https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/005-3-1000.jpg
664
1000
tc
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg
tc2024-12-05 10:55:492024-12-05 10:57:32በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ዐበይት የሥራ ክንውኖችና አባታዊ መመሪያዎች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በቅዱስ ፓትርያርክነት ሥልጣን ከተሠየሙበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ በቅዱስ ሲኖዶስ እያስወሰኑ ለቤተ ክርስቲያናችን በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መቀላጠፍ ዐይነተኛ ጠቀሜታ ያላቸው መመሪያዎችን አስተላልፈዋል፡፡
በቅዱስ ፓትርያርኩ ከተሰጡት ውጤታማ መመሪያዎችና ከተከናወኑት ተግባራት ውስጥ በጒልሕ የሚታወቁ ከዚህ በፊት ያልተደፈሩና በታሪክ ሊታወሱ የሚገባቸው እንዲሁም በመጪው ትውልድ ዘንድ በውጤታማነታቸው ሲዘከሩ መኖር ያለባቸውን ብቻ በጥቂቱ በመምረጥ ከዚህ ቀጥሎ በአጭሩ እናቀርባለን፡፡