• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

ግንቦት 05 ቀን 2012 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

May 13, 2020

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣

በየተሰማራንበት ሁሉ እግዚአብሔር እየረዳን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና የምግብና ሥራችንን እየተወጣን ከቆየንበት ሀገረ ሰብከት በሰላም አምጥቶና አንድ ላይ አሰባስቦ ስለ ሃይማኖታችንና ስለሀገራችን ለመወያየት የሰበሰበን እግዚአብሔር አምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን፡፡

“ትግሁ ወጸልዩ ከመ ኢትባኡ ውስተ መንሱት፤ ወደፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ” (ማቴ-6፡1)፡፡ ፈጣሬ ፍጥረታት እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚወድ ብቻ ሳይሆን ከሕዝቡ መለየት የማይፈልግ አምላክ ነው፣ የእግዚአብሔር መኖሪያ በሰው እጅ በተሠራው ቍሳዊ ነገር ሳይሆን እሱ ራሱ በሠራው በሰው ልቡና ስለሆነ፣ ከሰው ጋር መገናኘት የሚፈልገውም በዋናነት በዚሁ ስፍራ እንደሆነ እሱ ራሱ ነግሮናል፤ ታዲያ እግዚአብሔር ከሰው ልቡና መለየት እንደማይፈልግ ሁሉ ሰውም ምንም ደካማ ቢሆንም ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር መለየት አይፈልግም፤ ይህም የጋራ ፍላጎት ሊከናወን የሚችለው በእምነትና በጸሎት ነው፡፡ ይህ ግንኙነት የደጋፊና ተደጋፊ ዐላማ ያለው ግንኙነት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችንን በዚህ መልኩ በጸሎት ስንቀርብ በቀላሉ እንደምናገኘው እናምናለን፤

“ወሀቦ ለልዑል ጸሎተከ ትጼውዐኒ በዕለተ ምንዳቤከ አድኅነከ ወተአኵተኒ — ጸሎትህን ለልዑል እግዚአብሔር አቅርብ፤ በመከራህ ቀን ትጠራኛለህ፤ እኔም አድንሃለሁ፤ አንተም ታመሰግነኛለህ” ሲል ቃል ገብቶልናል፡፡ ይህ ወቅት በመላ ክፍለ ዓለም ተሰራጭቶ የሚገኘው የኮረና ቫይረስ በሽታ ፍጥረተ ሰብእን በጠቅላላ ከባድ ሥጋት ላይ የጣለበት ወቅት ነው፤ “በእንቅርት ላይ—-” እንደሚባለው ሀገራችን በሌሎች ውስብስብ ነገሮች በተወጠረችበት ወቅት ይህ ዐይነቱ መድኀኒት የለሽ በሽታ መከሠቱ በሀገራችን ላይ ሥጋት እንዲበዛ አድርጓል፡፡

ይህ ወቅት ለሀገራችንም ለቤተ ክርስቲያናችንም ለሕዝባችንም ከባድ የፈተና ወቅት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ እንደ ትናንቱ የመሰለ አካሄድና አስተሳሰብ ጭራሽ የሚያስኬድ አይሆንም፤ እኛ ሊቃነ ጳጳሳት የሕዝበ እግዚአብሔር እረኞች ሆነን እዚህ ላይ የተሰበሰብነው ሕዝቡን በሁለንተናዊ ሕይወቱ ከፈተና ለመጠበቅ መሆኑን በውል የምንገነዘበው ነው፡፡ ይህ ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ በብዙ መልኩ እየተፈተነ ነው፤ ሕዝቡ በሰላም ዕጦት የኅሊና ጭንቀት ላይ ነው የሚገኘው፤ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በቀጣዮቹ ዓመታት በእጅጉ ሊጎዳ እንደሚችል የበሽታው ተጽዕኖ ምልክት እያሳየ ነው፤ የተከሠተው በሽታ መቼ ሊወገድ እንደሚችል የሚታወቅ ነገር የለም፤ ስለሆነም በዚህ ሁሉ ፈተና ተጎጂው ማን ነው? ሲባል እኛ እረኛ የሆንለት ሰፊው ሕዝብ በተለይም በዝቅተኛ ኑሮ የሚኖር ድሀው ሕዝባችነ ነው፡፡

