• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

ሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጅጅጋ፣ በጎዴ ከተማና በሌሎችም ከተሞች በደረሰው አሠቃቂ ግድያና ዘረፋ እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥተዋል

August 6, 2018

ሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጅጅጋ፣ በጎዴ ከተማና በሌሎችም ከተሞች በደረሰው አሠቃቂ ግድያና ዘረፋ ምክንያት በየመጠለያው በረኃብ፣ በጽምና በዕርዛት ለሚሠቃዩ ካህናትና ምእመናን መንግሥት ተፋጥኖ እንዲደርስላቸውና የነፍስ አድን ሥራ እንዲሠራ በአጽንዖት አሳሰበ፡፡ ማሳሰቢያውን ቅዱስነታቸው እንደሚከተለው አስታውቀዋል፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በረዥም የታሪክ ጒዞዋ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በእኩልነት ደረጃ ስታገለግል የኖረች እናት ቤተ ክርስቲያን ናት አሁንም አገልግሎቷን ከመፈጸም የተገታችበት ጊዜ የለም፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረ ሰቦችና ሕዝቦች ሀገር ብትሆንም ሕዝቦቿ በሃይማኖት፣ በጎሣና በቋንቋ ሳይለያይዩ ሀገርን የሚወር፤ ነፃነትን የሚገፍፍ ጠላት በሀገር ላይ ሲነሣ አንድነቱን አጠናክሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ የሀገሩን ነፃነት ሲያስከብር ኖሮአል፡፡ በተለይም የክርስትናና የእስልምና እምነት ተከታዮች በወንድማማችነት ተሳስበው የኖሩት አንዱ የሌላውን እምነትና ሥርዐት ሳይነካ ከኢትዮጵያዊነት ስሜት በመነጨ መተሳሰብና እውነተኛ ፍቅር ነው፡፡

ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሕግና መንግሥት ባለበት ሀገር በአንዳንድ የክልልና የዞን መስተዳድሮች በባሌ ጎባ፣ በጣና በለስ፣ በኦሮምያ ክልል፣ አሁን ሰሞኑን ደግሞ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልና በአንዳንድ ቦታዎች በተለያየ ምክንያት በሚፈጠር የርስ በርስ ግጭት መነሻነት በአርኣያ እግዚአብሔር የተፈጠረ፣ በቅዱስ ረድኤቱ የከበረ፣ ሕያዊት፣ ነባቢት ነፍስ የተዋሐደችው፣ ፍጹም አእምሮና ዕውቀት የተሰጠው የሰው ነፍስ እየጠፋ እናያለን፤ ይልቁንም በሱማሌ ክልል ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፤ ካህናት ተገድለዋል፤ ንብረት ተዘርፎአል፡፡ ዛሬ በመላ ሀገራችን ከመሐል ኢትዮጵያ እስከጠረፍ ዳርቻ ባሉት ክልሎችና የመስተዳድር ዞኖች ሰላም፣ ፍቅር አንድነት መከባበርና መቻቻል፤ እየተደማመጡና እየተናበቡ መሥራት በበለጠ እንዲዳብርና እንዲሰፍን የአመራር መርሕ በስፋትና በጥልቀት እየተሰጠ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ ለሚተላለፈው መመሪያና የሰላም መልእክት ትኵረት ባለመስጠት የሀገርና የወገን ፍቅር ስሜት የተለየው የጭካኔ ሥራን መሥራት ከኢትዮጵያውያን ዜጎች የሚጠበቅ ተግባር ሆኖ አላገኘነውም፡፡ ይህ መወገዝ ያለበት የዐመፅ ተግባር አብረው በኖሩ ወንድማማቾች መካከል የፈጠረው ግጭት፤ አለመግባባትና መቃቃር በዚህ ሳቢያ እየተካሄደ ያለው መጠፋፋት እየሰፋና እያደገ ወደሌላ ከመሸጋገሩ በፊት ከወዲሁ ታስቦበት ተፋጥኖ ይገታ ዘንድ የባለ ድርሻ አካላት ሁሉ መረባረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም የተፈጠረው ችግር ተወግዶ የተሟላ ሰላምና መረጋጋት እውን እስከሚሆን ድረስ የመፍትሔው አካል በመሆን የሚቻላትን ሁሉ በመፈጸምና በማስፈጸም ያለባትን ሀገራዊ ግዴታና ኀላፊነት በተግባር ማረጋገጥ ይጠበቅባታል፡፡ የሀገሪቱንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሰላምና መረጋጋት በሚጎዳ መንገድ የሚሄዱ ግለሰቦች ሁሉ እንዲስተካከሉ ከእግዚአብሔር ሕግ አኳያ ምክርና ትምህርት በመለገስና በማስተላለፍ ዓላማዋና ዐይነተኛው ተግባርዋ እንደሆነም ማስገንዘብ ይኖርባታል፡፡ ስለዚህ ሰላምና መረጋጋት የሚመነጨው ከቤተ ሰብና ኅብረተ ሰብ ስለሆነ፤ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲመክሩ፣ እንዲገሥጹ እንዲያስተምሩ ያስፈልጋል፡፡

