• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

የካቲት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ቀናት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

March 8, 2016

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤
«ኅሡ ሰላማ ለብሔር እስመ በሰላመ ዚኣሃ ይከውን ሰላምክሙ፤
የአገርን ሰላም ሹ ፈልጉ የአገራችሁ ሰላም የእናንተ ሰላም ነውና።

የሀገርና የወገን ፍቅር ያለው ሕዝብ ሰላም ከእግዚአብሔር መሆኑን ያውቃል፣ ሰላም ለሰው ልጆች ከማናቸውም መሠረታውያን ፍላጎቶች በላይ ተቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራችን የተለያዩ ሃይማኖቶች፣ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ተቻችለውና ተረዳድተው የሚኖሩባት የዓለም ምሳሌ ናት፡፡ ይህን ዓለምን የሚያስደንቅ ገጽታችንን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንዲከተለው ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት! ኢትዮጵያ አህጉረ ሰላም (የሰላም ሀገሮች) ከሚባሉት ከዓለም ሀገሮች አንዷ ስትሆን በአሁኑ ጊዜ በአንዳንድ ከተሞች የሚታየው አለመረጋጋት ሁሉንም የሚያሳስብ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ከዚህም ጋር ባሳለፍናቸው ሳምንታት በተከሠተው ያልተጠበቀ ችግር፡-

1. በአንዳንድ አካባቢ የሰው ሕይወት ሲጠፋ፣ ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ፣ የንግድ ተቋማት፣ የሕዝብና የመንግሥት ንብረት፣ የእምነት ተቋማት ሲወድም የሕዝባችን የዕለት ከዕለት ኑሮ ሲናጋ ሁሉም ኅብረተሰብ የችግሩ ተጠቂ ሆኗል፣ የዚህ ዐይነቱ ድርጊት በዚህ ሁኔታ የሕዝባችን ህልውና የትውልዱም የወደፊት ዕድል አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል፡፡
2. ባሳለፍናቸው ሳምንታት በተከሠተው ሁኔታ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች በመሪር ኀዘንና ጸሎት እናስባቸዋለን፡፡ ስለዚህ ሁላችሁም ልጆቻችን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወንድ፣ ሴት፣ ወጣት፣ ሽማግሌ ሳትሉ ችግራችሁን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለሚመለከተው እንድታቀርቡ መንግሥትም የሕዝቡን ችግር እና ሰላማዊ ጥያቄ በመገንዘብ መፍትሔ በመስጠትና ሰላም ለማምጣት እያደረገ ያለውን የዕለት ከዕለት ጥረት እንዲቀጥልበት በቤተ ክርስቲያናችን ስም እናሳስባለን፡፡
3. ሕዝባችንና ሀገራችን በረኃብ፣ በድኅነትና በበሽታ ቸነፈር በተቸገረበት ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት መሠረታዊ ወደሆነው ልማት የሰላምና የድርቅ ጉዳይ በማተኮር መልስ ሰጭ መሆን ይገባዋል ብለን በጽኑ እናምናለን፡፡
4. ወገኖቻችን ሆይ በአሁኑ ጊዜ የወቅቱ የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ (ብሎጎችና የፌስ ቡክ) ተጠቃሚዎች በሙሉ ኢትዮጵያውያን ከሙያችሁ ከዕውቀታችሁ ተጠቃሚዎች የመሆን ምኞታቸው የላቀ ነው፡፡ ሆኖም መልካሙንና ለእድገት የሚያግዛቸውን ዕውቀት እንጂ ኅብረተሰቡን የሚለያይና የሚያራርቅ መረጃ (ኢንፎርሜሽን) ዕለት ዕለት ብታስነብቡት ትርፉ መራራቅን እንጂ መቀራረብን፣ መለያየትን እንጂ መግባባትን አያመጣም፣ ከዚህ አንጻር የእናንተም ጥረትና ድካም ከንቱ ሆኖ ይቀራል፡፡ በመሆኑም የተከበረ ዕውቀታችሁን ሙያችሁን ለሕዝባችን ፍቅርና አንድነት፣ ለሀገራችን ሰላምና እድገት እንድታውሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጥብቃ ትጠይቃለች፡፡

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን፡ ተቻችሎና ተረዳድቶ የመኖር የተቀደሰ ነባር ባህላችንን የሚያጎድፍ ማናቸውንም አስተሳሰብና እንቅስቃሴ በአንድነት መቋቋም እንደሚገባ አበክረን እየገለጽን፣ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን በሙሉ በተለይም አገር ተረካቢ ትውልድ የሆናችሁ ወጣቶች ሁከትና ብጥብጥን ከሚያስከትሉ መጥፎ ድርጊቶች እንድትቈጠቡ ለአገር ልማትና ሰላም ጠንክራችሁ እንድትቆሙ በልዑል እግዚአብሔር ስም አጥብቀን እያሳሰብን በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የሀብትና፣ የንብረት ውድመት፣ በተለይም የሕዝብ መገልገያ የሆኑ የእምነት ተቋማት መቃጠል የተሰማንን ኀዘን እንገልጻለን፡፡ ይልቁንም ከሁሉም በላይ ሁሉን ማድረግ የሚችል እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ለሀገራችን ሕዝቦች ሰላሙን፣ ፍቅሩን አንድነቱን ይሰጥልን ዘንድ፣ ድርቁን ረኀቡን አስታግሦ መጪው ጊዜ ዝናመ በረከቱን ይሰጠን ዘንድ በያዝነው በዐቢይ ጾም ሱባኤ ጸሎተ ምሕላ በመላ ሀገሪቱ ባሉት ገዳማትና አድባራት የገጠር አብያተ ክርስቲያናት እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖአል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/007-3.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32016-03-08 08:34:392024-12-07 08:37:54የካቲት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ቀናት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት... Link to: ሚያዝያ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በንጹሓን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሠቃቂ ግፍ Link to: ሚያዝያ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በንጹሓን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሠቃቂ ግፍ ሚያዝያ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top