ይህ ሕዝብ እየታዩ ባሉት ችግሮች በመከራ ቢለበለብ በእግዚአብሔር ዘንድ ያስጠይቀናል፤ ሕዝቡም ይታዘበናል፤ ይህም እንዳይሆን በተቻለ ዐቅም በጸሎትም፣ በትምህርትም፣ በምክርም፣ በማስታረቅም ሰፊ የማግባባትና የሕዝብ አድን ሥራ መሥራት አለብን፤ አሁን ያለው ጥያቄ ሀገርንና ሕዝብን ከፈተና የመታደግ ጥያቄ ነው፤ ይህንን ፈተና መሸጋገር የምንችለው በአንድነት ሆነን ስንቆም ብቻ ነው፤ አንድነትን ለማምጣት ደግሞ የማግባባት ሥራ የግድ መሥራት አለብን፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ይህ ጉባዔ በጥልቀትና በአጽንዖት ተወያይቶ ወደ ተጨባጭ ሥራ እንዲገባ ያስፈልጋል፡፡

ሕዝባችን በውስጣዊና አካባቢያዊ የአስተሳሰብ ልዩነት ምክንያት ብዙ ውጣ ውረድ ባለበት ወቅት ተጨማሪ ሸክም ሆኖ የመጣብንን የኮረና በሽታም በአጭር ታጥቀን ሕዝቡን በማስተማር፣ በጸሎት በመትጋትም ክፉውን ቀን በሰላም እንድናሸጋግረው ጠንክረን መሥራት አለብን፡፡ እስከ አሁን ድረስ ቤተ ክርስቲያናችን፣ ሌሎች አብያተ ሃይማኖት፣ መንግሥትና ሕዝብ፣ እንደዚሁም የተለያዩ የሚድያ አውታሮች በጋራ ሆነው በሠሩት ሥራ ቢያንስ የወረርሽኙ በሽታ የከፋ አደጋ እንዳያደርስ በመከላከላቸው በዚህ አጋጣሚ ሳናመሰግን አናልፍም ለወደፊቱም በዚሁ እንዲቀጥል በጋራ እየተባበሩ መሥራቱን ማጠናከር ይኖርብናል፡፡

በመጨረሻም፡ ሁላችንም እንደምናየውና እንደምንገነዘበው በሀገራችን እየተከሠቱ ያሉት የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ችግሮች ሁሉ መንግሥትና የፖለቲካ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እግዚአብሔርና ታሪክ የጣለባችሁን አደራ በላቀ አስተውሎት ነገሩን በማጤን ሀገርንና ሕዝብን በሰላም፣ በጤና እና በአንድነት የማሻገር ከፍተኛ ኀላፊነት በእጃችሁ እንዳለ አውቃችሁ ይህንን ሕዝብና ሀገር ወደ ተሻለ አስተማማኝ ሰላም፣ ጤንነትና እድገት በፍቅርና በአንድነት ሁናችሁ እንድታሸጋግሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አደራ ትላችኋለች፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ጊዜም ከሕዝቡ ጎን መሆኑን እየገለጽን የሁለት ሺ ዐሥራ ሁለት ዓመተ ምሕረት የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ በዛሬው ዕለት መከፈቱን እናበሥራለን፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ይቀድስ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/007-3.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32020-05-13 09:57:302025-01-27 09:59:08ግንቦት 05 ቀን 2012 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ሚያዝያ 11 ቀን 2012 ዓ.ም የበዓለ የትንሣኤ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ሚያዝያ 11 ቀን 2012 ዓ.ም የበዓለ የትንሣኤ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሚያዝያ 11 ቀን 2012 ዓ.ም የበዓለ የትንሣኤ ቃለ ምዕዳንና... Link to: ከግንቦት 05 ቀን እስከ ግንቦት 06 ቀን 2012 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡ Link to: ከግንቦት 05 ቀን እስከ ግንቦት 06 ቀን 2012 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡ ከግንቦት 05 ቀን እስከ ግንቦት 06 ቀን 2012 ዓ.ም የተካሄደው...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top