• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም የዓብይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ

March 28, 2021

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ወምእመናት በሙሉመልካም ስጦታ ሁሉ ገንዘቡ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሦስት ዓመተ ምሕረት የጌታችን የአምላካችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ጾም በሰላም አደረሳችሁ!!

“ኦሆ በልዎ ለእግዚአብሔር ወእንብየ በልዎ ለሰይጣን ወይጐይይ እምኔክሙ
እንግዲህ ለእግዚአብሔር እሺ በሉት፤ ሰይጣንን ግን እንቢ በሉት ከእናንተም ይሸሻል።”
(ያዕ. 4፥7)

ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ በዚህ መልእክቱ እግዚአብሔርን እሽ እንድንል፥ ሰይጣንን ግን እምቢ እንድንል ያስተማረን ያለምክንያት አልነበረም፤ እኛ ሰዎች ከክብር ወደ ኀሣር፤ ከማግኘት ወደማጣት የወረድንበት ክ ጠላት እሱ ስለሆነ እንጂ፤ቀዳማዊ አዳም ለእግዚአብሔር መታዘዝን ቸል ብሎ ወይም ትቶ ለሰይጣን የታዘዘ ቀን ነበረ የሰው ልጅ ጸጋውን ሁሉ ያጣው፤ ያን ጊዜ ሰው ሰይጣንን እምቢ ብሎ ለእግዚአብሔር ቢታዘዝ ኖሮ በሰው ላይ የደረሰው ውድቀት አይከሠትም ነበር፡፡ ሰይጣን ሰውን የጣለው በመብል ምክንያት እንደነበረ ቅዱስ መጽሐፍ የሚነግረን እውነታ ነው፤ሰውን አስጐምጅተው ወደ ስሕተት ከሚጥሉ ነገሮች አንዱ መብል እንደሆነም እናውቃለን፡፡

ዲያብሎስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመፈተን የተጠቀመው ስልትም እንደዚሁ መብል ነበረ፡፡ ነገር ግን ክብር ለእርሱ ይሁንና ዲያብሎስ፡-
• በስስዕት ቢመጣበት በትዕግሥት፣
• በትዕቢት ቢመጣበት በትሕትና፣
• በፍቅረ ንዋይ ቢመጣበት በጸሊአ ንዋይ ድል ስላደረገው ተስፋ በመቊረጥ ትቶት እንደ ሄደ ከቅዱስ መጽሐፍ እንረዳለን፡፡

ይህ ሁናቴ የሚያመለክተን እውነታ ቢኖር ሰው በዲያብሎስ የሚሸነፈው በፈቃደ ሥጋው ዝንባሌ መሆኑ ነው፤ዲያብሎስ ለቀዳማዊ አዳምም ሆነ ለዳግማዊ አዳም የዘረጋቸው የጥፋት ወጥመዶች ከላይ የተጠቀሱት ፈቃዳተ ሥጋ ናቸው፡፡ ቀዳማዊ አዳምን ለእሱ ታዛዥ በማድረግ ድል ያደረገበትም ይኸው ፈቃደ ሥጋ ነው፤ በአንጻሩ ደግሞ ዳግማዊ አዳም እሱን ድል ያደረገበት ይህን ፈቃደ ሥጋ ባለመቀበል ነው፡፡ከዚህ አኳያ ዲያብሎስ ሰውን ለመጣል የሚጠቀምበት መሣሪያ ፈቃደ ሥጋ ከሆነ ለፈቃደ ሥጋ ባለመሸነፍ ዲያብሎስን በብርቱ መቃወም ይኖርብናል። በአንጻሩ ደግሞ ለእግዚአብሔር በታማኝነት መታዘዝ ይኖርብናል ማለት ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፤

የጌታችንን ጾም በማሰብ የምንጾመው ይህ ዐቢይ ጾም ዋና ዐላማው ዲያብሎስን በመቃወም ለእግዚአብሔር ለመታዘዝና ለመገዛት ነው፤የዲያብሎስ ውጊያ ለብዙዎቻችን ላይገባን ይችላል፡፡ ነገር ግን ላስተዋለው እጅግ በጣም ቀላል ነው፤ ይኸውም ፈቃደ ሥጋችንን ለመፈጸም ብለን የማይገባውን ነገር ለማድረግ ስንጐመጅ ያን መልእክት የዲያብሎስ ውጊያ መሆኑን ማወቅ እንችላለን፤ታድያ በዚህ ጊዜ የእኛ አቅዋም ሊሆን የሚገባው መቃወም ብቻ ነው፡፡

