• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

ከግንቦት 05 ቀን እስከ ግንቦት 06 ቀን 2012 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

May 14, 2020

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቍጥር 164 ድንጋጌ መሠረት ከግንቦት 4 እስከ ግንቦት 6 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደውን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔዎች፤

1. በዓለማችንና በሀገራችን በኢትዮጵያ ጭምር ከቅርብ ወራት ወዲህ የተከሠተው የኮረና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ እስከ አሁን በብዙ ሚሊየን የሚቈጠሩ ሰዎችን በመያዙና ከመቶ ሺሕዎች ላላነሱ ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት በመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤን በእጅጉ ያሳዘነ ሲሆን ጉባኤው፣ በቫይረሱ የተጠቁትን ምሕረት እንዲሰጥልን እስከ አሁን በቫይረሱ ያልተጠቁትንም እንዲጠብቅልን ተማሕፅኖውን ለእግዚአብሔር አቅርቧል፡፡
2. ይኸው ተላላፊና የሰው ልጆችን በሞት እየነጠቀ ያለውን ቫይረስ እግዚአብሔር አምላክ በምሕረቱ እንዲያጠፋልን ምእመናን እንደ አንድ ልብ መካሪና እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን እንዲጸልዩ ተይዞ የነበረውን የሱባዔ ጊዜ በአግባቡ መከናወኑን ጉባኤው ተገንዝቦ ለወደፊቱም ካህናትም ሆኑ ምእመናን ወደ እግዚአብሔር የሚያደርጉትን ጸሎት በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በቤታቸው አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጉባኤው አበክሮ አሳስቧል፡፡
3. በዚሁ ወረርሽኝ መከሠት ምክንያት በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ የሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት መቋረጡ በምእመናን ሕይወት ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑና ምእመናን ከቤተ ክርስቲያን ተለይተው መኖር ስለማይችሉ በቀጣይም የሕዝቡን ጤና መጠበቅ በሚያረጋግጥ መልኩ የሚመለከታቸው የሃይማኖት አባቶች እና የጤና ባለሙያዎች በሚሰጡት ሙያዊ ምክርና መንግሥትም በሚሰጠው መመሪያ መሠረት አሁንም የአካላዊ ርቀትና ንጽሕና አጠባበቅ ከምንጊዜውም በላይ ትኵረት ተሰጥቶት፣ ለዚሁ ተግባር በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ በተመደቡ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች አስተናጋጅነት ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲከናወን፣
4. ሀገራችን ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር፣ ሕዝቧም ሕዝበ እግዚአብሔር እየተባለ እንደሚጠራ ይታወቃል፡፡ መጠራትም ብቻ ሳይሆን ሕዝባችን በፈሪሀ እግዚአብሔር ተከባብሮ እንኳን የራሱ የሆነውን ወገኑን ቀርቶ ሌላውን እንደራሱ አድርጎ የሚወድ፣ ያለው ከሌለው ጋር የሚካፈልና በደግነቱ የሚታወቅ ሕዝብ መሆኑን ዓለም የሚመሰክረው ነው፡፡ በመሆኑም ይህ የደግነት ምሳሌነታችን በተለይም በዚህ የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ በጸናበትና ሁሉም ወገን የችግሩ ተጋላጭ ሆኖ በተገኘበት በአሁኑ ጊዜ ያለውን ለሌለው በማካፈል ይበልጥ ደግነታችን ጐልቶ እንዲታይ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ እንደምንገኝ የተገነዘበው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሁላችንም ባለን ነገር ሁሉ በመረዳዳት ይህን ፈታኝ ጊዜ እንድናልፈው ጥሪውን ያቀርባል፡፡
5. ከዚህም ጋር ዜጋው እንደ ሀገር በሁለት እግሩ ቁሞ ህልውናው ተጠብቆ ሊኖር የሚችለውና ሀገራዊ ልማትም ሆነ ሕዝባዊ እድገት ሊመጣ የሚችለው በሁሉም ዘንድ ሰላምና አንድነት መግባባትም ጭምር ሲኖር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን በፖለቲካ ድርጅቶች መካከል እየታየ ያለው አለመግባባትና የቃላት መወራወር በአጭሩ ካልተገታና ወደ መግባባት በመምጣት መፍትሔ ካልተበጀለት ተጨማሪ ሀገራዊ ቀውስ ሊያስከትል፣ ከፍተኛም ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል በመገንዘብ የሚመለከታችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ለሀገራዊ ሰላምና ለሕዝባዊ አንድነቱ በጋራ እንድትቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
6. ሀገራችን ኢትዮጵያን ለከፍተኛ እድገት ያበቃል ሕዝባችንን ከድህነት አረንቋ ያወጣል በሚል እምነት ከረጅም ጊዜ አንሥቶ ሕዝባችን ትኵረት ሰጥቶ ምንም ሳይኖረው ጦሙን እያደረ አስተዋፅኦ በማድረግ እዚህ ደረጃ ላይ ያደረሰው የሕዳሴ ግድባችን አብዛኛው የግድቡ ሥራ እየተጠናቀቀና ወደ ፍጻሜውም እየደረሰ መሆኑን ስለተገለጸ ጉባኤው በከፍተኛ አድናቆት ተመልክቶታል፡፡ በቀጣይም የግድቡን ፍጻሜ ለማየት፣ የመላውን ሕዝባችን ርብርብ እንደሚጠይቅ ግንዛቤ የተወሰደ በመሆኑ እንደአባቶቻችን ለትውልድ የሚተርፍ ታሪክ ለመሥራት ሕዝባዊ አንድነቱና ተሳትፎው እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡

በመጨረሻም ከግንቦት 4-6 ቀናት በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ፣ እንዲሁም ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሲነጋገር የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጠናቅቆ በዛሬው ቀን በጸሎት ተዘግቷል፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/007-3.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32020-05-14 09:59:362025-01-27 10:01:05ከግንቦት 05 ቀን እስከ ግንቦት 06 ቀን 2012 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ግንቦት 05 ቀን 2012 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ግንቦት 05 ቀን 2012 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ግንቦት 05 ቀን 2012 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ... Link to: ነሐሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም የ2012 ዓ.ም የጾመ ፍልሰታ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ነሐሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም የ2012 ዓ.ም የጾመ ፍልሰታ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ነሐሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም የ2012 ዓ.ም የጾመ ፍልሰታ ቃለ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top