• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ/ም የጾመ ፍልሰታ መግቢያ ቃለ ቡራኬና ምዕዳን

August 7, 2016

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

በሀገር ውስጥም ሆነ በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ወምእመናት፣

እንኳን ለሁለት ሺሕ ስምንት ዓመተ ምሕረት የቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ።

‹‹ቃለ እግዚአብሔር ንጹሕ ወየሐዩ ለዓለም
የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ነው፤ ለዘለዓለሙም ያድናል።››
(መዝ.18፡9)፡፡

ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ስለ ቃለ እግዚአብሔር አስመልክቶ በዘመረው መዝሙር ሲናገር ‹‹የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ነው›› ይላል፤ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቃል የተለያዩ ፍጡራን ከሚናገሩዋቸው ቃላት ልዩ፣ ንጹሕ፣ ቅዱስና ክቡር ነው፡፡ የፍጡራን ቃል ከሐሰት፣ ከወላዋይነት፣ ካላዋቂነት፣ ከጥርጣሬ፣ ከአስመሳይነት፣ ከአታላይነትና ከዐቅም ውሱንነት ጋር ተቀላቅሎ ስለሚነገር ንጹሕ ነው ብሎ መናገር አይቻልም፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን ከዚህ ሁሉ የተለየ በመሆኑ ፍጹም ንጹሕ ነው፤ እውነትም ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ብቻ ሳይሆን ኀያልም ነውና በተናገረው መሠረት ከሚፈጸም በቀር ፍጹም የማይቀለበስ ነው፡፡

‹‹የእግዚአብሔር ቃል ከሚወድቅ፣ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል›› የሚለው የጌታችን የአምላካችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ኀይለ ትምህርት፣ የእግዚአብሔር ቃል ከሁሉም በላይ የሆነ ክብር፣ ኀይልና ጽናት ያለው መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ በመሆኑም ንጹሕና እውነት የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል በማጣመም፣ ወይም በመሸራረፍ፣ ወይም በመቀናነስ ወይም ለራስ ፍላጎት በሚያመች ሁኔታ እያዛቡ መናገርና ማስተማር በእግዚአብሔር መንግሥት ከሁሉ ይልቅ ታናሽ የሚያደርግ መሆኑን በቅዱስ ወንጌል ተጽፎአል፤ (ማቴ. 5፡19)፤ የእግዚአብሔር ቃል እውነተኛና ንጹሕ የመሆኑን ያህል ሕያውና ዘለዓለማዊ ነው፤ በሁለት ወገን ስለት ካለው ሰይፍም ይልቅ የሚቈርጥና የሚለይ ኀይል አለው (ዕብ.4፡12)፡፡ ይህም ማለት የእግዚአብሔርን ቃል እንዳለ ተቀብለው የሚጠብቁትንና የሚታዘዙለትን ለዘለዓለሙ ሕያዋን የማድረጉን ያህል፣ የሚሸራርፉትንና የሚያጣምሙትን ደግሞ የመቅጣት ሥልጣን ያለው መሆኑን ያሳየናል፡፡ በመሆኑም የሰው ልጅ ድኅነት፣ ቃሉን በመጠበቅና ባለመጠበቅ ሚዛን ላይ ተቀምጦ እንዳለ መገንዘብ አለብን፡፡

