• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም 42ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡

October 16, 2023

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

•ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
•ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና በሰሜን አሜሪካ የኒዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳስት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤
•የየመምሪያውና የየድርጅቱ ኃላፊዎች፣
•የየሀገረ ስብከቱ ተወካዮች፣
•የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣
•ከልዩ ልዩ ክፍለ ዓለማት የመጣችሁ እንግዶች፣
•በአጠቃላይ በዚህ ዓቢይ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ የተገኛችሁ በሙሉ

እግዚአብሔር አምላካችን ከዓመት ዓመት አድርሶ ይህን የተቀደሰ ቀኖናዊ ጉባኤ ለማካሄድ ስለሰበሰበን ክብርና ምስጋና ለሱ እናቀርባለን እናንተንም እንኳን ደኅና መጣችሁ እንላለን፡
“በብዙኅ ሕማም ሀለወነ ንባኣ ለመንግሥተ እግዚአብሔር” ወደ እግዚብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ይገባል (የሐ.ሥራ 14፥22)

ይህ የቅዱስ መጽሐፍ አስተምህሮ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ጠንካራ ጥረትና ጽናት የሚያስፈልግ መሆኑን የሚያስገነዝብ ገዢ አስተምህሮ ነው ከቅዱስ መጽሐፍም ከታሪክም በትክክል ተመዝግቦ እንደሚገኘው የቤተክርስቲያን ጉዞ ገና ከጅምሩ አንሥቶ በጸዊረ መስቀል የታጀበ ነው

ጸዊረ መስቀል ምንም የመረረ ቢሆንም ተሸንፎ ግን አያውቅም ነገረ መስቀል በአሸናፊነት እንጂ በተሸናፊነት አይታወቅምና ነው ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ መግባት አለብን ሲሉ የመከራ መስቀል ዓጸፋ አሸናፊነትና መዳን መሆኑን ስለሚያውቁ ነው በሀገራችንም ሆነ በመላው ዓለም ዙሪያ ያሉ ክርስቲያኖች የተለያዩ ጸዋትወ መከራዎችን በመቀበል የሚገኙት ከመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ከሐዋርያት ተጋድሎ ባገኙት ውርስ ነው፡፡

•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
•ክቡራን የጉባኤው ተሳታፊዎች!!

እንደ ዕድል ሆኖ ዘመናችን በመከራ መስቀል የታጀበ ሆኖ ይታያል ብዙ ክርስቲያኖች በአሁኑ ጊዜ በዚህ ፍኖተ መስቀል እያለፉ ነው አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ፣ ካህናትና ምእመናን እየተፈናቀሉ፣ እየተሰደዱና እየተገደሉ ነው ሌላም ጫና ሁሉ እያንገላታቸው ነው ይህ ሁኔታ ሄዶ ሄዶ ሃይማኖቱን የሚያዳክም ነው ሃይማኖቱ ሲደክም ደግሞ ኢትዮጵያዊ ማንነትና ባህል አብሮ ይደበዝዝና አለን ብለን የምንመካበት ዕሤት በሙሉ ነበረ ወደ ማለት ይቀየራል ታሪኩን ሃይማኖቱንና ባህሉን ሥነ ምግባሩንና ትውፊቱን ያጣ ወይም የማያውቅ ትውልድም ይተካና ሁሉም በጨለማና በድንግርግር ይዋጣል

ይህ ዓይነቱ የሃይማኖት የታሪክ የማንነትና ባህል ውድቀት እንዳያጥለቀልቀን ጠንክሮ መስራት ዛሬ ከምንም ጊዜ በላይ ይጠበቅብናል የኛ ዐቅም ከመንፈስ ቅዱስ መንጭቶ በምእመናን ልቡና የሚመላለስ ኃይል ስለሆነ ይህንን ዐቅም ለመጠቀም ከሁሉ በላይ ምእመናንን በእንክብካቤ መያዝ ያስፈልገናል በዘመነ ሰማዕታት ቤተክርስቲያንን በፀዊረ መስቀል ያሻገሯት ካህናትና ምእመናን እንደፈትልና ሰም ተዋሕደው ነው ለምእመናን የምናቀርበው አገልግሎት ሁሉ የምእመኑን ልብ የሚረታና ለሃይማኖቱ በፍጹም ልቡ ታማኝ ሆኖ እንዲቆም የሚያስችል ሊሆን ይገባል፡፡

•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
•ክቡራን የጉባኤው ተሳታፊዎች!!

