• Amharic  
  • English 
  • Home
  • Papal Messages
  • Biography
  • Patriarchs
  • Contact
  • Menu Menu

ሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓ.ም በአባቶች መካከል በተፈጠረው ልዩነት የተላለፈው ቃለ ውግዘት ተነሣ

July 30, 2018

ሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓ.ም በአባቶች መካከል በተፈጠረው ልዩነት የተላለፈው ቃለ ውግዘት ተነሣ ይኽንኑ አስምልከተው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የቅዱስ ሲኖዶስ ወሳኔ በመገናኛ ብዙኃን አስተላልፈዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ሐዋርያዊት፣ ጥንታዊትና ታሪካዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በረጅም የታሪክ ዘመኗ አንድነቷን ጠብቃ፤ የሀገሪቱንም አንድነትና ነፃነት በማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋፅ ስታደርግ ኑራለች፤ አሁንም ከማድረግ የተቈጠበችበት ጊዜ የለም፡፡

ይህች ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ከብዙ ዘመን በኋላ ከራስዋ ሊቃውንት መካከል መርጣ ከኤጲስ ቆጶስነት እስከ ፓትርያርክነት ለመሾም የበቃች ቢሆንም ከሁለት ዐሥርት ዓመታት ወዲህ በአንዳንድ አላስፈላጊ ምክንያት ያልተጠበቁ ችግሮች መከሠታቸው አልቀረም፤ እነዚህን ችግሮች በውይይት፤ በሰላምና በፍቅር በማስተካከል የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በጋራ ማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያይቶ ከውድ እናት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ወጥተው በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ውሳኔን አሳልፎአል፡፡

ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ልኡካንን ለአምስተኛ ጊዜ ወደ ሰሜን አሜሪካ እንዲሄዱ በማድረግ፤ ልኡካኑ በቦታው ተገኝተው፤ ተገቢውን ውይይት አካሂደው፤ ለውጤት የሚበቃ ነጥብ መዝግበው የተደረሰበትን የሚያስረዳ መግለጫን አቅርበዋል፡፡
ከቀረበው የዕርቀ ሰላሙ የጋራ ስምምነት ሰነድ ላይ መረዳት እንደተቻለው፦

ሀ/ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ሆኖ፤ በመንበረ ፓትርያርኩ ግቢ ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ቦታ ተዘጋጅቶ፤ የሚያስፈልጋቸው ሁሉ ተሟልቶ በክብር እንዲቀመጡ፤ የሥራ ድርሻን በተመለከተም፤ ጸሎትና ቡራኬን በማድረግ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ፤
ለ/ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን በተመለከተም በሕገ ቤተ ክርስቲያን ድንጋጌ መሠረት የአስተዳደር ሥራን እየሠሩ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንዲመሩ ሆኖ፤ የሁለቱም ፓትርያርኮች ስም የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለችበት ቦታ ሁሉ ዘወትር በጸሎት እንዲነሣ የሚሉትና የመሳሰሉት ዐበይት ነጥቦች በልኡካኑ መግለጫ ተመዝግበው እንደሚገኙ ምልአተ ጉባኤው ተገንዝቧል፤ ከዚህ ግንዛቤ በመነሣት በፊደል ተራ ቁጥር ‹‹ሀ›› እና ‹‹ለ›› የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፤

