• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

መስከረም 16 ቀን 2008 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል (የእስክንድርያ ፓትርያርክ መገኘት ጋር)

September 27, 2015

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

“ወደምሰሰ ለነ መጽሐፈ ዕዳነ በሥርዐቱ እምእድውነ ወአእተቶ እማእከሌነ ወቀነዎ በመስቀሉ —
በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዝ የተጻፈውን የእዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፡፡ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል” (ቆላ. 2፥14)።

የተወደዳችሁ በዚህ በዓል ላይ የተገኛችሁ ሁሉ፤

እንኳን ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ መስቀል በሰላም አደረሳችሁ

በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሚከበሩት ታላላቅ በዓላት አንዱ በዓለ መስቀል ሲሆን ስለ መስቀል መናገር ማለት ስለ ሰው ልጅ የድኅነት ታሪክ መናገር ነው፡፡ መስቀሉ የመዳናችን ብቻ ሳይሆን የሕይወትና የድል አድራጊነት ምልክታችንም ነውና፡፡ በመስቀሉ ዕርቅና ሰላም፣ ነፃነትና ተስፋ ይሰበካሉ፤ ቅዱስ መስቀል ዕርቅ የተፈጸመበት አደባባይ፣ አማናዊው የሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት የተሠዋበት መንበር ነው፡፡ በመስቀሉ ጌታችን በሰው ላይ የተፈረደውንና የሕይወት ዕንቅፋት የነበረውን ሞትን በራሱ መሣሪያ አቅርቦ ከመንገድ ያስወገደበት፣ እርሱ ጌታችን የሕይወት ንጉሥ ሆኖ የነገሠበት ዙፋን ነው፡፡የተቀደሰ ነው የምንለውም በክርስቶስ ደም የተቀደሰ ስለሆነ ነው፡፡

ጌታችን እኛን ከሰይጣን ቍራኝነት ነፃ ያወጣን፤ ወደራሱ ያቀረበን፣ ጠብን እንድናሳድድ ጥላቻን እንድናስወግድ፣ከጥፋት እንድንድን ያደረገን በመስቀሉ ስለ ሆነ ይህ በዓል ለእኛ የድኅነታች ማስታወሻ አድርገን እናከብረዋለን፤ ከቅዱሳት መጻሕፍትና ከታሪክ እንደምንረዳው ጌታችንን የሰቀሉት አይሁድና የወቅቱ መሪዎች ከሙታን መነሣቱ ስለቈጫቸው የተሰቀለበትን መስቀል ዓለም እንዳያስታውሰው ቀበሩት፡፡ ይሁን እንጂ በመስቀሉ የተፈጸመውን ድኀነትና ፍቅር መቅበር ስላልቻሉ፤ፍቅሩ በልባቸው የታተመው ክርስቲያኖች በንግሥት እሌኒ መሪነት ከሦስት መቶ ዓመት በኋላ ቅዱስ መስቀሉን ከተቀበረበት አወጡት፡፡ አስቀድሞ በመስቀሉ የተገኘውን ድኅነትና ሰላም፣ የተገለጸው ፍቅር፣ የተደመሰሰው የዕዳ ጽሕፈት፣ የተወገደው ጥላቻና ሞት በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ዋና ጉዳዮች ስለሆኑ በክርስቲያኖች ዘንድ መስቀሉን ማክበር ተቋርጦ ዐያውቅም፡፡ እኛም በሀገራችን በአንድነትና በፍቅር ሁነን ጥንታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በዓለ መስቀሉን በአደባባይ ወጥተን ደመራ ደምረን እያከበርን እንገኛለን፡፡

የዘንድሮውን የ2008 ዓ/ም በዓለ መስቀል ልዩ የሚያደርገው ብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ታዋድሮስ ዳግማዊ የእስክንድርያ ፖፕና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ከግብጽ ሀገር በመምጣት በመካከላችን መገኘታቸውና በዓለ መስቀሉ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ሁኖ በተመዘገበበት ማግስት መሆኑ ነው፡፡

