• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

ጥቅምት 8 ቀን 2014 ዓ.ም 40ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡

October 18, 2021

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

ብፁዕ አቡነ ያሬድ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የበላይ ኀላፊ፣ የአርሲ ሀገረ ስብከት እና የምሥራቅ ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ፣ የሲዳማ ክልል፣ የጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የየመምሪያውና የየድርጅቱ ኀላፊዎች፣
ከሀገር ውስጥና ከውጭ አህጉር የመጣችሁ የየሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጆች፣
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የየክፍሉ ኀላፊዎች፣
የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣
ከሁሉም አህጉረ ስብከት የመጣችሁ ተወካዮች በአጠቃላይ፤ የተበታተኑትን የሚሰበስብ፣ የተራራቁትን የሚያቀራርብ እግዚአብሔር አምላካችን ከልዩ ልዩ አጽናፈ ዓለም የመጣችሁትንና ከዚህ ከቅርብ የቆየነውን በአንድነት አሰባስቦ ስላገናኘን ክብርና ምስጋና ለአምላካችን እናቀርባለን።

“ወአናቅጸ ሲኦል ኢይኄይልዋ ወኢያንቀለቅልዋ፤
የሲኦል በሮች አይበረቱባትም፤ አያናዋውጧትምም።”
(ማቴ. 16፥18)

