሕመምና ጻዕረ ሞት ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድ በሰላም ዐርፈዋል፡፡

 

የቅዱሳን ፓትርያርኮችና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጰሳት በረከት አይለየን፡፡

 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

 

ዋቢ ምንጮች

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐዋርያዊ ድርጅት፣ «ትንሣኤ፡ የሃያ አምስት ዓመታት መንፈሳዊ እርምጃ» ፤ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት (፲፱፻፶፱ ዓ/ም) ።
  • ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ «የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ»፤ ብርሃንና ሰላም በቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ማተሚያ ቤት (፲፱፻፶፮ ዓ/ም)
  • «ዜና ባስልዮስ ሊቀ ጳጳሳት ኢትዮጵያዊ»፤ ትንሳዔ ዘጉባዔ ማተሚያ ቤት (፲፱፻፶ ዓ/ም)
  • ዜና መዋዕል ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ
  • ዜና መዋዕል ዘብፁዕ አቡነ ተክለሃይማኖት
  • ዜና መዋዕል ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ
  • የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ታሪክ
  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሉሌ መላኩ
  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል

ስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፣

በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ፤
የዲያብሎስን የፈተና ወጥመዶች በጣጥሶ በድል ኣድራጊነት የተገለጠው ጌታችን ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት የጾመ ኢየሱስ ሱባዔ ኣደረሰን አደረሳችሁ!

“አኮ በኅብስት ክመ ዘየሓዩ ሰብእ አላ በኵሉ ቃል ዘይወፅእ እምኣፉሁ ለእግዚአብሔር፡- ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ ኣይኖርም” (ማቴ.፬÷፬)፤
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ ሳይውል ሳያድር ወዲያውኑ ወደ በረኻ በመሄድ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ፡፡
በአርባዎቹ ቀናት ሁሉ በቀንም ሆነ በሌሊት ምንም አልበላም ነበር፤ ካርባ ቀንም በኋላ ተራበ፤ በመብል ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ማጣላት ልማዱ የሆነ ዲያብሎስም መራቡን ኣይቶ ለምን ትራባለህ? እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ ይሁኑ ብለህ እዘዝና ብላ፤ የእግዚአብሔር ልጅ አይደለህምን? ይህንን ማድረግ ኣያቅትህም ብሎ በመብል ምክንያት የሱ ታዛዥ እንዲሆን ፈተነው::  በዚህ ጊዜ የጌታችን መልስ “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ ኣይኖርም” የሚል ነበረ፤ ጌታችን በዚህ አባባሉ የዲያብሎስን ክፉ ሐሳብ የሚንድ እንጂ የእሱ ታዛዥ አለመሆኑን ኣሳየ፤ ዲያብሎስ በዚህ ሳያበቃ በትዕቢት በፍቅረ ንዋይና በባዕድ አምልኮ ሊጥለው ደጋግሞ ሙከራ አደረገ፤ ግን አልተሳካለትም፤
በመጨረሻም ጌታ “ሑር እምድኅሬየ ሰይጣን፣ ሰይጣን ከኋላዬ ወግድ” ብሎ እኩይ ተግባሩን ውድቅ ኣድርጎበታል፤ እሱም ተስፋ ቆርጦና በጌታችን መንፈሳዊ ልዕልና ተሸንፎ ሂዶአል::