ሁላችንም እንደምንገነዘበው አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ዓላማ በተወሰነ የንዋይ አሰባሰብ ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን በቤተክርስቲያኒቱ ዙሪያ መለስ ተልእኮ ላይ የሚሠማራ ዓቢይ ተልእኮ ነው በተለይም በምእመናን ህልውናና ደኅንነት ላይ አብዝቶ መስራት ያስፈልጋል ምእመናን ካሉ ሁሉም አለ ምእመናን ከሌሉ ግን ሁሉም የለም ይህንን ሁላችንም በትኲረት ልንገነዘብ ይገባል፡፡
ሌላው ልናልፈው የማንችል ታላቅ ነገር የቤተክርስቲያናችንን አንድነት ነው በቤተክርስቲያን አንድነት እንደዚሁም በሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ይዘቱ ላይ ጥያቄ ያለው ሰው ይኖራል ብለን አንገምትም በዚህም ብዙ ልዩነት አናይም ነገር ግን በአንዳንድ አስተዳደራዊና ዘመን ወለድ ቅሬታዎች አንድነታችን እየተፈተነ ነው ይህ የማንም ስሕተት ሳይሆን በውስጣችን የተፈጠረ ዕንቅፋት ነው
በመሆኑም ይህ እየተፈታተነን የሚገኘው የአንድነት ፈተና በተለመደው የቅዱስ መጽሐፍ አስተምህሮ በጥበብና በብልሐት ማረም ግድ ይለናል ቅሬታ ብቻ ሳይሆን የቅሬታ መፍቻም አለና እሱን ተጠቅመን አንድነቱን ማምጣት አለብን ተለያይቶ መኖር ያሳፍራል ያዳክማልም እንጂ በየትኛውም መመዘኛ ብርታት ይሰጣል ተብሎ አይገመትም ስለሆነም ቅሬታን በድርድርና በውይይት በይቅርታና በመተማመን ዘግተን አንድነታችንን ማጽናት አለብን፡፡
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
•ክቡራን የጉባኤው ተሳታፊዎች!!

ቤተክርስቲያናችን ወደ ፊት ተራምዳ ታላቁ ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ካደረጋት አንዱ የአሰራር ስልታችን እንደሆነ ማንም አይስተው በመሆኑም ይህንን ዘመኑን የማይዋጅ የአሰራር ስልታችን ለማሻሻል የሚያስችል፣ ሊመራና አቅጣጫ ሊያመላክት የሚችል መሪ ዕቅድ እንዲዘጋጅ በቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑ ይታወቃል በውሳኔው መሠረት የመሪ ዕቅድ ሰነድ ተዘጋጅቶና ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ ይሁንታ አግኝቶ በአሁኑ ጊዜ የሥርጸትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ
በመሆኑም መሪ ዕቅዱ፣ አሰራራችንን መልክ በማስያዝ፣ ለውጤት በሚያበቃ አተገባበርና አፈጻጸም በመከተል በመናበብና በመግባባት ልንጠቀምበት ይገባል ሃይማኖትን ከመንካት በቀር ሃይማኖታችንን ለማስጠበቅ የሚያስችለንን የዘመኑ ቴክኖሎጂ (የአሰራር ጥበብና ዘዴ) በሙሉ ተጠቅመን መምራት ጊዜው የሚጠይቀው ቊልፍ ተግባር ነው
ከዚህ ሌላ ትንሽም ሆነ ትልቅ ስራ መስራትና ውጤት ማስመዝገብ የሚቻለው ሰላም ሲኖር ነው ሀገራችንን ጨምሮ በአካባቢያችን የሚገኙ ጎረቤቶች በሰላም እጦት እየተንገላቱ ነው ስለሆነም አሁንም አብዝተን ወደ አምላካችን በመጸለይ፣ ስለ ሰላም ስለ አንድነትና ስለ ወንድማማችነት ፍቅር ደጋግመን ልናስተምርና ልንጮህ ይገባል መንግሥታችንም የአብያተ ሃይማኖት ደኅንነት የካህናትና የምእመናን የመኖር ዋስትና የሁሉም ዜጎች ሰላማዊ ኑሮ በማስፈን ለአካባቢው ሰላም የበኩሉን እንዲወጣ፣ ሕዝቡም ለዚሀ አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ በዚህ አጋጣሚ በቤተ ክርስቲያናችን ስም ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
በመጨረሻም
በዚህ ዓለም ዐቀፋዊና ዓመታዊ የቤተክርስቲያናችን አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ለመገኘት ከሀገር ውስጥና ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት የመጣችሁ ሁላችሁም በድጋሚ እንኳን ደኅና መጣችሁ እያልን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 32ኛውን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጸሎት የተከፈተ መሆኑን እናበስራለን፡፡

እግዚአብሔር የተባረከና የተቀደሰ ጉባኤ ያድርግልን፤
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን፡፡

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/photo_2023-10-16_12-06-25-1030x579-1.jpg 579 1030 tc https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc2023-10-16 20:38:552025-02-28 20:41:21ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም 42ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል የቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል የቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል የቅዱስነታቸው... Link to: የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል Link to: የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top