ንጹሕና ሕያው የሆነው፣ ሰዎችንም ለዘለዓለሙ በሕይወት እንዲኖሩ የሚያደርገው የእግዚአብሔር ቃል፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በተመለከተ የተናገረው እውነት አለ፤ በቀጣዮቹ ሁለት ሱባዔያት የቅድስት ድንግል ማርያምን ነገረ ፍልሰት ምክንያት በማድረግ የምንፈጽመው አምልኮተ እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔር ቃል ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተናገረውን በማስታወስና ለቃሉ ተገዥ በመሆን ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብዙ ተናግሮአል፤ ከተናገራቸውም መካከል፡ (1) ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ (2) እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው፤ (3) ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ (4) በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን አግኝተሻል፤ (5) መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፣ የልዑልም ኀይል ይጸልልሻል፤ (6) የጌታዬ እናት ወደኔ ትመጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ? (7) ብፅዕት ነሽ፤ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ (8) እነሆ ልጅሽ እነኋት እናትህ፤ የሚሉ ይገኙባቸዋል፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም የተናገረውን ቃል ጠቅለል አድርገን ስንመለከት በዋናነት የሚያሳየው ቅድስት ድንግል ማርያምን የጌታ እናት መሆኗን አምነው በመቀበል ‹‹ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ነሽ›› እያሉ እንዲያከብሯት በእግዚአብሔር መታዘዙ ነው፤ ምክንያቱም የድንግል ማርያም ክብር፣ ከእግዚአብሔር ክብር ጋር የተያያዘ ባሕርይ አለውና ነው፤ ቅድስት ድንግል ማርያም ምልእተ ጸጋ፣ ሙኃዘ ፍሥሐ፣ ምልእተ በረከት፣ የእግዚአብሔር ባለሟል፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለች፣ ብፅዕት ባትሆን ኖሮ ጌታን ለመውለድ የሚያስችል ንጽሕናና ቅድስና አይኖራትም ነበር፤ እግዚአብሔር ንጹሐ ባሕርይ እንደ መሆኑ መጠን በንጹሐንና በቅዱሳን አድሮ ይኖራልና፡፡

ቅድስት ድንግል ማርያም ጸጋን፣ በረከትን፣ ባለሟልነትን፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መሆንን፣ በድንግልና መፅነስን በእግዚአብሔር ኀይል መከለልን ገንዘብ አድርጋ መገኘቷ፣ ከእርስዋ የተወለደው ማን እንደሆነ በትክክል እንድናውቅ ያስችለናል፡፡ ቅዱስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ ሳንል፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክ ወሰብእ ብለን ማመንና መዳን አንችልም፤ ቅድስት ድንግል ማርያምን ምልእተ ጸጋ፣ ምልእተ በረከት፣ ሙኃዘ ፍሥሐ፣ ብፅዕት፣ ንጽሕት፣ ቅድስት ስንል ነው ከእርስዋ የተወለደውን ጌታ የባሕርይ አምላክ ነው ማለት የምንችለው፣ ምክንያቱም የቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ ጸጋና ቅድስና ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት አስረጅ በመሆኑ ‹‹ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ነሽ›› እያልን እመቤታችንን እንድናከብር የእግዚአብሔር ቃል አዞናልና፤ (ሉቃ. 1፥45-48)፡፡

ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱና በቅድስት ድንግል ማርያም መካከል ያለው ግንኙነት የእናትነትና የልጅነት እንደሆነ ሁሉ፣ በምእመናንና በድንግል ማርያም መካከል ያለው ግንኙነትም በእናትነትና በልጅነት ደረጃ እንዲሆን አዞአል፤ (ዮሐ19፡26-27)፡፡ በሁሉም ዘንድ እንደ ሚታወቀው አንድን ልጅ አቅፋ፣ አዝላ፣ አጥብታ፣ መግባ፣ ንጽሕናውን ጠብቃ፣ በእንክብካቤ የምታሳድግ እናት ታስፈልገዋለች፤ እናትም የሚያከብራትና የሚያስከብራት ልጅ ያስፈልጋታል፤ እንደዚሁም ሁሉ ጌታችን እመቤታችንን የምእመናን እናት እንድትሆን ሲያደርግ፣ በሥጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ተጐሳቁለን እንዳንጎዳ በጸሎቷ፣ በልመናዋ፣ በአማላጅነቷ እያገዘችና እየደገፈች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ልታደርሰን ብሎ እንደሆነ ልብ ብሎ ማስተዋሉ ተገቢ ነው፡፡ ምእመናንም የእመቤታችን ልጆች እንድንሆን ማድረጉ፣ በዚህ ዓለም ስንኖር እርስዋን አክብረንና አስከብረን በስሟ እየተማፀን የበረከቷና የጸጋዋ ተካፋይ እንድንሆን ብሎ እንደሆነ በውል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹እነኋት እናትህ›› ከተባለበት ሰዓት ጀምሮ እመቤታችንን ወስዶ በቤቱ አኑሮአታል፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እመቤታችን በእያንዳንዱ አማኝ ልጇ ቤት በመንፈስ እየገባች ትኖራለች፡፡ በዚህ የጌታችን ቃል፣ የሐዋርያት ትምህርትና ትውፊት መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ቤት፣ የእመቤታችን ቤት ሆኖ ይገኛል፤ ምክንያቱም በቤቱ የድንግል ማርያምን ሥዕል አስገብቶ እምዬ እናቴ፣ ብፅዕት ነሽ እያለ የማይጸልይና የማይማፀን የለምና፣ በዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመን የሆነ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ሳይሸራርፍ፣ ሳይቀናንስና ሳያጣምም እንዳለ ተቀብሎ እየፈጸመ ይገኛል፤ ቃሉን በምልአት በመጠበቁና በመፈጸሙም እንደ ቃሉ ተስፋ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ ይኖራል፡፡

