• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል

February 28, 2022

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ፤

በጾምና በጸሎት ወደ እርሱ የሚቀርቡትን በዐይነ ምሕረት የሚቀበል እግዚአብሔር አምላካችን፣ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ አራት ዓመተ ምሕረት የጾመ ኢየሱስ ሱባዔ በሰላም አደረሳችሁ።

“ትግሁ ወጸልዩ ከመ ኢትባኡ ውስተ መንሱት
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ፤”
(ማቴ. ፳፮፥፵፩)

ምድራውያን ሰዎች የምንኖርባት ይህች ዓለመ መሬት ከሰው ውድቀት በኋላ በልዩ ልዩ ፈተና የምትናጥ እንደ ሆነች ሁላችንም የምናውቀው ነው፤ እሷን ከፈተና ነፃ ማድረግም ሆነ መከላከል የሚችል ከፍጡራን ወገን አልተገኘም፤ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም “ወበዓለምሰ ሀለወክሙ ትርከቡ ሕማመ፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ “ማለቱ ይህንን የሚያመለክት ነው፤ ከዚህ አኳያ ሲታይ ዓለም ምን ጊዜም ከፈተና ውጭ አይደለችም ማለት ነው፤ ይህ እውነት እንደ ሆነ እኛም በዓይናችን የምናየው፣ በአእምሮአችን የምንገነዘበው ሓቅ ነው፤ ግብረ ኀጢአትና ክፉ ሕሊና እስካሉ ድረስ ፈተና ባይቀርም፣ መለኮታዊ መከላከያ የሌለው ግን አይደለም፤ መከላከያውም ኀይለ እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔር ኀይልና ረድኤት ለማግኘት ደግሞ፣ ሰው ቆም ብሎ ማሰብና በንስሓ ወደ እግዚአብሔር፤ መመለስ ያስፈልገዋል፤ ከዚህ አንጻር የንስሓ፣ የጾምና የጸሎት አስፈላጊነት ፈተናን ለመከላከል እንደሆነ እንገነዘባለን፤ ይህም በመሆኑ ጌታችን፣ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ በማለት አስተማረን።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት፤

በጌታችን አስተምህሮ መሠረት ፈተናው ከማየሉ በፊት ተግተን ካልጸለይን ፈተና ሁሌም ይጸናብናል፤ ይሁን እንጂ ጌታችን በሌላ በኩል “ለምኑ ይሰጣችኋል” ብሎ ቃል የገባልን በመሆኑ በፈተና ውስጥ ሆነንም በንስሓ፣ በጾምና በጸሎት እሱን በመለመን ፈተናን መከላከል እንችላለን ፤ ጌታችን እኛን ለማስተማር አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በጾመ ጊዜ በፈተና አምጪው ፍጡር ላይ የተቀዳጀው ድል የምናውቀው ነው፤ አሁን የምንጀምረው የጾመ ኢየሱስ ሱባዔም ፈተናን እንዲያስቀርልን፣ በምትኩም ምሕረቱን እንዲያወርድልን ለመለመን እንደሆነ ሕዝበ ክርስቲያኑ በውል ተገንዝቦ በተመሥጦ ወደፈጣሪው መማፀን ይኖርበታል። እንግዲህ መዋዕለ ጾም የንስሓ ጊዜ ነው ሲባል፣ ንስሓ የምንገባው እንዴት ነው የሚለውንም ማስተዋሉ ተገቢ ነው፤ ልባችን እንደሚመሰክርብን ያለንበት ጊዜ፣ጥል ያየለበት፣ጭካኔ ሥር የሰደደበት እንደሆነ አይካድም፤ በዚህም ምክንያት የብዙ ልጆቻችንና ወገኖቻችን ሕይወት ተቀጥፎአል ፣ኑሮም ተመሰቃቅሎአል፤ ጥላቻ ቦታ ካገኘ ውጤቱ ከዚህ ሌላ ሊሆን አይችልምና ይህንን ሁሉ አስከትሎብናል፤ በመሆኑም በዚህ ወርኀ ጾም ንስሓ መግባት አለብን ስንል የከረምንበቱን የጥላቻ ሕሊና ከሥር መሠረቱ ነቅለን በመጣል፤ ፍቅርንና ሰላምን በመሻት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አለብን ማለታችን ነው ፤ ጾምን በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ መሥዋዕት የሚያደርገው፣ ኀይል ሰጪ ከሆኑት መባልዕት መከልከል ብቻ ሳይሆን ከጠብና ጥላቻ መራቅና መከልከል እንደ ሆነ በሚገባ ማስተዋል ይኖርብናል፤ በመዋዕለ ጾም ወቅት ኀይል ሰጪ ከሆኑ መባልዕት መከልከል ያስፈለገውም ጠብና ጥላቻን ለመቀነስ፣ብሎም ለማስወገድ ምቹ መደላድልን ለመፍጠር እንጂ ምግቦቹ በራሳቸው ኀጢአት ሆነው አይደለም፤ በመሆኑም ከፈተና ለማምለጥ የእግዚአብሔር ኀይል ያስፈልገናል የእግዚአብሔርን ኀይል ለማግኘት ደግሞ በኀይለ ሥጋ ሳይሆን በኀይለ መንፈስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ያስፈልጋል፤ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ደግሞ ከባልንጀራ ጋር በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ ፍጹም ፍቅር መመሥረት ያስፈልጋል፣ ፍቅር ስለተባለውም ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ “በአጠገብህ ያለውን ወንድምህን ሳትወድ እግዚአብሔርን እወዳለሁ ማለት ውሸት ነው” ብሎ እንዳስተማረን ወንድማችንን ሳንወድ ወደ እግዚአብሔር ብንቀርብ ተቀባይነት እንደ ማይኖረን ማወቅ አለብን፤ በመሆኑም ለእግዚአብሔር ክብርና ለዘላቂ ሰላም ሲባል ወደ እውነተኛው ፍቅር መሸጋገር አለብን፤ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ፍቅራችንን ድልድይ አድርጎ ፈተናውን ያርቅልናል፤