በዚሁ አጋጣሚ ብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ታዋድሮስ ዳግማዊ ጥሪያችንን ተቀብለው በመምጣታቸው የተሰማኝን ደስታ እየገለጽኩ በድጋሚ እንኳን ደኅና መጡ እላለሁ፡፡ እንደሚታወቀው በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል ለብዙ ዘመናት የቆየ ግንኙነት ያለሲሆን፣ ግንኙነቱ በእግዚአብሔር ፈቃድና በተፈጥሮ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ይህ ግንኙነት ቆይቶ ወደማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሃይማኖታዊ ግንኙነት እያደገ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ቀደም ሲል እንደተባለው ግንኙነቱ የተመሠረተው በተፈጥሮ ላይ ስለሆነ ወደፊትም አይቋረጥም፡፡ ለዚህ አንዱ ምሳሌ የዐባይ ወንዝ ነው፡፡ ይህ በቅዱሳት መጻሕፍት ሳይቀር ስሙ የተጠቀሰው ታላቁ ወንዝ ለዘመናት ሁለቱን ሀገሮች እያጠጣ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ከራሳቸው አልፎ ለጎረቤት ሀገሮች ሳይቀር የሚጠቅም ግድብ እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ የግድቡ መገንባትም በማንም ላይ ጒዳት እንማያደርስ በዓለም ዐቀፍ ባለሙያዎችም ጭምር መረጋገጡ ሁላችንም ያስደሰተ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በወንድም ላይ ጒዳት ሳያደርሱ ራስን መጥቀም ደግሞ ወገናችን የሆነው የግብጽ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ፈጣሪንም የሚያስደስት የሥነ ልቦና ነፃነትን የሚሰጥ ሰላማዊ ተግባር ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር የመስቀል በዓልን ስናከብር ፍቅርን ወዳጅነት እንደምንዘክር ሁሉ የቅዱስነታቸውም በመካከላችን መገኘት ለሁለቱ ሀገሮች ሕዝቦች የወደፊት ትብብር ብቻ ሳይሆን የሃይማኖት አባቶች ለዓለም ሰላምና ደኅንነት ለምናሰማው የጋራ ድምፅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ በተለይ በአሁኑ ጊዜ ባለ መቻቻል፣ በጽንፈኝነት፣ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በስደት፣ በእርስ በእርስ ጦርነት፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ እና በመሳሰሉት ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ችግሮች የሰው ልጅ ሕይወት ለአደጋ በተጋለጠባቸው የዓለማችን ክፍሎች መፍትሔ ለመስጠት የሚመለከታቸ ሁሉ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታሳስባለች፡፡

በቅርቡ ከሀገራቸው የወጡ የኢትዮጵያና የግብጽ ወጣቶች የዚሁ ችግር ሰማዕታት ሲሆኑ የሁለቱም ሀገሮች አባቶች ተመሳሳይ መልእክትን ለዓለም አስተላልፈዋል፡፡ ኢትዮጵያውያንና ግብጻውያንም በችግርና በደስታ ያለቸውን አንድነት ገልጸዋል፡፡ ከወራት በፊት ቅዱስነታቸው ባስተላለፉልን ጥሪ መሠረት ከብፁዓን አባቶች ጋር በመሆን ግብጽን የጎብኝን ሲሆን አሁን ደግሞ እኛ ባቀረብንላቸው ጥሪ መሠረት ወደ ሀገራችን መጥተው በመካከላችን ተገኝተዋል፡፡ ቅዱስነታቸው በኢትዮጵያ የሚኖራቸው ቆይታ ታሪካዊ እንደ ሚሆንና የሁለቱን ሀገሮች መልካም ግኑኝነት የበለጠ እንደሚያጠናክር ጽኑ እምነት አለን፡፡

በዓሉን የሰላምና የፍቅር ያድርግልን፣ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ይጠብቃችሁ፣ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/001-2-1000.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32015-09-27 12:55:552025-01-28 12:56:56መስከረም 16 ቀን 2008 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል (የእስክንድርያ ፓትርያርክ መገኘት ጋር)
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: መስከረም 1 ቀን የ2008 ዓ.ም አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት Link to: መስከረም 1 ቀን የ2008 ዓ.ም አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት መስከረም 1 ቀን የ2008 ዓ.ም አዲስ ዓመት የእንኳን... Link to: 34ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከጥቅምት 8-11 ቀን 2008 ዓ.ም አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡ Link to: 34ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከጥቅምት 8-11 ቀን 2008 ዓ.ም አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡ 34ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከጥቅምት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top