እግዚአብሔር በቅድስት ድንግል ማርያም በኩል የሰጠን ትልቁ ስጦታ ፍጹም ፍቅር ነው፤ ይኸውም በእናትና በልጅ መካከል ያለውን ፍቅር ነው፤ ያ ፍቅር ነው እስካሁን እመቤታችንንና እኛን አስተሳስሮ የሚገኘው፤ ከዚህ ፍቅር ሊለዩን የሚሞክሩትን ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል፣ በኦርቶዶክሳዊና በኢትዮጵያዊ መንፈስ ልንቋቋማቸው ይገባል፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምን ብፁዕት ነሽ እያለ የሚያመሰግን ሁሉ፣ እንደ ኤልሳቤጥ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላና የእግዚአብሔርን ቃል በምልአት የያዘ መሆኑን እርግጠኛ ይሁን ፡፡ በእኛና በቅድስት ድንግል ማርያም ያለው ፍቅር ዐቢይና ጥልቅ እንደመሆኑ መጠን፣ ስመ ማርያምን ጠርቶ ቁራሽ እንጀራ የሚለምን ሁሉ፣ ስለእርስዋ ፍቅር ብለን ለድሆች ስንዘክር፣ የነበረውን ሃይማኖታዊ ተግባራችን ዛሬም ሳይቀዘቅዝ ሊቀጥል ይገባል፡፡

በዚህ በጾመ ማርያም ወቅት የተራቡትን በማጒረስ የታረዙትን በማልበስ፣ የታመሙትን በመጠየቅ፣ የታሠሩትን እግዚአብሔር ያስፈታችሁ በማለት፣ በማኅበረ ሰቡ መካከል መቻቻልን፣ መተማመንን፣ ወንድማማችነትን፣ ስምምነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን በማስፈን ሱባዔውን ልንፈጽም ይገባል፤ ከዚህም ጋር በአሁኑ ጊዜ በስፋት እያጋጠመ ያለውን የትራፊክ አደጋ መቀነስ ይቻል ዘንድ፣ ምእመናን ሁሉ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመላለሱም ሆነ በሌላ ቦታ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ጥንቃቄ ባልተለየው ሁኔታ እንዲሆን፣ ሹፌሮችም ሲያሽከረክሩ ኀላፊነት፣ ጥንቃቄና ማስተዋል ባልተለየው ሁኔታ እንዲሠሩ መንፈሳዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፤ በየቤተ ክርስቲያኑ የሚገኙ መምህራንና ሰባክያንም የጉዳዩን አሳሳቢነት በማስገንዘብ ሕዝቡ ከትራፊክ አደጋ ጥንቃቄ ያደርግ ዘንድ በዚሁ ሱባኤ ሰፊ ትምህርትና ምክር እንዲሰጡ አደራ ጭምር መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ይቀድስ፤ስብሐት እግዚአብሔር አሜን፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/001-2-1000.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32016-08-07 13:04:362025-01-28 13:05:41ነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ/ም የጾመ ፍልሰታ መግቢያ ቃለ ቡራኬና ምዕዳን
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ከግንቦት 16 ቀን እስከ ሰኔ 1 ቀን 2008 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡ Link to: ከግንቦት 16 ቀን እስከ ሰኔ 1 ቀን 2008 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡ ከግንቦት 16 ቀን እስከ ሰኔ 1 ቀን 2008 ዓ.ም የተካሄደው... Link to: ነሐሴ 13 ቀን 2008 ዓ.ም. በዓለ ደብረ ታቦርን በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ነሐሴ 13 ቀን 2008 ዓ.ም. በዓለ ደብረ ታቦርን በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ነሐሴ 13 ቀን 2008 ዓ.ም. በዓለ ደብረ ታቦርን በማስመልከት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top