• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

ከሚያዝያ 24 ቀን እስከ 29 ቀን 2010 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡

May 7, 2018

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ አምስት ንኡስ አንቀጽ 164 በተደነገገው መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ የዘንድሮውን የርክበ ካህናት ጉባኤ በማስመልከት የስብሰባው መክፈቻ ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከበዓሉ ዋዜማ ከሚያዝያ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ለአንድ ሱባኤ ያህል ባደረገው ስብሰባ ለሀገራችንና ለቤተ ክርስቲያናችን የሚበጁ ጠቀሜታ ያላቸውን ውሳኔዎች አሳልፎአል፡፡ ከውሳኔዎቹም መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ለጉባኤው በቀረበው አጀንዳ ተራ ቊጥር 1 የተገለጸውን በተመለከተ፤ የጉባኤው መክፈቻ ንግግር፣ ትምህርትና መመሪያ የቤተ ክርስቲያኒቱንና የሀገሪቱን ሁለተናዊ ገጽታ የዳሰሰ፣ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎትን የሚገነባ ተልዕኮ ያለው በመሆኑ ምልአተ ጉባኤው በበሙሉ ድምፅ ተቀብሎታል።
2. ከግንቦት ወር 2009 ዓ.ም. እስከ ሚያስዝያ 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤና በቋሚ ሲኖዶስ የተላለፉ ውሳኔዎች በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ አማካይነት ቀርበው ምልአተ ጉባኤው በአፈጻጸማቸው ዙሪያ ከተወያየ በኋላ አስፈላጊውን መመሪያ በመስጠት ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡
3. በተለያየ ምክንያት የሥራ ዝውውር እንዲደረግላቸው ጥያቄ ያቀረቡ አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳትና ጳጳሳት የጥያቄያቸው አስፈላጊነት በቅዱስ ሲኖዶስ ከተጠና በኋላ ዝውውሩ ተፈጽሞላቸዋል፤
4. እናት አባታቸው ሙተውባቸው ሰብሳቢ ያጡ ሕፃናትን እያሳደገና እያስተማረ ለቁም ነገር ያበቃ ዘንድ ቀደም ሲል ቤተ ክርስቲያኒቱ ያቋቋመችው የሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ርዳታ ለጋሾች ጋር ያለውን የቅርብ ግንኙነት በበለጠ እያጠናከረ ሥራውን ይቀጥል ዘንድ ምልአተ ጉባኤው መመሪያን ሰጥቷል፤
5. የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከተሠየሙበት ጊዜ ጀምሮ እያደረጉት ያለው ታሪካዊ ንግግር፣ ሀገራዊ አንድነትን፣ ፍቅርና ትሕትናን የሚያስተምር፣ ሰላምንና መረጋጋትን የሚያበሥር፣ የሩቁንና የቅርቡን የሚያስተባብር መንግሥታዊ ኀላፊነት የተሞላበት መልእክት በመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በአክብሮት ተቀብሎታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየክልሉ እየተዘዋወሩ በወንድማማች ሕዝቦች መካከል የተፈጠረው መቃቃር ይቅርታ ባልተለየው መንፈስ ተወግዶ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን መመሪያ ከመስጠት ጋር እያደረጉት ያለውን ከፍተኛ ጥረት ቅዱስ ሲኖዶስ በሙሉ ልብ ደግፎታል፤ የጥረቱም አካል በመሆን የበኩሉን ድርሻ እንደሚያበረክት ምልአተ ጉባኤው ተስማምቷል፡፡
6. ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የመጡት ክቡር የእስራኤል ሀገር ፕሬዚዳንት ሪቨን ሪቢሊን የርክበ ካህናቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በሚጀመርበት ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በፓትርያርኬቱ ተገኝተው ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ጎብኝተዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ስለ ዴር ሡልጣን ገዳማችን ሁኔታ ለ30 ደቂቃ ያህል የጋራ ውይይት ካደረግን በኋላ በኢየሩሳሌም ያሉት ገዳማት በሙሉ እንደሚታደሱ፣ በተለይም አሁን በቅርቡ የመፍረስ አደጋ የደረሰበት የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ እንደሚታደስ የቃል ተስፋ በመስጠት አረጋግጠውልናል፡፡
7. እግዚአብሔርን መፍራት የመጀመሪያው ጥበብ እንደሆነ እየተገነዘበ የመጣው ወጣቱ ትውልድ፤ ሀገሩንና ሃይማኖቱን፣ ባህሉንና ቋንቋውን፣ ሥርዓቱንና ትውፊቱን ከመጠበቅ ጋር ሥራ የመፍጠር ክሂሎቱን በበለጠ አጎልብቶ ሀገሩን እንዲያለማ ቅዱስ ሲኖዶስ አደራውን ጥሎበታል፡፡
8. የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ከተጣለበት ጊዜ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያናችን የግንባታው ሥራ ማከናወኛ የሚሆን ገንዘብ እንዲያዋጣ ሕዝቡን ከማስተባበር ደረጃ ጀምሮ አስፈላጊውን የገንዘብ ድጋፍ ሁሉ ከመለገስ ወደኋላ ያለችበት ጊዜ እንደሌለ ቢታወቅም፣ የማጠናቀቂያው የደወል ድምፅ እስካልተሰማ ድረስ የማስተባበሩ ሥራም ሆነ የእርዳታ ገንዘብ አሰባሰቡ ተግባር እንዲቀጥል ማድረግ ሀገራዊ ግዴታ መሆኑን ትገነዘባለች፡፡

ከዚህ አንጻር የግድቡን ሥራ ለማጠናቀቅ ሁሉም ኅብረተሰብ የጋራ ኀላፊነት ያለበት መሆኑን በመገንዘብና በውል በመረዳት የርዳታ እጁን እንዲዘረጋ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከዚህ በላይ በተገለጹትና በሌሎችም መንፈሳዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ሲወያይ ሰንብቶ አስፈላጊዎቹን በመወሰን ስብሰባውን በጸሎት አጠናቋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/007-3.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32018-05-07 14:04:402024-12-10 14:07:18ከሚያዝያ 24 ቀን እስከ 29 ቀን 2010 ዓ.ም የተካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ... Link to: ሐምሌ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ ልዩ አስቸኳይ ጉባኤ Link to: ሐምሌ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ ልዩ አስቸኳይ ጉባኤ ሐምሌ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ ልዩ አስቸኳይ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top