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ከጌታችን ጾም የምንወስደው ብዙ ትምህርት አለ፤ ከሁሉ በፊት ሰው በሕይወት መኖር የሚችለው በእንጀራ ብቻ ኣይደለም ብሎናል፤ ይህ ኣባባል በሕይወት ለመኖር እንጀራ አያስፈልግም ማለት ኣይደለም፤ ሕይወትን ማኖር የሚቻለው በእንጀራ ብቻ እንደ ሆነ አድርገን እንዳናስብ ግን ቃሉ ያስተምራል፤ይህም በዓለማችን በየዕለቱ የምናውቀው ሓቅ ነው፤ ብዙ ሰዎች እንጀራን ሳያጡ በየዕለቱ ሕይወትን ያጣሉ፤ ምክንያቱም በሕይወት ለመኖር የእግዚአብሔር ቃልም እንጂ እንጀራ ብቻው በቂ አይደለምና ነው:: ዓለማት ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ሁኑ ተብለው በቃሉ እንደተፈጠሩ፤ በቃሉም ጸንተው እንደሚኖሩ ኋላም በቃሉ እንደሚያልፉ ሁሉ የሰው ሕይወትም በዚህ ቃል ይወሰናል፤ እንጀራ ኖረም አልኖረ ቃሉ በቃ ካለ ያበቃል፤ ኑር ካለ ደግሞ እንጀራ ባይኖርም ይኖራል፤ ስለዚህ በሕይወታችን ወሳኝ ሥልጣን ያለው የእግዚአብሔር ቃል እንጂ፣ እንጀራ ብቻ ኣለመሆኑ ጌታችን በዚህ ኣስተምሮናል::

ከዚህም ሌላ የዲያብሎስን ፈተናዎች እንዴት በድል ማለፍ እንደምንችል ጌታችን በተግባር ኣሳይቶናል፤ ጌታችን ዲያብሎስን ያሸነበፈበት ስልት በመንፈስ ልዕልና እንጂ በዱላም፣ በካባድ መሳሪያም ኣይደለም፤ አለመሆኑንም የድርጊቱ ሂደት በግልጽ ያመለክታል፤ እንግዲያውስ እኛም ዲያብሎስን የምናሸንፈው በዚህ የመንፈስ ልዕልና ነው ማለት ነው::
ይህም ማለት በእግዚአብሔር የተከለከሉትን ግብረ ኃጣውእ እንድንፈጽም ዲያብሎስ ኅሊናችንን ሲገፋፋው፣ ያን ጊዜ ዲያብሎስ ሊፈትነን እየከጀለ እንደሆነ መንቃት ያስፈልገናል::
ጌታችን እንዳሳየንም ለክፉው ግብረ ኃጢኣት የእሺታ መልስ ሳይሆን የእንቢታ ግብረ መልስ መስጠት ይገባናል ማለት ነው፤ ይህንን ኣቅዋም የሕይወታችን ቀዋሚ መርሕ ካደረግን፤ ዲያብሎስ እየተሸነፈ፣ እኛም እያሸነፍን እንኖራለን፤ ይህንን ስንለማመድ ሓሳባችን ወይም መንፈሳችን ከዲያብሎስ በላይ የላቀና የተራቀቀ ይሆናል፤ ዲያብሎስ ረቂቅ ነው፤ የሚጣላንም ረቂቁን አእምሮኣችን በመጠቀም ነው፤ እኛም እሱን መዋጋትና ማሸነፍ የምንችለው ረቂቁ ኣእምሮኣችን ከሱ የላቀና የረቀቀ ኣድርገን በመጠቀም መሆኑን መገንዘብ ይገባል፤ይህን ካደረግን እሱ በኛ ላይ ዓቅም ኣይኖረውም::

