• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

መስከረም 16 ቀን የ2007 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

September 26, 2014

የሀገራችንን ዳር ድንበር በመጠበቅና በማስከበር በየዘርፉ ያላችሁ፥
በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ የተኛችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ፤

በመስቀል ላይ በተከፈለው መሥዋዕትነት የሰውን ልጅ ከኀጢአት ፍዳ የታደገ ጌታችንና አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለ2007 ዓ.ም በዓለ መስቀል አደረሳችሁ፡፡

በመስቀል ላይ የተከናወነውና የተከፈለው ዋጋ ድንገተኛ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢተ ነቢያት የተነገረነው፡፡ የመስቀሉ ሥራ የማዳን ሥራ ነው፡፡ የጌታ ደስታ ከድኅነተ ምእመናን ጋር የተያያዘ ነው የሰውም ደስታ የድኅነት ባለቤት ሆኖ መገኘት ነው፡፡ መስቀል የሚለው ቃል ብዙ ትርጓሜ ቢኖረውም ሁለት ዐበይት ነገሮችን ማየት ይቻላል፡፡ ይኸውም በምሥጢራዊ ትርጒሙ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መሥዋዕት በመሆን በኀጢአት የተበከለውን ዓለም ማዳኑን የሚያመለክት ቃል ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ዓለም በክርስቶስ መስቀል ዳነ ሲል ሰው በክርስቶስ መሥዋዕትነት መዳኑን ያመለክታል፡፡ መስቀል ኀይላችን ነው፣ መስቀል ቤዛችን ነው፣ መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው፡፡ከመስቀሉ በቀር ሌላ የምንመካበት ነገር የለንም የሚሉት ኀይለ ቃላት መዳናችንና ማሸነፋችን ነው፡፡ በሌላ በኩል መስቀል የመሥዋዕትነት ትምህርት ወይም አርማ ነው፡፡ እኛም በመስቀሉ እንፈወሳለን እንባረካለንም መስቀልን ማክበር ክርስቶስን ማክበር ማለት ነው፡፡ የክርስትና ሃይማኖት በተጀመረበት ዘመን የነበሩ ሰዎች የክርስቶስን መስቀል በመቅበርና በመሠሰወር የተነሡበት ምክንያት መስቀሉ የመፈወስ ሥልጣን በማሳየቱ ነው። የመስቀሉ መገኘት ኢአማንያንን ያሸማቀቀ ክሥተት ነበር፡፡ የመስቀሉ አዳኝነት እስከ አሁን ድረስ ቀጥሎአል የቀደሙ ቅዱሳን አባቶቻችን ካወረሱን መንፈሳዊ ውርስ አንዱ በዓለ መስቀልን እያከበሩ በሃይማኖት ጸንተው መኖርን ነው፡፡ እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማንያን በየዓመቱ በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዐት በምናከብረው የመስቀል በዓል አማካኝነት የክርስቶስን አዳኝነት ለዓለም እንመሰክራለን በዚህም ዓለምን ወክሎ በሚገኘው የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) ሕጋዊ ዕውቅና ሰጥቶናል፡፡ ስለዚህ መላው ሕዝበ ክርስቲያን እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ የመስቀል በዓላችን ያሬዳዊ ዜማችንና ብቸኛው ፊደላችን ልዩ የሆነው የዘመን አቈጣጠራችን የዓለም አቀፉ ተቋም ዩኒስኮ እንዲመዘግባቸው የማስተዋወቅ ሥራ ለመሥራት ጥሪአችንን እናስተላለለፋለን፡፡ ,

የዘንድሮው የመስቀልን በዓል የምናከብረው ልማታዊና ሰላማዊ ተልእኳችንን ከግብ ለማድረስ ቃል በመግባት ነው፡፡ እየተገነቡ ያሉት ሕንጻዎች የአንድነታችን መገለጫዎች መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም፤ ሁላችንም አንድነታችንና ሰላማችንን ጠብቀን በእኩልነትና በመከባበር ለአንዲት ሀገር መነሳት አለብን በማለት ቅዱስነታቸው ሰፋ ያለ ትምህርታዊ ማብራርያ ከሰጡ በኋላ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ስጦታው በበኩላቸው የመስቀል ደመራ አከባበር በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) በማይዳሰሱ ቅርሶች በቅርስነት መመዝገቡ በቱሪዝም ዘርፍ ከሚገኘው ጠቀሜታ ባሻገር የሀገራችንን መልካም ገጽታ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ አወንታዊ በሆነ መልኩ በመገንባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚኖረው ይሆናል፡፡ ከቱሪስት መስሕብነት ባሻገር በዓሉ ከቀድሞ በተሻለ እንክብካቤ የሚደረግለትና ለትውልድ እንዲተላለፍ እገዛ እንደሚሰጥ ጽኑ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡የሀገራችን መንግሥት በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ልዩ ልዩ የማይዳሰሱ ቅርሶች በቅርስነት እንዲመዘገቡ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡የመስቀል ደመራ በዓል የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ለዘመናት በድምቀት ሲያከብሩት የኖሩት ሃይማኖታዊ በዓል ብቻ ሳይሆን ዓለም ዐቀፍ ዕውቅና አግኝቶ የሀገራችንን ገጽታ በቱሪዝም ልማት ይቀይራል በኢፊድሪ ሕገ መንግሥት በተረጋገጠው የእምነት ነፃነት መሠረት የሀገራችን ሕዝቦች በዓላትን እንደ እምነታቸው ማክበር ከጀመሩ ዓመታት ተቈጥረዋል መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው ሲባል አንዱ ባንዱ ላይ ጣልቃ ሳይገባ የየራሳቸውን ሥራ እንዲፈጽሙ የሚያደርግ እንጂ መንግሥትና የሃይማኖት ተቋማት በጋራ ሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ የሚያደርጉት ተሳትፎ የሚደነቅ ነው፡፡ ይህንንም አጠናክረው ሊቀጥሉበት ይገባል፡፡ የመከባበርና የመቻቻል አኵሪ ባህላችን ማውሳት አንዱ ጉዳይ ሆኖ ዛሬ በዓለም ካሉና በሥልጣኔ ካደጉ ሀገራት እኩል የሀገራችንን ስም ለማስጠራት በመንግሥታችን የተጀመረውን ፀረ ድህነት ትግል በእልህና በወኔ እንዲሁም በታላቅ ሀገራዊ ፍቅርና ስሜት ለማሳካት መረባረብ ይኖርብናል፡፡

 

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/001-2-1000.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32014-09-26 12:39:582025-01-28 12:41:42መስከረም 16 ቀን የ2007 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: መስከረም 1 ቀን የ2007 ዓ.ም የዘመን መለወጫ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: መስከረም 1 ቀን የ2007 ዓ.ም የዘመን መለወጫ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ መስከረም 1 ቀን የ2007 ዓ.ም የዘመን መለወጫ ቃለ ምዕዳንና... Link to: 33ኛው ዓመታዊ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከጥቅምት 5-8 ቀን 2007 ዓ/ም አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡ Link to: 33ኛው ዓመታዊ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከጥቅምት 5-8 ቀን 2007 ዓ/ም አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡ 33ኛው ዓመታዊ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top