ይህን አረፍተ ነገር ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኀይልና ጽናት አስመልክቶ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረን ትምህርት ነው፤ አረፍተ ነገሩ እንደሚያመለክተው ቤተ ክርስቲያን ፈተና የሚያበዙባት ፈታኞች እንደማይለዩዋት ነው፤ ፈተናውን የሚያመጡባት አካላት በስም ባይጠሩም በተግባራቸው የሲኦል በሮች ተብለው ስለ ተጠቀሱ ሞትና መቃብር እንደዚሁም የእነሱ ዘበኞች የሆኑ ሠራዊተ አጋንንት እንደሆኑ መረዳቱ አያዳግትም፤ ጌታችን የቤተ ክርስቲያን ፈታኞች እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ በሙሉ ዐቅማቸው ቤተ ክርስቲያንን ቢታገሏትም ሊያሸንፏት ግን አይችሉም ማለቱ በራእየ ዮሐንስ እንደተገለጸው መቃብር በትንሣኤ ዘጉባኤ፣ ሠራዊተ አጋንንት ደግሞ በደመ በግዑ በመጨረሻ የሚሸነፉና ከነካቴው የሚወገዱ መሆናቸውን ለመግለጽ እንደሆነ እናስተውላለን፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትነ ክቡራን የጉባኤው ታዳሚዎች
ሊቀ ኖሎት በሆነው በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተቋቋመውና የተሰበሰበው ይህ ዓለም ዐቀፍ ጉባኤ፣ የሲኦል በሮች የማያናውጧትን ቤተ ክርስቲያን ለመጠበቅ እንደሆነ ሁላችንም የምንገነዘበው ነው፤ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ሺሕ ዘመናት ያህል በመከራ እየተፈተነች እስካሁን ድረስ ከዕለት ወደ ዕለት እየሰፋችና ሁሉንም እያዳረሰች የመጓዟ ምሥጢር መድኀኒታችን ከላይ የገባላትን ቃል ኪዳን ሊቀለብስ የሚችል ኀይል በሰማይም ይሁን በምድር የሌለ በመሆኑ እንደሆነ አንዘነጋውም፤ ይሁን እንጂ ዋናውና ላዕላዊው ጠባቂ እሱ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ እኛም የጥበቃው ተሳታፊዎች አድርጎ ሹሞናልና አደራ ጭምር ያለበት የጥበቃ ተልእኮና ኀላፊነት አለብን፡፡ በዚህም “አማልክት አንትሙ ወደቂቀ ልዑል ኲልክሙ፤ እናንተ አማልክት ናችሁ፤ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ” ብሎ ያናገረው የጸጋ አምላክነት በእኛ ላይ እንዴት ተፈጻሚ እንደሆነ ማጤኑ ተገቢ ነው፤ ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ የቤተ ክርስቲያን ፈተና በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?በየአካባቢው የሚገኙ ኖሎትስ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ ያደረጉት ጥረት ምን ይመስላል? ለወደፊቱስ የቤተ ክርስቲያንን ፈተና ለማቅለል ምን ማድረግ ይገባል? የሚሉትን መሪ ሐሳቦች በማንሣት ይህ ጉባኤ የማየት ኀላፊነት አለበት፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ክቡራን የጉባኤው ታዳሚዎች፣
ቤተ ክርስቲያን በአየር የተንሳፈፈች ነገር ሳትሆን በማኅበረ አማንያን ልቡና ውስጥ ተጠልላ የምትገኝ መንፈሳዊት መንግሥተ እግዚአብሔር ናት፤ ይህም ባሕርይዋ ከአማንያን ህልውና ጋር ያቀራኛታል፤ አማንያንም ያለ ሀገር ህልውና ስለሌላቸው ቤተ ክርስቲያን በተከታዮቿ አማካኝነት ከሀገር ሰላም ጋር ትተሳሰራለች፣ ይህ ብቻም አይደለም፤ የዓለሙን ሰላምና ፍቅር አስተማሪ፣ ሰባኪና ተምሳሌት በመሆን የሰው ልጆችን ሁሉ የመጠበቅ ኀላፊነትም አለባት፤ ይህንም ስታደርግ እንደ እናትም እንደ መምህርም እንደ ሽማግሌም ማእከላዊት ሆኖ ሥራዋን በለብዎ ማከናወን እንዳለባት ይታወቃል፡፡ ይሁንና ቤተ ክርስቲያናችን በአሁኑ ጊዜ በፈተና ተከባ፣ ልጆችዋም እርስ በርስ እየተጣሉ እንደሚገኙ ዓለም ሁሉ የሚያውቀው ነው፤ እነዚህ ወገኖቻችን ቤተ ክርስቲያን ልጆቼ ብላ የተቀበለቻቸው፣ በልጅነት ያከበረቻቸውና ለእግዚአብሔር መንግሥት ዕጩ ያደረገቻቸው፣ ያም ባይሆን በአርኣያ እግዚአብሔር የተፈጠሩ ክቡራን ሰዎች ናቸው፤ ቤተ ክርስቲያን በዚህም በዚያም ያሉ ሁሉ ልጆቿ ናቸውና ስለነሱ ይገዳታል፤ ይሰማታል፣ ያሳስባታልም፤ በመሆኑም ብትችል መክራና አስተምራ፣ ገሥጻና ተቈጥታ፣ ካልሆነም ልባዊ የሆነ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በማቅረብ ከእርስ በርስ ጠብ ተላቅቀው በአንድነት፣ በሰላምና በፍቅር እንዲኖሩ በጸሎትና በምሕላ ፈጣሪን መማፀን አለባት፤ ይህን ስናደርግ የኖላዊነት ኀላፊነታችንን በአግባቡ እየተወጣን ነው ማለት እንችላለን፤ በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያስተላልፈው ቀኖናዊ መልእክት ገዳማቱ አድባራቱና አብያተ ክርስቲያናቱ በጸሎትና በምሕላ ተጠምደው ስለ ሕዝብ ስለ ምእመናንና ስለሀገር ደኅንነት አጥብቀው ፈጣሪን እንዲማፀኑ በዚህ ጉባኤ ፊት አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

በመጨረሻም አርባኛው ዓለም ዐቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተከፍቶ በፈቃደ እግዚአብሔር የተጀመረ መሆኑን እናበሥራለን፡፡

እግዚአብሔር የተባረከ የተቀደሰ ጉባኤ ያድርግልን፤
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/001-2-1000.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32021-10-18 14:53:332025-01-28 14:54:41ጥቅምት 8 ቀን 2014 ዓ.ም 40ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል... Link to: ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top