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ጾመ ኢየሱስ እያልን በየዓመቱ የምንጾመው የታላቁ ጾማችን ዓላማ ዲያብሎስን ለማሸነፍ ነው፤ የዲያብሎስ ማሸነፊያ ስልት የመልካም ኅሊና ልዕልና ነው፤ ሰውነታችን በመብልና በመጠጥ ሲደነድን መልካም ኅሊና በውስጣችን ዓቅም ያጥረዋል፤ መልካም ኅሊና ሲያጥረን ዲያብሎስ ዘው ብሎ ይገባና ወደ ክፉ ኅሊና፣ ከዚያም ወደ ግብረ ኃጢኣት ይወስደናል፤ በዚህ ጊዜ እኛ ተሸናፊዎች እሱ ኣሸናፊ ይሆናል፤ በአንጻሩ ደግሞ ሰውነታችን ከመብልና ከመጠጥ ሲለይ መልካም ኅሊና፣ ቊጥብነት፣ ማስተዋልና ማመዛዘን በውስጣችን ትልቅ ጉልበት ያገኛሉ፤ እነሱ ጐለበቱ ማለት ዲያብሎስ መግቢያ አጣ ማለት ነው፤ እሱ ካልገባ ግብረ ኃጢኣት አንፈጽምም፤ በዚህ ጊዜ ዲያብሎስ ተሸናፊ እኛ ኣሸናፊዎች እንሆናለን፤ ስለሆነም ጾምን የምንጾመው በዚህ ስልት ዲያብሎስንና ግብረ ኃጢአትን ለማሸነፍ ነው:: ከዚህ አኳያ ዲያብሎስን ለማሸነፍ መጾም ግድ ስለሆነ ጌታችን በከፈተልንና ባሳየን መንገድ እንጾማለን፤ እንግዲህ በወርኃ ጾም ከመልካም ኅሊና የሚመነጭ መልካም ስራ ማከናወን ግድ ይለናል፤ ምክንያቱም ጾምን የምንጾመው መልካም ኅሊና ኖሮን ለእግዚአብሔር ለመታዘዝና ለመገዛት፣ ከዚያም ከቃሉ በተነገረን መሠረት የተራቡትን ልንመግብ፣ የተራቈቱትን ልናለብስ፣ የተጣሉትን ልናስታርቅ፣ ፍትሕ ያጡትን ፍትሕ እንዲያገኙ ልናደርግ፣ ለንኡሳን የሕብረተ ሰብ ክፍሎች የተለየ ትኵረት ልንሰጥ፤ እኩልና ፍትሓዊ የሀብት ክፍፍል በሰው ልጆች መካከል ልናረጋግጥ፣ ሰብኣዊ ክብር እንዳይነካ ጦርነት፣ ጥላቻ፣ አደገኛ የቃላት ውርወራና መነቃቀፍ እንዲቀር ልናደርግ ነው፤ በዚህ መንፈስ ጾሙን ከጾምን ጾማችን ግቡን መትቶአል፤ ዲያብሎስም ተሸንፎአል ማለት ነው፤ ስለሆነም በዚህ መንፈስ ጾሙን ልንጾም ይገባል፡፡

በመጨረሻም፡-

ወርኀ ጾሙን የተራበውን በመመገብ የተራቈተውን በማልበስ በኃላፊነት ያለን የኅብረተሰብ መሪዎችም ፍትሕንና እኩልነትን በማስፈንና ከነገሮች ሁሉ በፊት ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ በመስጠት ጾሙን እንድናሳልፍ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን::

መልካም ወርኀ ጾም ያድርግልን
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አሜን!!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
የካቲት ፲፯ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈ የምህላ ሱባዔ፡-
‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምህላ አስተጋብኡ ሕዝበ ሊቃውንተ ሕዝብ፤ ጾምን ቀድሱ፣ጉባኤውንም አውጁ፤ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ኣምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ (ኢዩ ፩÷፲፬)

ሁላችንም እንደምናውቀው ያለንበት ዓለም የመከራ ዓለም ነው፣ መከራው በኛ ስሕተትና ክፋት የመጣና እየሆነ ያለ መሆኑም ይታወቃል፤ እኛ የምንፈጽመው ጥቃቅንና ትላልቅ ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን እንደሚያስቈጣ በቅዱስ መጽሐፍ ተረጋግጦ ያደረ ነው፤ ለዚህም ከነነዌ ነዋሪ ሕዝብ የበለጠ ማስረጃ የለንም፤ የነነዌ ከተማ ነዋሪዎች በፈጸሙት ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን አስቈጥተዋል፤ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ ቢሆንም እሱ ምሕረቱን ማስቀደም ስለፈለገ በዮናስ በኩል አስጠንቅቆአቸዋል፤ የነነዌ ነዋሪዎችም በዮናስ በኩል የደረሳቸውን የንስሓ ጥሪ ወዲያውኑ ተቀብለው በምህላ፣ በጾም፣ በጸሎት ንስሓ ስለገቡ እግዚአብሔር ፍጹም ይቅርታ አድርጎላቸዋል፤

• የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን !

