• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

መስከረም 1 ቀን 2015 ዓ.ም ርዕሰ ዐውደ ዓመት የዘመን መለወጫ በዓል መግባትን አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡

September 11, 2022

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
በሕመም ምክንት በየጸበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵውያት በሙሉ፤

የዓመታትና የአዝማናት ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለአዲሱ ዓመት ለሁለት ሺሕ ዐሥራ አምስት ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሉቃስ በሰላም አደረሳችሁ።

“ወዓመቲከኒ ለትውልደ ትውልድ
ዓመቶችህ ለልጅ ልጅ ናቸው፤”
(መዝ. ፻፩፥፳፬)፡፡

ይህንን ቃለ እግዚአብሔር የተናገረው እግዚአብሔር በቅብእ ቅዱስ አማካኝነት ሀብተ ትንቢት ወመዝሙር ያሳደረበት ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ነው፤ የቃሉ መሠረተ ሐሳብም ዓመታት የእግዚአብሔር ስጦታ መሆናቸውን፣ እንደዚሁም የተሰጡት ለሰው ልጆች መሆናቸውን ይገልጻል፡፡ በእርግጥም ዓመታት ከእግዚአብሔር ለሰው ልጆች የተሰጡ ሀብቶች ናቸው፤ ዓመታት፣ ወራት፣ ዕለታት፣ ቀናት፣ ሰዓታት የሚያስፈልጉት ለሰው ልጅ እንጂ ለእግዚአብሔርና በመንፈሳዊ ዓለም ለሚገኙ ፍጡራን አይደለም፤ ምክንያቱም ሰው በደካማው ዓለም የሚኖር ደካማ ፍጡር ስለሆነ ለኑሮው ጊዜያት የግድ ያስፈልጉታል፤ በመንፈሳዊ ዓለም የሚገኙ ፍጡራን ግን፣ ድካም የሌለባቸው ትጉሃን ስለሆኑ፣ ዓመትም ቀንም ሰዓትም ወዘተ አያስፈልጋቸውም፤ የሰዓት መለኪያ ብርሃንም የላቸውም፤ ምክንያቱም ያሉበት ዓለም ሁሌም ብርሃን እንጂ ጨለማ ስለማይፈራረቀው፣ እንደዚሁም ተለዋዋጭ አየርም ሆነ ዕድሜ ስለሌላቸው ማለት ነው፤ ለሰው ግን የጊዜ መለኪያ የሚሆኑ ብርሃናትና አዝማናት ወዘተ የተመደቡለት ስለሆነ፣ በእነርሱ እየተመራ ጊዜያትን ይለካል፤ ዓመታትን ወራትንና ቀናትን ወዘተ ይቈጥራል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

ዓመታት ከእግዚአብሔር ለእኛ የተሰጡን ያለምክንያት አይደለም፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ሁሉ ክብርም ጥቅምም አለውና ልናከብረውና ልንጠቀምበት እንጂ፤ ሁላችንም እንደምንገነዘበው ጊዜ ትልቁና ቀዳሚው የሥራ መሣሪያ ነው፡፡ እህልን ዘርተን የዓመት ምግባችንን የምናገኘው ወርኀ ክረምት ስለተሰጠን ነው፤ ይህ ወቅት ባይኖር ኖሮ የእርሻ ሥራ ሠርተን ራሳችንን መመገብ እንደማንችል የምንስተው አይሆንም፡፡ ከዚህ አንጻር ዓመታትንና ወቅቶችን እንደ አመቺነታቸው እየተጠቀምን ልንሠራባቸው እግዚአብሔር አመቻችቶ ሰጥቶናል ማለት ነው፤ ስለዚህ በብሂለ አበው “ጊዜ ሳለ ሩጥ ….” እንደሚባለው ሁሉንም በጊዜው ጊዜ መሥራትና ተጠቃሚ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ሰውም ሆነ ጊዜ ለሥራ የተፈጠሩበት ምክንያት መክበርም መዳንም ማግኘትም ማደግም መልማትም በሥራና በሥራ ብቻ የሚገኝ ከመሆኑ የተነሣ እንደሆነ ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፤ “ብላዕ በሐፈ ገጽከ፤ በፊትህ ላብ እንጀራህን ብላ” የሚለው አምላካዊ ትእዛዝም ይህንን ይገልጻል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

