• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ ዓመታዊ ጉባኤ ከጥቅምት 4 እስከ 11 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም. አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡

October 21, 2013

“ከሁሉ በፊት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና በቤተ ክርስቲያናችን የአመራር አካላት በሙሉ እንደተለመደው ሁሉ የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ አክብራችሁ እንኳን በደኅና መጣችሁ፡፡

ይህ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ጉባኤ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በአዲስ አበባ ርእሰ ከተማ በቤተ ክርስቲያኒቱ ማእከላዊ አስተዳደር በዓመት አንድ ጊዜ እየተሰበሰብን በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በአጠቃላይም በሁለንተናዊ እድገት ላይ እየተወያየን የሚጠበቅብንን ግዳጅ ስንወጣ እነሆ! ዛሬ ለሠላሳ ሁለተኛው መደበኛ ስብሰባ ለመድረስ በቅተናል፡፡

በቃለ ዐዋዲው የቤተ ክርስቲያናችን መተዳደሪያ ደንብ እየታገዘ ሰበካ ጉባኤ አስተዳዳር ከሚሠራው የስብከተ ወንጌል ክፍል አንዱ አካል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ አንጻር የቤተ ክርስቲያናችን የደም ሥር የሆነውን የስብከተ ወንጌሉን ተግባር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ማሳደግ ይጠበቅብናል፣ ለማስረጃም ያህል አንድ ሰው ሕይወት የምትሰጠው ነፍሱ ከተለየች በዓለም ላይ የመኖር ተስፋ ስለሌለው የሚጠብቀው ዕድል ወደ ዐፈርነት መለወጥ ብቻ ነው፡፡

እንደዚሁ ሁሉ ቤተ ክርስቲያናችን ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እስከ መንበረ ፓትርያርክ ድረስ ባለው መዋቅር በስብከተ ወንጌል ካልተጠናከረች የሚጠበቅባትን ያህል አበርክታለች ለማለት አያስደፍርም፣ እንግዲህ ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲጠብቅ እንደቆየ ሁሉ አሁንም የስብከተ ወንጌሉን ተግባር ለማጠናከር መቀጠል አለበት ስንል ቢያንስ ሦስት ዐበይት ነጥቦችን መጥቀስ ያስፈልጋል፡፡

ስብከተ ወንጌልን በተመለከተ፡- የስብከተ ወንጌል ሠራተኞች ብቃት ባላቸውና በሠለጠኑ መምህራን በተደገፈ የወንጌል ትምህርት መሠልጠን አለባቸው፡፡ እነዚህ ለተልእኮ የሚፋጠኑ አስተማሪዎች የቈራጥነት መንፈስ ያልተለያቸው፣ የተቈርቋሪነት ባሕርይ ያደረባቸው መሆን አለባቸው፡፡

የገንዘብ (ፋይናንስ) አስተዳደር ሁኔታን በተመለከተ፡- የፋይናንስ ዐቅምን ማጠናከር የስብከተ ወንጌሉን ተግባር በበለጠ ማፋጠን ያስችላል፡፡ የፋይንስ ዐቅም ባልጎለበተበት ሁኔታ የሥራውን ድኅንነት ለመቈጣጠርም ሆነ ሂደቱን ለማፋጠን አስቸጋሪ እንደሚሆን ስለሚታወቅ ነው፡፡ ስለዚህ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት በአሠራር እየቀደሙ የሚታዩት ተከታዮቻቸው የሚከፍሉትን የአስተዋፅኦ ገንዘብ በማጎልበት እንደሆነ ከጉባኤው አመለካከት ይሠወራል ብለን ባንገምትም በበኩላችንም ሕዝበ ክርስቲያኑን ጠንክረን ማስተማርና ማስተባበር ይጠበቅብናል፡፡

መልካም አስተዳደርን በሚመለከት፡- ኀላፊነት ሐቀኝነትና ተጠያቂነት የተሞላበት መልካም አስተዳደር ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እስከ መንበረ ፓትርያርክ ድረስ እንዲሰፍን ማድረግ ተገቢነቱ አያጠያይቅም፡፡ መልካም አስተዳደር ከሌለ ሁሉም ነገር ከንቱ እንደሆነ እናምናለን፡፡ በቅዱስ መጽሐፋችንም ሲነገር የኖረ አሁንም እየተነገረ ያለ ስለሆነ ለመልካም አስተዳዳር መስፈን ምዕራፍ ከፋች በሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ዙሪያ ልናደርገው የሚገባንን ምግባረ ሠናይ ሁሉ በመፈጸምና በማስፈጸም ለቤተ ክርስቲያናችን ያለንን ደጀንነት መግለጽ ይጠበቅበናል፡፡
ስለዚህ በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ የተገኛችሁት፡- የየሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት፣ የየሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጆች፣ የየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች፣ በአጠቃላይም የጉባኤው ተሳታፊዎች ሁላችሁ ይህ ዓመታዊ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ ለግብ እንዲበቃ፣ የምታደርጉት ጥረት እንዲሳካ እንጸልያለን፡፡

እግዚአብሔር ይባርካችሁ ይቀድሳችሁ፡፡”

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/001-2-1000.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32013-10-21 14:37:142025-01-28 14:39:4632ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ ዓመታዊ ጉባኤ ከጥቅምት 4 እስከ 11 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም. አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: መስከረም 16 ቀን የ2006 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል Link to: መስከረም 16 ቀን የ2006 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል መስከረም 16 ቀን የ2006 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓ... Link to: ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top