በአንጻሩ ደግሞ ለእግዚአብሔርም ለሰውም የሚበጅ፤ለሊናም ጸጸት የሌለው ሥራ እንድንሠራ ሊናችንም ቤተ ክርስቲያንም ሲነግሩን፣ አእምሮአችንም ሲቀበለው ያ ነገር በቀጥታ የእግዚአብሔር መልእክት መሆኑን ተገንዝበን እሱን መፈጸም ነው፤ለእግዚአብሔር መታዘዝ ማለትም ይኸው ነው፤ በሌላ አገላለጽ፣ እግዚአብሔር በቅዱስ መጽሐፍ አድርጉ ያለንን ማድረግ አታድርጉ ያለንን አለማድረግ ነው፤ ይህም ማለት ለእግዚአብሔር መገዛት ማለት እንደሆነ ማስተዋል ይገባል፤ መታዘዝም ማለት ይኸው ነው፤ይህ ነገር በሕይወታችን ዘመን ሁሉ እንደ ዐይን ብሌን ልንጠብቀውና ልንፈጽመው ይገባናል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፤

ዲያብሎስን መቃወም በአንጻሩ ደግሞ ለእግዚአብሔር መታዘዝ የዘወትር ተግባራችን ቢሆንም በተለይም በጾም ወቅት በብርቱ ልንፈጽመው ስለሚገባ ፈቃደ ሥጋን በማድከም፣ ፈቃደ ነፍስን ግን በማጐልበት እንጾማለን፤ በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ አብዝተን ልንሠራው ከሚገባን ፈቃደ ነፍስ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ስምምነት፣ ይቅር ባይነት፣ መታዘዝ፣ መተጋገዝ፣ መራራት ካለው ከፍሎ ለሌለው መስጠት የሚሉት በዋናነት የሚታዩ ናቸው፡፡ ምክንያቱም በሀገራችን በተከሠተው ችግር መንሥኤነት ብዙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ለረኃብ፤ ለእርዛት፤ ለመፈናቀል መዳረጋቸውን በብዙ መልኩ እየሰማን ነው፤ እያየንም ነው፤ችግሩ እኛን ብቻ ሳይሆን የዓለም ማበረ ሰብንም እያሳሰበ እንደሆነ እያየን ነው፡፡ በመሠረቱ ይህ መከራ ሊከሠትብን የቻለው በውስጣችን ፍቅርና ሰላም በመጥፋቱ ስለሆነና አሁንም መፍትሔው በእኛው እጅ ስለሆነ ነገሮች በሰላምና በፍቅር እልባት እንዲያገኙ ሁሉም ወገን ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ለወገን ደራሽ ወገን ነውና በየአቅጣጫው ያሉ የተቸገሩ ወገኖቻችንን ለመርዳትና ለማገዝ እጆቻችን በርራኄ ሊዘረጉ ይገባል፡፡ በዚህ መንፈስ ተቃኝተን ጾምን የምንጾም ከሆነ በእርግጥም ለእግዚአብሔር ታዝዘናል ማለት ነው፡፡

በመጨረሻም፤ ከሁሉ በፊት የሰው ሕይወት በቀጣይነት እንዳይጎዳ፣ አብያተ ክርስቲያናት እንዳይደፈሩ፣ ንዋየ ቅድሳትና ቅርሶች እንዳይዘረ መንግሥት ድርጊቱን በማስቆም ለሁሉም የሕግ ከለላ እንዲያደርግላቸው ሕዝቡ የሃይማኖት ተቅዋማትና በጎ አድራጊዎችም በችግር ያሉ ወገኖችን በመደገፍ የበኩላቸውን ርዳታ እንዲያደርጉ፣ መንፈሳዊና አባታዊ ጥሪያችንን እያስተላለፍን በጎ አድራጊዎች ሁሉ ለእግዚአብሔር እና ለሰብኣዊ ፍጡር ሲሉ በከፍተኛ ችግር ላይ የወደቁትን ወገኖች ሁሉ ሕይወት እንዲያተርፉ በእግዚአብሔር ስም እንማፀናለን፣ እናሳስባለን፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ወርኀ ጾሙን አስፈጽሞ ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም ያድርሰን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/001-2-1000.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32021-03-28 14:11:312025-01-28 14:12:29የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም የዓብይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ጥር 11 ቀን 2013 ዓ.ም.የጥምቀት በዓልን በማስመልከት በጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት ያስተለለፉት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ጥር 11 ቀን 2013 ዓ.ም.የጥምቀት በዓልን በማስመልከት በጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት ያስተለለፉት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ጥር 11 ቀን 2013 ዓ.ም.የጥምቀት በዓልን በማስመልከት... Link to: ሚያዝያ 24 ቀን 2013 ዓ.ም ቅዱስነታቸው የትንሣኤ በዓልን አስመልክተው የሰጡት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ሚያዝያ 24 ቀን 2013 ዓ.ም ቅዱስነታቸው የትንሣኤ በዓልን አስመልክተው የሰጡት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሚያዝያ 24 ቀን 2013 ዓ.ም ቅዱስነታቸው የትንሣኤ በዓልን...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top