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት፤

ባጋጠመን ሀገራዊ ፈተና መነሻነት ሕዝባችን ሲፈተን ቤተ ክርስቲያናችንም የችግሩ ገፈት ቀማሽ ከመሆን እንዳላመለጠች ሁላችንም የምንገነዘበው ነው፤ ቤተ ክርስቲያን ለሕዝብ የተፈጠረችና በሕዝብ መካከል ያለች በመሆኗ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰው ሁሉ በእርስዋ ላይም በቀጥታ ይደርሳል፤ ከዚህ አኳያ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምም በዚህ መዋዕለ ጾም ፍቅርን በተላበሰ ንስሓ እግዚአብሔርን እንድንጠይቅ በዚህ አጋጣሚ አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፤

በመጨረሻም፦ በመዋዕለ ጾሙ ስለ ሀገርና ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ፣ስለ ሕዝባችን ዘላቂ ፍቅርና ስምምነት አጥብቀን እንድንጸልይ፣እንደዚሁም በግጭቱና በድርቁ ለተጐዱ ወገኖቻችን ካለን በማካፈል የችግሮቻቸው ተካፋይ እንድንሆን፣ ከዚህም ጋር ለሀገራዊ ሰላምና ፍቅር መሳካት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ መዋዕለ ጾሙን እንድናሳልፍ በእግዚአብሔር ስም መልእክታችንን በድጋሚ እናስተላልፋለን ።

እግዚአብሔር ወርኀ ጾሙን በሰላም አስፈጽሞ ለብርሃነ ትንሣኤው በደPና ያድርሰን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝባችንን ይባርክ፤ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/001-2-1000.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32022-02-28 14:20:302025-01-28 14:21:26የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ጥር 11 ቀን 2014 ዓ.ም የጥምቀት በዓልን በማስመልከት በጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት በተወካያቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል። Link to: ጥር 11 ቀን 2014 ዓ.ም የጥምቀት በዓልን በማስመልከት በጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት በተወካያቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል። ጥር 11 ቀን 2014 ዓ.ም የጥምቀት በዓልን በማስመልከት... Link to: ሚያዝያ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ቅዱስነታቸው የትንሣኤ በዓል በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል Link to: ሚያዝያ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ቅዱስነታቸው የትንሣኤ በዓል በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል ሚያዝያ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ቅዱስነታቸው የትንሣኤ በዓል...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top