ኅብረተሰቡም በዘር በሃይማኖትና በጎሣ ሳይለያይ በሀገራችን በአንዳንድ አካባቢ እየተሰማና እየታየ ካለው መጥፎ እንቅስቃሴ ራሱን እንዲገታ እንዲቈጣጠር፤ ካህናትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም የመልካም ሥነ ምግባር መሠረት በሆነችው ሀገራችን ላይ ችግሩ በተከሠተበት አካባቢ እየተገኙ ትምህርተ ወንጌል እየሰጡ የማረጋጋት፣ የማጽናናትና የማስታረቅ ሥራን እንዲሠሩ፡፡ ይህን አላስፈላጊ ግጭት ከሕዝባችንና ከሀገራችን እግዚአብሔር እንዲያርቅልን ጾመ ፍልሰታ ለማርያምን ምክንያት በማድግ ሙሉ ሱባኤውን በሁሉም ገዳማትና አድባራት ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ፤ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጅጅጋ፣ በጎዴ ከተማና በሌሎችም ከተሞች በደረሰው አሠቃቂ ግድያና ዘረፋ ምክንያት በየመጠለያው በረኃብ፣ በጽምና በዕርዛት ለሚሠቃዩ ካህናትና ምእመናን መንግሥት ተፋጥኖ እንዲደርስላቸውና የነፍስ አድን ሥራ እንዲሠራ በአጽንዖት እናሳስባለን፡፡

ለሞቱት ወገኖቻችንም በመላ ገዳማትና አድባራት ጸሎተ ፍትሐት እንዲደረግ፤ በችግሩ ዙሪያ የሚገኙ የክልልና የዞን መስተዳድር አካላትም የገላጋይ ያለህ የሚል ሮሮ እስከሚሰማ ድረስ ሳይጠብቁ በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠውን ድንጋጌ በማክበርና በማስከበር ከመንግሥትና ከሕዝብ የተረከቡትን ኀላፊነት በብቃት እንዲወጡ በቤተ ክርስቲያናችን ስም አደራ እያለን ይህን መልእክት እናስተላልፋለን፡፡ ኅልፈተ ሕይወት ያጋጠማቸው ወገኖቻችንን እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበልልን ያዘኑትን እንዲያረጋጋልን፤ የተጎዱትን በምሕረቱ እንዲጎበኝልን፤ ዘላቂ ሰላምም እንዲሰጠን እንጸልያለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/007-3.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32018-08-06 09:12:152025-01-27 09:14:41ሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጅጅጋ፣ በጎዴ ከተማና በሌሎችም ከተሞች በደረሰው አሠቃቂ ግድያና ዘረፋ እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥተዋል
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሲኖዶሳዊ ዕርቅ፣ በሰላምና በአንድነት ወደ ሀገራቸው መግባታቸውን አስመልክቶ መንግሥት በሚሊኒየም አዳራሽ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ Link to: ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሲኖዶሳዊ ዕርቅ፣ በሰላምና በአንድነት ወደ ሀገራቸው መግባታቸውን አስመልክቶ መንግሥት በሚሊኒየም አዳራሽ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ... Link to: ነሐሴ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. የጾመ ፍልሰታ ሙሉ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ Link to: ነሐሴ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. የጾመ ፍልሰታ ሙሉ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ነሐሴ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. የጾመ ፍልሰታ ሙሉ ቃለ ምዕዳንና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top