እኛ ሰዎች ዛሬም በየሰዓቱ ብቻ ሳይሆን በየደቂቃው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ አበሳ እንደምንፈጽም ማወቅ ኣለብን፣ አበሳውና ኃጢኣቱ ሲበዛ እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነውና ወደ ዳኝነት ተግባሩ ይገባል፤ይህ ደግሞ በሰብአ ትካት በሰዶምና በጎሞራ ያስተላለፈውን ዳኝነት ያስታውሰናል፤ አሁን ያለንበት ዘመን ዓመተ ምሕረት በመሆኑ እግዚአብሔር ለጊዜው ቢታገሠንም በኃጢኣታችን የምንጠየቅበት ጊዜ አዘጋጅቶአል፤ ዛሬም ቢሆን የማናስተውለው ሆነን ካልሆነ በስተቀር እግዚአብሔር ተግሣጹን ማስተላለፍ አላቆምም፤ በምድራችን ላይ በምናደርሰው የተዛባ ተግባር በጐርፍ፣ በድርቅ፣ በመሬት መንቀጥቀጥና በአየር መዛባት እየገሠጸን እንደሆነ ማስተዋል አለብን፤

እግዚአብሔር ከጥንቱ ከጠዋቱ ጀምሮ ምድርን እንድንከባከባት፤ እንድናበጃት፣ እንድናጠብቃትና እንድናለማት አዞናል፤ ሆኖም ይህን ትእዛዙን ገሸሽ አድርገን በኬሜካልና በመርዛም ጋዝ ምድርን በመበከል፣ደንዋን በመመጠርና ራቁቷን በማስቀረት በምናደርገው ድርጊት አበሳ እየፈጸምን እንደሆነ ያወቅነው አይመስልም፤ በዚህም ምክንያት በጐርፍ፣ በድርቅ ለሰው ልጆች በማይመች የኣየር ፀባይ ወዘተ . . . ስጋት ውስጥ እየወደቅን ነው፤

በሌላም በኩል በምናወሳስበው የአስተዳደር ርእዮትና መሳሳብ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭና ያላስፈላጊ አደጋ ላይ እንድወድቅ እያደረግን ነው፤ በዚህም ጠንቅ ሰላም እየደፈረሰ፣ ፍቅርና አንድነት እየላላ የሃይማኖት ክብርና ልዕልና እየተነካ ራሳችንንም እየጐዳን ነው፤በዚህ ሁሉ ተግባራችን እግዚአብሔርን እያሳዘንን ነው፤ ይህ ሊገባንና ሊቈረቁረን ይገባል፤

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አላቸው፤ መፍትሔውም የሚገኘው ከእግዚአብሔርና ከእኛ ነው፤ ከእኛ በንስሓ ተመልሰን ከልብ እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና ከክፉ ተግባራችን በእውነት መጸጸት ይጠበቃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ዓይነቱ ንስሓ ከኛ መኖሩ ሲመለከት ምሕረትና ይቅርታን ይለግሰናል፤በዚህም መፍትሔና ፈውስ ይገኛል፤ ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችንና ለዓለማችን ስጋት የሆኑ የጦርነት ክሥተቶች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የአየር መዛባት፣የድርቅ መከሠት፣የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰላም መደፍረስ፣ የሰላማውያን ወገኖች መጎዳት፣ የፍቅርና የአንድነት መላላት ወዘተ. . . . ከምድራችን ተወግደው ፍጹም ምሕረትና ሰላም እናገኝ ዘንድ በኃጢኣታችን ተጸጽተን በምህላ ንስሓ መግባት አለብን፤

ከዚህ አኳያ ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ የሚጾመው ጾመ ነነዌ ለዚህ አመቺ ጊዜ ስለሆነ ከየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ፤ እንደዚሁም በሀገራችንና በውጭ ያላችሁ ሊቃውንተ ሕዝብ ቀኖናውን ጠብቃችሁ ይህንን በማስፈጸም ምህላውን በቀኖናው መሠረት እንድታከናውኑ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፤

እግዚአብሔር አምላካችን ምሕረቱን ይቅርታውንና ሰላሙን ለሀገራችንና ለዓለማችን ይስጠን፤ ምህላችንንም ይቀበልልን፤
“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ” ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