1. በውጭ ሀገር በሚኖሩ አባቶችና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል የነበረው መለያየት ለውግዘት በሚዳርግ ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበር የታወቀ ነው፡፡ አሁን ግን ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ነውና ብዙ ጊዜ ሲደከምበት የቆየው ታሪካዊው ዕርቀ ሰላም ለሠመረ ውጤት በመብቃቱ በጋራ ስምምነቱ መሠረት ጳጒሜን 2 ቀን 1984 ዓ.ም.፤ መስከረም 15 ቀን 1985 ዓ.ም. እና ጥር 25 ቀን 1999 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ የተላለፈው ቃለ ውግዘት ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ቃለ ውግዘቱ ተነሥቶአል፡፡
2. ከልዩነት በፊት የተሾሙ ነባር ሊቃነ ጳጳሳትም በውጭ ሀገርም ሆነ በሀገር ቤት በቅዱስ ሲኖዶ ውሳኔ ተመድበው እንዲያገለግሉ ሆኖ፤ ከልዩነት በኋላ የተሾሙ ሊቃነ ጳጳሳትን፤ ጳጳሳትንና ኤጲስ ቆጶሳትን በተመለከተም ስያሜያቸው እንዳለ እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ በሀገር ውስጥና በውጭ አህጉረ ስብከት ተመድበው ይሠሩ ዘንድ ምልአተ ጉባኤው ተቀብሎአቸዋል፡፡
3. በአጠቃላይም በልኡካኑ የጋራ መግለጫ በተዘረዘሩት ነጥቦች ጥልቅ ውይይት በማካሄድ የቤተ ክርስቲያናችን አንድነት በበለጠ እንዲጠናከር፤ የሀገራችን ሰላምና መረጋጋት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሚያስችል ሁኔታ ላይ የበኩሉን ድርሻ መፈጸም እንዳለበት በማመን በመግለጫው ከ1-6 ተራ ቊጥር የተዘረዘሩትን ምልአተ ጉባኤው ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡
4. በመጨረሻም ይህ የቤተ ክርስቲያናችን አሳሳቢ ጉዳይ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሲከታተሉ የቆዩትን የተለያዩ የኮሚቴ አባላትን፤ ማኅበረ ካህናቱንና ማኅበረ ምእመናንን በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል የተከሠተው መለያየት የሀገሪቱ ችግር ጭምር መሆኑን በመገንዘብና ትኵረት በመስጠት ውድ የሀገር መሪነት ጊዜያቸውን ሠውተው ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው በታሪካዊው የዕርቀ ሰላም ጉባኤ ላይ በመገኘት አስተጋባኢና አሰባሳቢ የሆነ መመሪያን በመስጠት ብዙ ዘመን የተደከመበት ጉዳይ ፈጣን መፍትሔን እንዲያገኝ ላደረጉት ለኤፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ለክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ቅዱስ ሲኖዶስ ከፍ ያለ ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/007-3.jpg 664 1000 tc3 https://eotcp.org/e/wp-content/uploads/logo-en.svg tc32018-07-30 08:59:342025-01-27 09:01:30ሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓ.ም በአባቶች መካከል በተፈጠረው ልዩነት የተላለፈው ቃለ ውግዘት ተነሣ
Search Search

Recent Posts

  • ሃይማኖተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ
  • የኢትዮጵያ መንበረ ፓትርያርክ እና ሐዋርያዊ የሥልጣነ ክህነት ትውፊት
  • የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው የዐቢይ ጾምን መግባት በማስመልከት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል
  • ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ
  • በቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና የተከናወኑና በታሪክ የሚዘከሩ ዐበይት ተግባራት፤

Archives

  • February 2025
  • December 2024
  • October 2024
  • September 2024
  • August 2024
  • June 2024
  • May 2024
  • March 2024
  • October 2023
  • September 2023
  • November 2022
  • October 2022
  • September 2022
  • August 2022
  • June 2022
  • May 2022
  • April 2022
  • February 2022
  • January 2022
  • October 2021
  • September 2021
  • August 2021
  • May 2021
  • March 2021
  • January 2021
  • November 2020
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • May 2020
  • April 2020
  • March 2020
  • February 2020
  • January 2020
  • November 2019
  • October 2019
  • September 2019
  • July 2019
  • June 2019
  • May 2019
  • April 2019
  • March 2019
  • January 2019
  • October 2018
  • September 2018
  • August 2018
  • July 2018
  • May 2018
  • April 2018
  • February 2018
  • January 2018
  • October 2017
  • September 2017
  • August 2017
  • July 2017
  • June 2017
  • May 2017
  • April 2017
  • March 2017
  • February 2017
  • January 2017
  • October 2016
  • September 2016
  • August 2016
  • June 2016
  • May 2016
  • April 2016
  • March 2016
  • January 2016
  • November 2015
  • October 2015
  • September 2015
  • August 2015
  • May 2015
  • April 2015
  • February 2015
  • January 2015
  • November 2014
  • October 2014
  • September 2014
  • August 2014
  • May 2014
  • April 2014
  • February 2014
  • January 2014
  • October 2013
  • September 2013
  • June 2013
  • May 2013
  • March 2013
© Ethiopian Orthodox Tewahedo Church | Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ልኡካን ሽኝት ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም Link to: የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ልኡካን ሽኝት ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ልኡካን ሽኝት ሐምሌ 10... Link to: ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሃያ ሰባት ዓመታት በስደት ይኖሩ የነበሩት የኢትዮጵያ አራተኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በዕርቀ ሰላም እና በአንድነት ወደ ሀገራቸው ገብተዋል፡፡ Link to: ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሃያ ሰባት ዓመታት በስደት ይኖሩ የነበሩት የኢትዮጵያ አራተኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በዕርቀ ሰላም እና በአንድነት ወደ ሀገራቸው ገብተዋል፡፡ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሃያ ሰባት ዓመታት በስደት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top