እግዚአብሔር አምላክ ያለመታከት ሠርተን ራሳችንን በራሳችን የምናስተዳድርባት በሀብትና በጊዜ የተዋበች ምድር አስረክቦናል፤ ምድሪቱንም ለእኛ በሚመች አኳኋን አበጅተን እንድንጠቀምባት የሚያስችል አእምሮና ጒልበትም ከጤና ጋር ሰጥቶናል፤ ሐቁ ይህ ከሆነ ታድያ ለምንድን ነው በምድራችን ሥጋትና ጭንቀት፤ ረኃብና ዕርዛት፣ የሀብት እጥረትና የእርስ በርስ ግጭት በስፋት የሚታየው የሚለውን ጥያቄ ሰው ሁሉ በጥልቀት ሊያጤነው ይገባል፡፡ እግዚአብሔር የሰጠን ምድር አሁንም ለፍጡራን የሚበቃ የተትረፈረፈ ሀብት ያለጥርጥር አላት፣ የአጠቃቀም ጉዳይ ካልሆነ በቀር ሀብት የሌለው የምድር አካባቢ ፈጽሞ የለም፡፡ ይህም ከሆነ ሁሉም ወደሥራና ሥራ ብቻ ተሰማርቶ ጥረቱን ከቀጠለ የሚያጣው ነገር የለም ማለት ነው፣ ሰው ጤና ዕውቀትና ሰላም ካለው ሀብታም ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ከተሟሉለት ሌላው ሁሉ እግዚአብሔር ከሰጠው ምድር ሠርቶ የሚያገኘው ነው፡፡ ሰላም ከሌለ ግን ነገሩ ሁሉ ጨለማ ይሆንበታል፤ አካላዊና አእምሮአዊ ጤናውም ይደፈርስና ሳያጣ ያጣ ወደ መሆን ይቀየራል፡፡ ዛሬ በሀገራችንም ሆነ በዓለማችን እየተከሠተ ያለው ሐቅ ይኸው ነው፡፡

ይህ የሰላም ዕጦት በሀገራችን በኢትዮጵያ በርከት ላሉ ዓመታት እየተደጋገመ በመከሠቱ፣ በዚህ ጠንቅ ሕዝባችን ሳያጣ ያጣ ሆኖአል፤ ኢትዮጵያን በመሰለች ለምና ምድራዊት ገነት ተቀምጠን፣ በዓለም ውስጥ የድህነት ተምሳሌት ሆነን መገኘታችን፣ የሁላችንም ኅሊና ሊኰረኲረው ይገባል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

በአዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን ሁሉ በአጽንዖት የምንመክረው ዐቢይ ምክር በግጭት ችግሮቻችንን መፍታት በፍጹም አንችልም፤ በመራራቅም ማደግ አንችልም፤ በተለያየን ቊጥር ድህነታችንን ከማስቀጠልና ደካሞች ከመሆን በቀር የምናገኘው አንዳች ፋይዳ የለም፤ እውነቱ ይህ ከሆነ ከገባንበት ያላስፈላጊ ግጭት በፍጥነት ወጥተን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት ወደሚያስችል ወደ ምክክርና ውይይት እንግባ፤ አዲሱ ዓመት እውነተኛ አዲስ ዓመት ሊሆን የሚችለው ይህንን ያደረግን እንደሆነ ነው፡፡ አሮጌውን አስተሳሰብ እንዳለ ተሸክመን ለመቀጠል እየዳዳን ከሆነ አዲስ ዓመት ማለቱ የአፍና የጆሮ ቀለብ ከመሆን በቀር የሚሰጠን አንዳች ትርጒም የለም፡፡ ስለሆነም አዲሱን ዓመት አዲስ የሆነ የሰላምና የዕርቅ የስምምነትና የአንድነት የይቅርታና የምሕረት የፍትሕና የእኩልነት መርሕ አንግበን ፍጹም ሰላምን ለማንገሥ በቊርጥ ማሰብና መነሣሣት አለብን፣ ይህንንም ለማሳካት በአንድ አዳራሽ፣ በአንድ ጠረጴዛ ተገናኝተን ችግሮቻችንን በውይይትና በምክክር እንድንፈታ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

በመጨረሻም አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር የበረከት የእድገት የሃይማኖትና የልማት ዓመት እንዲሆንልን ወደ እግዚአብሔር በመጸለይና በብሩህ ተስፋ እንድንቀበለው መልእክታችንን በድጋሚ በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር መልካም አዲስ ዓመት ያድርግልን፤
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/001-2-1000.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32022-09-11 14:25:132025-01-28 14:25:52መስከረም 1 ቀን 2015 ዓ.ም ርዕሰ ዐውደ ዓመት የዘመን መለወጫ በዓል መግባትን አስመልከቶ የተሰጠ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ነሐሴ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የፆመ ፍልሰታ መግባትን አስመልክተው የተላለፈ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ነሐሴ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የፆመ ፍልሰታ መግባትን አስመልክተው የተላለፈ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ነሐሴ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የፆመ ፍልሰታ... Link to: መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል የቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል የቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል የቅዱስነታቸው...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top