ሰኔ 19 ቀን 2009 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት የግንዛቤ ሥልጠና በቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡

ሰኔ 19 ቀን 2009 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት የግንዛቤ ሥልጠና በቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም ወቅት ቅዱስነታቸው የሐዋርያነት ጥሪ ትልቁ የክርስትና ጥሪ ሲሆን ጥሪው መስቀል መሸከም መሆኑን አጽንዖት ሰጥተው አስገንዝበዋል፡፡
በትምህርታቸው ጅማሬ ላይ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ በማለት የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን ምክር በማስቀደም ምእመናንን ከነጣቂ ተኵላ እንዲጠብቁና የራሳቸውንም ሕይወት በጥንቃቄ እንዲመሩ አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም በእግዚአብሔር ቃል የሰውን አእምሮ በማልማት ለፍቅርና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ እንዲሆኑ ከማድረግ ባሻገር ከመንጋው ተለይተው የባዘኑትን ለመመለስ በተጠናከረ ጥናት ላይ ተመሥርታቸሁ እንድትሠሩ አደራችን የጠበቀ ነው በማለት አባታዊ መመሪያ በመስጠት ሥልጠናውን ባርከው አስጀምረዋል፡፡